ቴክኖ ሞባይል ፋንቶም 8 የተባለ ምርትን ይፋ አደረገ

Wednesday, 27 December 2017 12:11

 

     

በኢትዮጵያ የተንቀሳቃሽ ስልኮችን በማምረት የሚታወቀው ቴክኖ ሞባይል  ፋንቶም 8 በሚል የሚታወቅ አዲስ ምርትን ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል። ኩባንያው ምርቱን ይፋ ያደረገው ባሳለፍነው ቅዳሜ ታህሳስ 14 ቀን 2010 ዓ.ም በቦሌ መድሐኒያለም ቴክኖ ብራንድ መደብሩ ባካሄደው ሥነ ሥርዓት ነው።

       በዚሁ በርካታ እንግዶች በተገኙበት ሥነ ሥርዓት ላይ ይፋ የሆነው ይሄው አዲሱ አንድሮይድ ፋንቶም 8 ምርት በአመራረት ሂደቱ በርካታ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንዲያካትት የተደረገ መሆኑ ተመልክቷል። ስልኩ በዲዛይን፣በውበት በካሜራ የጥራት ደረጃና መረጃን በፍጥነት በመስጠት በብዙ መልኩ የተሻሻለ ምርት እንዲሆን ተደርጎ የተሰራ መሆኑ በዕለቱ በተደረገው ገለፃ ተመልክቷል።

የቴክኖ ሞባይል የብራንድ ማናጀር የሆኑት ቼል ሀይንግ በእለቱ አዲሱን ምርት አስመልክው በሰጡት ማብራሪያ “የኢትዮጵያ ገበያ በእጅጉ ለለውጥ የተጋለጠ ሲሆን እንዲሁም ምርቱ ላቅ ያለ የፈጠራ ክህሎትን በውበት ማራኪ ከሆነ ንድፍ ጋር የሚያጎላ ነው” ብለዋል።

      የቴክኖ ሞባይል ፋንቶም 8 ስማርት ፎን ከስማርት መንታ ሰልፊ ፍላሽ ጋር በ20 ሜጋ ፒክስሎች ከፊት ለፊት ካሜራ ጋር የተመረተ ነው። ከፊት ለፊት ያለው መንታ ቀለበት ፍላሽ  ፎቶዎችን በዝቅተኛ የብርሃን ወገግታ ባላቸው አካባቢዎች ፎቶግራፎችን ለማንሳት የሚያገለግል መሆኑ ታውቋል። አዲሱ ምርት ከዚህም በተጫማሪ 150 ደቂቃዎችን የንግግር ሰዓታትን እንደዚሁም 10 ደቂቃ ቻርጅ  የሚደረግ ባትሪን ያካተተ መሆኑ ታውቋል።

       ይሄው አዲሱ ፋንቶም 8 ከማይክሮ ሲም ጋር ወይም ከናኖ ሲም ካርድ ጋር አብሮ የሚሄድ እና እስከ 2 ቴራ ባይት ትራንስ ፍላሽ  መቀበል የሚችል እና 4 ሞጅሎችን፣ 20 ባንዶችን መቀበል የሚችል ነው። እንደዚሁም ከ 2 መቶ ሀገራት እና ዞኖች በላይ የሚሸፍን መሆኑ ታውቋል። ምርቱ ከዚህም በተጨማሪ  በአንድ በኩል አካሉ የብረት ጠርዝ ኖሮትና 2 ነጥብ 5 ዲ ድሮፐ ስክሪን-የታጠፈ የባትሪ ሽፋን ባከተተ መልኩ የተመረተ መሆኑ ተመልክቷል። ይህ ብቻ ሳይሆን 6 ጂቢ ራም + 2.6 ጊጋ ኸርዝ ሲፒዩ አልትራ ፋስት ገፅታ ያለው ሲሆን፤ ይሄውም 4 ጂ + እና የዳውሎድ ፍጥነቱም እስከ 3 መቶ ሜጋ ባይት በሰከንድ መሆኑ ተገልጿል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
305 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 247 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us