የህዝብና ቤት ቆጠራው ሂደት፤ ከየት ወዴት?

Wednesday, 03 January 2018 16:28

በኢትዮጵያ አራተኛው የቤትና ህዝብና ቤት ቆጠራ ሊካሄድ ቅድመ ዝግጅቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን የህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል። የህዝብና ቤት ቆጠራ; በመረጃ የተደገፈ ፖሊሲዎችን ለመቅረፅና የልማት ሥራዎችን ለማከናወን ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ።

የኢትዮጵያ የህዝብ ቆጠራ ታሪክ የሚያመለክተው የህዝብ ቆጠራው 1953 . የጀመረ መሆኑን ነው። ሆኖም በዚህ ወቅት የተካሄደው የህዝብ ቆጠራ አዲስ አበባን እና ታላላቅ ከተሞችን ብቻ የዳሰሰ እንጂ መላ ሀገሪቱን ባከተተ መልኩ የተካሄደ አልነበረም።

 ከዚህ በኋላ 1968 . ሀገር አቀፍ የህዝብና ቤት ቆጠራን ለማካሄድ ቢታሰብም በጊዜው የነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ውጥኑ ዳር እንዳይደርስ ያደረገው መሆኑን ከማዕከላዊ ስታስቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። መረጃው እንደሚያመለክተው ከሆነ በኢትዮጵያ የህዝብና ቤት ቆጠራ ታሪክ ሳይንሳዊ የቆጠራ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ የተካሄደው 1976 . ነው። ከዚያ በኋላም 1987 እንደዚሁም 1999 . ተካሂዷል። በኤፌዲሪ ህገ መንግስት የህዝብና ቤት ቆጠራ ድንጋጌ መሰረት የመጨረሻው ቆጠራ የተካሄደው 1999 . ሲሆን አራተኛው ቆጠራ መካሄድ የነበረበት 2009 . ቢሆንም አሁን ሊካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ያለው በያዝነው ዓመት ነው።

ከእነዚህ ሶስት ቆጠራዎች በኋላ አራተኛውን ቆጠራ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቶች በመደረግ ላይ ናቸው። የህዝብና ቤት ቆጠራ በየአስር ዓመቱ ልዩነት እንዲካሄድ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 103 ተደንግጓል የህገ መንግስቱንም ድንጋጌዎች ወደ መሬት ለማውረድ የሚያስችል አዋጅ ቁጥር 449/1997 እንዲወጣም ተደርጓል። በአሁኑ ሰዓት ለቆጠራው የሚደረጉ ቅድመ ዝግጅቶችም ይህንኑ ህግ መሰረት ያደረጉ ናቸው። የቆጠራ ሥራውንም እንዲያከናውን በህግ ኃላፊነት የተሰጠው የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን ነው።

ቆጣሪው ማነው?

እንደ ህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን መረጃ ከሆነ የህዝብ ቆጠራው የሚከናወነው በተለያየ ዘርፍ ተሰማርተው በሥራ ላይ ባሉ የመንግስት ሰራተኞች አማካኝነት ነው መምህራን፣ የግብርና ልማትና የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ቆጠራውን እንዲያከናውኑ ኃላፊነት የተሰጣቸው አካላት ናቸው። እነዚህ ቆጣሪዎች ቆጠራ ከማካሄዳቸው በፊት ተገቢውን ሥልጠና እንዲያገኙ የሚደረግ ሲሆን እስካሁንም ባለው ሂደት ከአሰልጣኞች ሥልጠና ጀምሮ ተከታታይ ሥልጠናዎች የተሰጡ መሆኑን የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል። በዚሁ በያዝነው ዓመት ለሚካሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ 145 ሺህ ቆጣሪዎችና 35 ሺህ ተቆጣጣሪዎች እንደዚሁም 2 ሺህ ያህል ቆጠራ ፅህፈት ቤት ሰራተኞች የሚሰማሩ መሆኑ ታውቋል።

የአራተኛውን ዙር ቆጠራ­ ምን ይለየዋል?

­­­­

እስከአሁን ባለው የሀገሪቱ የህዝብ ቆጠራ ሶስት ኦፊሴላዊ አጠቃላይ የህዝብ ቆጠራዎች ተካሂደዋል። የአሁኑን የህዝብና ቤት ቆጠራ የተለየ የሚያደርገው አንዱ ምክንያት ቆጠራው በታብሌት ኮምፒውተር አማካኝነት የሚከናወን መሆኑ ነው። መጠይቆቹ ከወረቀት ይልቅ በዲጂታል ታብሌቶች  እንዲካሄድ መደረጉ የተሰበሰቡትን መረጃዎች ወደ ኮምፒዩተር ገልብጦ ሪፖርቱን በፍጥነትና ለማደራጀትና ለመተንተን ያግዛል። በእጅ ፅሁፎች በኩል የሚታየውን አለመነበብም ችግር በቀላሉ ይቀርፋል። የመጨረሻውንም ውጤት ለህዝብ በመግለፁ በኩል ከዚህ ቀደም በነበሩት ቆጠራዎች የሚወስደውን ያህል ጊዜ የሚወስድበትም ሁኔታም አይኖርም

የመረጃው ሚስጥራዊነት

ቆጠራው የግለሰቦችን ማንነት በዝርዝር የሚመዘግብ በመሆኑ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሚሰበሰበውን መረጃ ሚስጥራዊነት በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎችና ስጋቶች ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል። እንደ ኮሚሽኑ መረጃ ከሆነ በቆጠራው ወቅት ከእያንዳንዱ ግለሰብ የሚሰበሰበው መረጃ በሚስጥር የተጠበቀ እንዲሆን ይደረጋል።

የዚህም መረጃ ሚስጥራዊነት በአዋጅ 449/1197 በተደገፈ መልኩ በቆጠራው ወቅት ማንኛውም ግለሰብ ስለራሱና ስለቤተሰቡ የሚሰጠው መረጃ በሙሉ በቡድንም ሆነ በተናጠል ለሌላ ማንኛውም አካል የማይገለፅ መሆኑ ተመልክቷል። የቆጠራው አላማ አጠቃላይ የሀገሪቱን ህዝቦች ቁጥርና ተያያዥ መረጃን ለመሰብሰብ እንጂ የአንድን ግለሰብ ወይንም ቤተሰብ መረጃ ነጥሎ ለማውጣት ያለመ አለመሆኑ የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል።

በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች ይቆጠራሉ?

የህዝብና ቤት ቆጠራው ከሚያካትታቸው አካላት መካከል በኢትዮጵያ የሚገኙ የውጭ ዜጎች ይገኙበታል። የውጭ ዜጎች የህዝብና የቤት ቆጠራው መጠይቅ የሚሞላው በእንግሊዘኛ ቋንቋ መሆኑ00000010 ከህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ይህ የቆጠራ መጠይቅ ለቆጠራ በተሰማሩ ባለሙያዎች የሚሞላ ሳይሆን በራሳቸው በግለሰቦቹ በቀጥታ እንዲሞላ የሚደረግ ነው።

መጠለያ አልባ ዜጎችስ?

እንደ ማረሚያ ቤት፣ ህፃናት ማሳደጊያዎች፣ የአረጋዊን መጦሪያዎችን፣ የወታደር ካምፖችንና የመሳሰሉትን ጭምር ያካተተ ነው። በቆጠራው ወቅት ከሚካተቱት ዋና መረጃዎች መካከልም የተቆጣሪው ግለሰብ ፆታ፣ ዕድሜ፣ ሃይማኖት፣ የብሔር/ ብሄረሰብ ሁኔታ የአካል ጉዳተኝነት ሁኔታ፣ የትምህርትና የሥራ ሁኔታና የመሳሰሉት ይገኙበታል። ቆጠራው ቤት ለቤት እየተዞረ የሚካሄድ በመሆኑ የተቆጣሪዎችን መኖሪያ ቤት መሰረት ያደረገ ይሆናል። ይሁንና ሁሉም ሰው በተለያዩ ምክንቶች መጠለያ ላይኖረው የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል። እዚህ ጋር ጎዳና ተዳዳሪዎችን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። እንደ ከሞሽኑ መረጃ ከሆነ ቆጠራው መጠለያ ባይኖራቸውም እነዚህንም ዜጎች ጭምር ያጠቃልላል። እነዚህ ሰዎች የሚቆጠሩት በመጀመሪያ ግለሰቦቹ የሚያድሩባቸውን ቦታዎች በመለየት ሲሆን በፖሊስና በቀበሌ ሰራተኞች ትብብር በአንድ በሚወሰን ቀንና ሰዓት መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ቆጠራው በማን ይጀመራል?

የህዝብና የቤት ቆጠራው በሚጀመርበት ዕለት ማለዳ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት፣የጠቅላይ ሚኒስትሩና የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ቤተሰቦች በመኖሪያ ቤታቸው የሚቆጠሩ ይሆናል። ይህም በርካታ ጋዜጠኞች በተገኙበት እንደዚሁም በቀጥታ የሚዲያ ሥርጭት የሚከናወን መሆኑን የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል።

በዕለቱም ከፍተኛ ባለስልጣናቱ ህብረተሰቡ ለቆጠራው ትብብር በማድረግ ተገቢውን መረጃ እንዲሰጥ መልዕከት የሚያስተላልፉበት አጋጣሚም ሆኖ እንዲያገለግል ይደረጋል ተብሏል። ይሄው ተመሳሳይ ተግባር በክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ቤት በመገኘትም ጭምር ይከናወናል ተብሏል።n

ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
388 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 65 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us