ኤርትራ 450 የንግድ ተቋማትን ዘጋች

Friday, 12 January 2018 16:45

 

-  የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ የከፋ ደረጃ ደርሷል

 የኤርትራ መንግስት 450 የሚሆኑ የግል የንግድ ተቋማትን ዘጋ። መንግስት እነዚህን እርምጃዎች የወሰደው የሀገሪቱን ፋይናንስ መመሪያ ባልተከተለ መልኩ ጥሬ ገንዘብን አከማችተዋል በሚል ነው።

 

 በኤርትራ በመሠረታዊነት ሁለት ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተከሰቱ መሆኑን ከሀገሪቱ የሚወጡት መረጃዎች እያመለከቱ ነው። የመጀመሪያው በሀገሪቱ እየተስፋፋ የመጣው የዋጋ ግሽበት ሲሆን ሁለተኛው ፈተና ሆኖ የሚታየው ደግሞ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ነው። መንግስት ችግሮቹን ለመፍታት የኢኮኖሚ ሳይንሱ የሚፈቅዳቸውን ገንዘብ ነክና (Monetary Policy) ገንዘብ ነክ ያልሆኑ (Physical Policy) እርምጃዎችን በማጣመር በጥናት አስደግፎ ከመውሰድ ይልቅ ዋነኛ ትኩረቱን ገንዘብ ነክ ባልሆኑ እርምጃዎች ላይ ማድረጉና በዜጎች ላይም ጥብቅ እርምጃን መውሰድ መጀመሩ ፈተናውን ያከበደው መሆኑን  ከዚያው ከኤርትራ ምድር የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

 

መንግስት የሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብ የሆነውን ናቅፋ የመግዛት አቅምን ማሽቆልቆል ለመከላከል የሄደበት መንገድ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን የገንዘብ ዝውውር መጠን መቆጣጠር ነው። ይህንንም ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ በመንግስት በኩል የተወሰደው እርምጃ ዜጎች ከባንክ በሚያወጡት ካሽ ላይ ገደብ በመጣል ቁጥጥር ማድረግ ነው። ይህ አሰራር በዋነኝነት ተግባራዊ የተደረገው በቢዝነስ ድርጅቶች ላይ መሆኑን ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ ከኤርትራ የወጡ ዘገባዎች ያመክታሉ።

 

የሀገሪቱ መንግስት ባወጣው የፋይናስ ቁጥጥር መመሪያ መሰረት ድርጅቶች ግብይት ሲያከናውኑ ክፍያ መፈፀም ያለባቸው በናቅፋ ገንዘብ ሳይሆን በቼክ ወይንም በባንክ ለባንክ የገንዘብ ዝውውር አማካኝነት ብቻ ነው። ክፍያ የሚፈፀምለት አካልም ቢሆን በመንግስት የፋይናንስ መመሪያ ከተቀመጠው ካሽ በላይ ከባንክ ማውጣት የሚችልበት እድል አይኖርምም።

 

 ድርጅቶች ከዚህም በተጨማሪ የየቀኑን የቢዝነስ እንቅስቃሴያቸውን የሚያሳይ ሂሳብ መያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህም የሂሳብ ማስረጃ ከተቀመጠለቸው የካሽ ጣሪያ በላይ ጥሬ ገንዘብ በካዝናቸው ውስጥ እንዳይኖር የሚደረገውን ቁጥጥር የበለጠ የሚያጠናክረው ይሆናል።

 

 ይህ የመንግስት ጥብቅ ቁጥጥር ግን በዋና ከተማዋ  አስመራ የሚገኙ ነጋዴዎችን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ የቢዝነስ ሰዎች ምቾትን የሚሰጥ ሆኖ አልተገኘም። ይህም በመሆኑ ነጋዴዎች በንግድ እንቅስቃሴያቸው ያገኙትን ገንዘብ በመመሪያው መሰረት ከተፈቀደላቸው የካሽ ጣሪያ በላይ ሲያልፍ በባንክ አካውንታቸው ከመክተት ይልቅ በየቤታቸው እየሸሸጉ ማስቀመጥን መርጠዋል። ይህ ሁኔታ በመላ ኤርትራ በተለይም በአስመራ ከተማ ትልልቅ ንግድ ቤቶች እየተስፋፋ መሄዱን ተከትሎ መንግስት በቅርቡ አስደንጋጭ እርምጃን ወስዷል።

 

 በዚህም መሰረት የመንግስትን መመሪያ በመጣስ ከተቀመጠላቸው ጣሪያ በላይ ጥሬ ገንዘብን አከማችተዋል በተባሉት ንግድ ቤቶች ላይ የእገዳና የማሸግ እርምጃ የተወሰደ መሆኑን የቮይስ ኦፍ አሜሪካ የድረገፅ ዘገባ ያመለክታል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም በተለይም በዋና ከተማዋ አስመራ ያሉ በርካታ ታላላቅ ሆቴሎች፣የሸቀጣሸቀጥ መደብሮች፣ ሬስቶራንቶችና ካፌዎች ሳይቀሩ እንዲታሸጉ የተደረገ መሆኑን ይሄው ዘገባ ያመለክታል።

 

በርካቶች የሚዝናኑባቸውና ጊዜያቸውን የሚያሳልፈባቸው ሆቴሎችና ካፌዎች ሳይቀሩ መታሸጋቸው አስመራና ምፅዋ ከተሞችን ጭር እንዲሉ ያደረጋቸው መሆኑን ከዚያው ከአስመራ የሚወጡ የፎቶግራፍ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

 

 ይህም የመንግስት የንግድ ተቋማትን በጅምላ የመዝጋት እርምጃ በቋፍ ላይ ያለውን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ የበለጠ እንዲኮታኮት ያደርገዋል የሚል ሥጋትን አሳድሯል።

የሀገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ድረገፅ መረጃ እንዳመለከተው ከሆነ 450  የሚሆኑ የንግድ ተቋማት እንዲዘጉ የተደረገ ሲሆን የከፋ ጥፋት ተገኝቶባቸዋል የተባሉ አንዳንድ የንግድ ተቋማት ደግሞ እስከ ስምንት ወራት የሚደርስ እገዳ የሚጣልባቸው መሆኑን ይሄው የሚኒስትር መስሪያቤቱ መረጃ ጨምሮ ያመለክታል። መንግስት በተለይ ሆቴሎችን ሳይቀር መዝጋቱ የቱሪዝም ዘርፉን እንቅስቃሴ ክፉኛ በመጉዳት ኢኮኖሚው የበለጠ እንዲኮታኮት ያደርገዋል የሚሉ ኢኮኖሚያዊ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው።

 

በአጠቃላይ መንግስት በአሁኑ ሰዓት እየወሰዳቸው ያሉት የኢኮኖሚ ሳይንስን ያልተከተሉ እርምጃዎች ሀገሪቱን ዋጋ እያስከፈላት ነው የሚሉ ኤርትራዊያን ምሁራን በርካቶች ናቸው።

ኳታርዋነኛየኤርትራየውጭምንዛሪምንጭእንደሆነችየሚነገርላትሀገርብትሆንምበቅርቡበሁለቱሀገራትመካከልየተነሳውየዲፕሎማሲግንኙነትመሻከርየኤርትራኢኮኖሚንየውጭምንዛሪገቢንአድርቆታል።ከዚህምበተጨማሪበኤርትራዊያንየሚላከውየውጭምንዛሪምቢሆንማሽቆልቆሉነውየሚነገረው።ከተፈጠረውየውጭምንዛሪእጥረትጋርበተያያዘተሸከርካሪዎችሳይቀሩነዳጅበኩፖንብቻመጠቀምየሚችሉበትአስገዳጅሁኔታምተፈጥሯል።ኤርትራያላትየኢኮኖሚእንቅስቃሴለዓለምአቀፉማህበረሰብግልፅስላልሆነከሀገሪቱየሚወጡመረጃዎችውስንነትየሚታይባቸውናቸው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
162 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 544 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us