ሱዳን የወርቅ ምርቷን የመጀመሪያ የኤክስፖርት ገቢዋ አደረገች

Wednesday, 27 December 2017 12:08

 

ሱዳን የውርቅ ምርቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲሆን በያዝነው የፈረጆች ዓመት ማጠናቀቂያም አጠቃላይ የምርት መጠኗ 105 ቶን መድረሱን የሱዳን ትሪብዩን ዘገባ ያመለክታል። የሱዳን ዋነኛ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ነዳጅ የነበረ ሲሆን  የደቡብ ሱዳን መገንጠልን ተከትሎ የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ክፉኛ አሽቆልቁሎ  ነበር። ሆኖም ሀገሪቱ በአሁኑ ሰዓት ሙሉ ትኩረቷን የወርቅ ማዕድን ላይ በማድረጓ ከዘርፉ የምታገኘው የገቢ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መሄዱን ዘገባዎች ያመለክታሉ። በዚህም በአሁኑ ሰዓት ወርቅ ዋነኛ የሱዳን የኤክስፖርት ገቢ ምንጭ መሆኑን ይሄው ዘገባ ጨምሮ ያመለክታል።

 

ሱዳን ከዋናው የወርቅ ምርት ባሻገር ባህላዊ ወርቅ አምራቾችን ሳይቀር በሰፊው የምታበረታታ ሲሆን ከሰሞኑም እነዚህኑ ባህላዊ ወርቅ አምራቾች በማበረታታት የሽልማት ሥነ ሥርዓት የተካሄደ መሆኑ ታውቋል። በአሁኑ ሠዓት ሀገሪቱ ባላት የወርቅ ምርት መጠን በአፍሪካ ደረጃ ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ የሁለተኝነት ደረጃ የያዘች መሆኗን ይሄው የሱዳን ትሪብዩን ዘገባ ጨምሮ ያመለክታል።

 

እንደ ዘገባው ከሆነ ሀገሪቱ በአፍሪካ የሁለተኝነት ደረጃን ከመያዝ ባለፈ በዓለም አቀፍ ደረጃም በዘጠንኛ ደረጃ ተቀምጣለች። እንደዘገባው ከሆነ መንግስት በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ከዘርፉ ያገኘው አጠቃላይ የገቢ መጠን 1 ነጥብ 9 ትሪሊዮን የሱዳን ፓውንድ ደርሷል። ሀገሪቱ የወርቅ ምርት ገቢዋን ለማሻሻል ከወሰደቻቸው እርምጃዎች መካከልም በከንትሮባንድ ከሀገር የሚወጣውን የወርቅ ምርት መጠን በሚገባ መቆጣጠር መቻሏ መሆኑን ዘገባው ጨምሮ ያመለክታል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
91 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 249 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us