የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት አወዳድሮ ሊሸልም ነው

Wednesday, 27 December 2017 12:13

 

      የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) ሀሙስ ታህሳስ 19 ቀን 2010 በሚያካሂደው ሥነ ሥርዓት በበጎ አድራጎት ተግባር የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን የሚሸልም መሆኑን አስታውቋል።   የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ እና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት ቃሊቲ ማሰልጠኛ አካባቢ በሚገኘው የመሥሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚከናወን መሆኑን የልማት ማህበራቱ ህብረት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሸሻ ሸዋረጋ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

 

 የልማት ማህበራቱ ህብረት በበጎ ሥራቸው ተወዳድረው አሸናፊ የሆኑ አምስት ድርጅቶችን ለሽልማት የሚያበቃ መሆኑን ዶክተር መሸሻ በሰጡት በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ አመለክተዋል። በዚሁ ውድድር አምስት ድርጅቶች ለሽልማት የሚመረጡበት አሰራር ያለ መሆኑን ያመለከቱት ዶክተር መሸሻ፤ ይሁንና በወድድሩ ሂደት ሁለት ድርጅቶች እኩል ነጥብ ያመጡ በመሆናቸው ሽልማቱ በዕለቱ ለስድስት ድርጅቶች የሚሰጥ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል።

 

 እነዚህን ድርጅቶች ለሽልማት ለማብቃት የተቀመጡ መሰረታዊ መስፈርቶች መኖራቸውን የገለፁት ኃላፊው፤ ከእነዚህም መስፈርቶች መካከል በጥቂት ገንዘብ ብዙ የልማት ሥራን ማከናወን፣ የሰዎችን  ህይወት በዘላቂነት ለውጥ በሚያመጣ መልኩ የልማት ሥራን ማከናወን፣ከመንግስት የልማት ፕሮግራሞች ጋር ያለው የትስስር ሁኔታ፣የሴቶችን የልማት ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ የተሰራው የልማት ሥራና የዘለቄታ ውጤቱ በታሳቢነት ተጠቅሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ በልማቱ ሥራ ህብረተሰብን የማሳተፍ ሥራም ከመስፈርቶቹ መካከል አንዱ መሆኑ ተመልክቷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
89 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 195 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us