በአፍሪካ የኤሌክትሪክ ልማት ላይ ትኩረቱን ያደረገ አውደ ርዕይ በአፍሪካ ህብረት ተከፈተ

Wednesday, 17 January 2018 12:03

 

በአፍሪካ ልማት ላይ ትኩረቱን ያደረገውና የ53 የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራትን የጥበብ ሰዎችን ስራ ያካተተው ኤግዚብሽን በአፍሪካ ህብረት ተከፈተ። የጥበብ ሥራ ኤግዚብሽኑ ባለፈው ሳምንት የተከፈተ ሲሆን እስከ የካቲት 2010 ዓ.ም ድረስ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይ መሆኑን አዘጋጆቹ  በአፍሪካ ህብረት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አመልክተዋል።

 

ይሄው በአፍሪካ የኤሌክትሪክ ኃይል ልማት ላይ ትኩረቱን ያደረገው አውደ ርዕይ “የአፍሪካ ብርሃን” የሚል ሥያሜ ተሰጥቶታል። በዚህ አውደ-ርዕይ ላይም የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የጥበብ ሰዎች የፎቶግራፍ ሥራዎች፣ ስዕሎችና ልዩ ልዩ ቅርፃ ቅርፆች ለዕይታ ቀርበዋል። አወደ ርዕዩ ልምድ ካላቸው አፍሪካዊና ጥበብ ሰዎች ሥራዎች በተጨማሪ አዳዲስ ወደ ዘርፉ ብቅ እያሉ ያሉ ወጣቶችንም ጭምር ያካተተ መሆኑን የአውደ ርዕዩ አዘጋጆች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። አርቲስቶቹና ሥራዎቻቸው የአፍሪካ አባል ሀገራት ከሆኑት 53ቱ ሀገራት የተውጣጡ ሲሆን ከዚህ ቀደም ይሄው ተመሳሳይ ሥራ በፓሪስ፣ በጄኒቫ፣ አቢጃን እና ዳካር የቀረበ መሆኑ ታውቋል።

 

 ኤሌክትሪክ ኃይል የእድገት ሞተር ሆኖ ሳለ ከአፍሪካ ህዝብ ውስጥ 20 በመቶ ብቻ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆኑን ያመለከቱት የኤግዚብሽኑ አዘጋጆች፤ይህንን የእድገት አቅም ለማልማት በሚደረገው ጥረት አፍሪካዊያን አርቲስቶች የራሳቸው የሆነ ሚና እና ድርሻ ሊኖራቸው የሚገባ መሆኑን አመልክተዋል። ያለበቂ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የአፍሪካን እድገት አስተማማኝ ማድረግ እንደማይቻል ያመለከቱት አርቲስቶቹና የአውደ ርዕዩ አዘጋጆች፤ በዚህ ዙሪያም መላ አፍሪካዊያን በተለይም በየደረጃው ውሳኔ ሰጪነት ደረጃ ያሉ አመራሮችን ግንዛቢ ማስጨበጥ የሚገባ መሆኑን አመልክተዋል።

 

 አፍሪካ ለኤሌክትሪክ ኃይል ልማት የሚሆን ከፍተኛ እምቅ አቅም ያላት አህጉር መሆኗ የተመለከተ ሲሆን ሀብቱን አልምቶ መጠቀሙ ላይ ግን ከፍተኛ ውስንነት የሚታይ መሆኑን በዕለቱ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተመልክቷል።

 

የጥበብ ሥራዎቻቸውን ከሚያቀርቡት አፍሪካዊያን መካከልም ኢትዮጵያዊያን አርቲስቶች የሚገኙበት መሆኑ ታውቋል። የፊልምና የፎቶግራፍ ባለሙያዋ ኢትዮጵያዊቷ አይዳ ሙሉነህ፣ የቅርፃ ቅርፅ ባለሙያውና ሰዓሊው ኤርትራዊው ኤርሚያስ እቁቤ እንደዚሁም ከጂቡቲ ማናን የሱፍ የተባለች ወጣት የፎቶግራፍ ባለሙያ በምስራቅ አፍሪካው ክፍለ አህጉር ሥራዎቻቸውን በኤግዚብሽኑ ላይ ካቀረቡት የጥበብ ሰዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።

 

የሁሉምአርቲስቶችዋነኛማጠንጠኛየአፍሪካየኤሌክትሪክኃይልልማትሲሆንኢትዮጵያይቷአይዳሙሉነህ “ጨለማለብርሃንስፍራውንሲለቅ (Darkness give away to light) የሚልርዕስየያዘንየፎቶግራፍናየእጅሥራቅብድብልቅያለውየጥበብሥራንበአውደርዕዩላይአቅርባለች።

Last modified on Wednesday, 17 January 2018 13:21
ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
79 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 799 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us