ናይጄሪያ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪ ልታደርግ ነው

Wednesday, 29 November 2017 12:43

“በናይጄሪያ የኤሌክትሪክ ኃይልን መንግስት ድጎማ ሲያደርግበት ቆይቷል” በሚል በቅርቡ ጭማሪ የሚደረግበት መሆኑን ሰሞኑን ፕሪሚየም ታይምስ ባሰራጨው ዘገባ አመልክቷል። ይህ የመንግስት እቅድ ይፋ የሆነው በቅርቡ በተካሄደው ስድስተኛው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንታዊ ፎረም ላይ ነው። ይሄንኑ ጉዳይ በተመለከተ ሀሳባቸውን የሰጡት የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የሚ ኦሲናባጆ የኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ ጭማሪው ዕቅድ ለለፕሬዝዳንቱ የቀረበ መሆኑ ታውቋል።

የናይጄሪያ መንግስት የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ ጭማሪ ማድረጉ የሀገሪቱን ኢንቨስትመንት ይጎዳል በሚል ጭማሪውን አዘግይቶት የቆየ ሲሆን፤ የዓለም ባንክ ግን የመንግስትን አቋም ሲቃወም የቆየ መሆኑን ዘገባው ያመለክታል። በሁኔታው የዓለም ባንክና ናይጄሪያ መንግስት ድርድር ሲያደርጉ ቆይቷል። በስተመጨረሻ ግን የናይጄሪያ መንግስት የታሪፍ ለውጥ በማድረጉ ውሳኔ ተስማምቷል። ይሁንና የታሪፍ ጭማሪው በናይጄሪያ የዋጋ ውድነትን ሊያባብስ ይችላል የሚል ሥጋትን አሳድሯል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
69 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us