ተማሪዎችን የታብሌት ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የማድረጉ ጅማሮ

Wednesday, 22 November 2017 12:07

 

በቴክኖሎጂ ተደራሽ ያልሆኑ ተማሪዎችን  በመድረሱ ረገድ የተለያዩ ሥራዎች ይሰራሉ። በዚህ በኩል እገዛ እያደረጉ ካሉት ድርጅቶች መካከል አንዱ ሰፖርት ኤጁኬሽን ነው። ድርጅቱ ከዩኒቨርስቲ ኦፍ አለባማ ጋር በመተባበር ተማሪዎች ታብሌቶችን በነፃ እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ነው። ታብሌቶቹ በውስጣቸው የፕላዝማ ትምህርቶችን፣ማጣቀሻ መፃህፍትን እና የመሳሰሉትን  መርጃ አጋዥ ግብዓቶች እንዲያካትቱ ተደርጓል። ተማሪው ምንም አይነት የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት ሳያስፈልገው እነዚህን ታብሌቶች መጠቀም የሚችል መሆኑ ታውቋል። ጉዳዩን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡን የሰፖርት ኤጁኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ አሰፋ፤ ሥራው የተጀመረው በ2008 ዓም መሆኑን ገልፀው፤ ለጊዜውም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ሁለት ትምህርት ቤቶች በናሙናነት የተጀመረ መሆኑን ገልፀውልናል።

 

 አቶ ሙሉጌታ ድርጅቱ  ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በደረሰው ስምምነት መሰረት አብሮ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።  የትምህርት መፃህፍትን በማተምና ለተማሪዎች በማዳረስ እንዲሁም በአጠቃላይ በተደራሽነት አንፃር ከፍተኛ ችግር ስላለ በዚህ በኩል  ታብሌቶቹ ከፍተኛ እገዛ ያላቸው መሆኑን አቶ ሙሉጌታ ጨምረው አመልክተዋል።

 

 

ታብሌቶቹ የፕላዝማ ትምህርቶች በውስጣቸው አካተው እንዲይዙ የተደረገ መሆኑም ተመልክቷል። የፕላዝማ ትምህርቶች በኤሌክትሪክ መቆራረጥና በመሳሰሉት ምክንያቶች ትምህርት ለተማሪዎች በበቂ ሁኔታ የማይደርሱባቸው ሁኔታዎች ስላሉ ታብሌቶቹ የፕላዝማ ትምህርትን ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያገለግሉ መሆኑም ታውቋል። በዚህ ረገድ ከሰፖርት ኤጁኬሽን ጋር በመሆን እገዛ እያደረገ ያለው በአሜሪካ ዩኒቨርስቲ ኦፍ አላባማ ሲሆን ታብሌቶቹን ለተማሪዎቹ በማድረሱ ረገድ ሙሉ ወጪውን የሸፈነ መሆኑ ተመልክቷል።

 

ታብሌቶቹ ሰርበርና ኢንተርኔት ሳያስፈልጋቸው ተማሪዎቹ በቂ ትምህርትን በሚያገኙበት መልኩ በውስጣቸው አስፈላጊ የሆኑ የትምህርት ግብዓቶችን እንዲያካተቱ መደረጉ ታውቋል። ታብሌቶቹ ከዚህም በተጨማሪ የማጣቀሻ መፃህፍትንም ጭምር እንዲያካትቱ ተደርጓል። በገጠር ከኤሌክትሪክ ተደራሽነት ጋር ካለው ችግር ጋር በተያያዘ ታብሌቶቹን በመጠቀሙ ረገድ እክሎች እንዳይገጥሙ ሶላር የኃይል መሰብሰቢያ መሳሪያዎችም አብረው እንዲካተቱ ተደርጓል።

 

ይህም ታብሌቶቹን በቀላሉ ቻርጅ አድርጎ ለመጠቀም ይረዳል ተብሏል። ታብሌቶቹን ተማሪዎቹ እንዲያገኙ በማድረጉ ረገድ በአሁኑ ሰዓት ለናሙና በተመረጡት ትምህርት ቤቶች በነፃ የታደሉ ሲሆን በቀጣይ ግን አንድ ተማሪ አንድን ታብሌት ከአንድ መቶ የአሜሪካን ዶላር በታች በሆነ ዋጋ የሚያገኝበት ሁኔታ እንዲኖር የሚደረግ መሆኑን አቶ ሙሉጌታ ገልፀውልናል። በአሁኑ ሰዓት በኦሮሚያና በአማራ ክልል በተመረጡት ሁለት ናሙና ትምህርት ቤቶች በአጠቃላይ 3720 ታብሌቶች ለተማሪዎች ታድለዋል ተብሏል።  ታብሌቶቹ የታደሉት ለአስረኛና ለአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች ነው።

 

 በትምህርት ሚኒስቴር በአጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ የሚኒስትር ደኤታው አማካሪ የሆኑት አቶ ብርሀኑ ሞረዳ በበኩላቸው ታብሌቶቹን ለተማሪው በቀላል ዋጋ ተደራሽ በማድረጉ ረገድ ሀገር ውስጥ መገጣጠሙና ማምረቱ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

 

 በዚህ ዙሪያ የተለያዩ ድርጅቶች የሚሰሩ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው፤ በቀጣይ ሁሉም በተቀናጀ መልኩ እገዛ የሚያደርጉበት ሥርዓት የሚኖር መሆኑን አመልክተዋል። ኃላፊው ታብሌቶቹ በፕላዝማ ትምህርት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በቴክኒክ ብልሽትና በመብራት መቆራረጥ ያለውን ችግር ለመፍታት ያስችላል ተብሏል። ሁሉም የፕላዝማ ትምህርቶች ተቀርፀው በታብሌቶቹ ውስጥ እንዲካተተቱ መደረጉ በፕላዝማ ትምህርት አሰጣጥ ያለውን  ክፍተት ይሞለዋል ብለዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
154 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 137 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us