የኬኒያ ኢኮኖሚ አሽቆለቆለ

Wednesday, 29 November 2017 12:46

 

ከምርጫው ውዝግብ ጋር በተያያዘ የኬኒያ ኢኮኖሚ ያሽቆለቆለ መሆኑን የአልጄዚራ ዘገባ አመልክቷል። እንደዘገባው ከሆነ የኬኒያ ኢኮኖሚ ከምርጫው ውዝግብ ጋር በተያያዘ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ክስረት ደርሶበታል። እንደዘገባው ከሆነ ኢኮኖሚው አሁን ባለበት ሂደት ተጨማሪ የማሽቆልቆል አደጋም ተጋርጦበታል። የኬኒያ የጀርባ አጥንት የሆነው የቱሪዝሙ ዘርፍ በቀደመው ምርጫም የከፋ መቀዛቀዝ ታይቶበት በብዙ ውጣ ውረድ ያገገመ ሲሆን፤ በአሁኑ የምርጫ ውጥረትም ተመሳሳይ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

 

 እንደ ፋይናሺያል ታይምስ ዘገባ ከሆነ ደግሞ የኬኒያ ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ የታየበት በቱሪዝሙ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በኮንስትራክሽኑ እንደዚሁም በበርካታ ዘርፎች ነው። በኬኒያ እ.ኤ.አ በ2007 የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ብጥብጥ 1 ሺህ 2 መቶ ሰዎች ሲሞቱ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል። ከዚያ በኋላም በነበረው ብሄራዊ ምርጫ ሀገሪቱ ተመሳሳይ የፖለቲካ ውጥረት ገጥሟት የነበረ ሲሆን ኢኮኖሚውም በዚያው መጠን የማሽቆልቆል አደጋ ገጥሟት ነበር። እንደ ፋይናሺያል ታይምስ ዘገባ ከሆነ መንግስት የሀገሪቱን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ትንበያ ይፋ ያደረገ ሲሆን አሁን ካለበት 5 ነጥብ 7 በመቶ በቀጣይ ዓመት ወደ 5 ነጥብ 5 በመቶ ያሽቆለቁላል ተብሎ ይጠበቃል። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
96 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 97 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us