በዓለማችን የገቢና የሀብት ልዩነት እየሰፋ ነው

Wednesday, 24 January 2018 13:53

 

የዓለማችን የገቢና የሀብት ክፍፍል ልዩነት በከፍተኛ ደረጃ እየሰፋ መሄዱን ሰሞኑን ይፋ የሆነው የኦክስፋም የጥናት ሪፖርት ያመለክታል። እንደ ጥናቱ ሪፖርት ከሆነ ባለፈው የፈንጆች ዓመት ዓለማችን ካመነጨችው አጠቃላይ ሀብት ውስጥ 82 በመቶ የሚሆነው የገባው አንድ በመቶ ወደሚሆኑት የምድራችን ሀብታሞች ኪስ ውስጥ ነው።

 

 ይህ የኦክስፋም ሪፖርት ባለፉት አምስት ዓመታት ድርጅቱ ሲያወጣው ከነበረው ሪፖርት ጋር ተመሳሳይ መሆኑን የቢቢሲ ድረገፅ ዘገባ ያመለክታል። ለዚህ የገቢና የሀብት ልዩነት መስፋት ምክንያት አድርጎ ያስቀመጠው የዓለማችን ቱጃሮች መንግስታት ለእነሱ በሚመችና ድሆችን በሚጎዳ መልኩ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን እንዲቀረፅ ማድረጋቸውን ነው።

 

 ይህ ብቻ ሳይሆን በየሀገራቱ ያለው የታክስ ማጭበርበር አንዱ ለገቢ ልዩነት መስፋት ተደርጎ ተጠቅሷል። ታክስ በቀጥታ ለልማት ከሚያበረክተው ገቢ በተጨማሪ በዜጎች መካከል ፍትሃዊ የሃብት ስርጭት እንዲኖር የራሱን አስተዋፅኦ ያደርጋል። ሆኖም በድሃም ሆነ በሀብታም ሀገራት ካሉ ባለፀጎች መካከል በቁጥር ቀላል የማይባሉት የታክስ ስወራ ድርጊትን የሚፈፅሙ ከመሆናቸው ጋር በተያያዘ በርካታ ቢሊዮን ዶላር በመንግስታት የልማት ሥራዎች አማካኝነት ወደ ህብረተሰቡ የሚደርስበት ሁኔታ ከሚፈጠር ይልቅ በሀብታሞቹ ካዝና ውስጥ የሚቀር የመሆኑ ጉዳይ መንግስታትን የሚያስወቀስ ተግባር ሆኗል።

 

 ኦክስፋም ባካሄደው በዚሁ ዓለም አቀፍ ጥናት ዙሪያ የተለያዩ ሀገራት ዜጎችን ያናገረ ሲሆን  በአስር ሀገራት የሚገኙ 70 ሺህ ዜጎች በገቢና በሀብት ልዩነቱ መፍትሄ ዙሪያ ጥያቄ ያቀረበላቸው መሆኑን አመልክቷል። እንደሪፖርቱም ከሆነ 72 በመቶ የሚሆኑት የመጠይቁ አካላት የሰጡት ምላሽ የገቢና የሀብት ልዩነቱን ለማጥበብ መንግስታቶቻቸው በአፋጣኝ ጣልቃ እንዲገቡ ይፈልጋሉ።

ይህንን የኦክስፋም ጥናት በተመለከተ የማይቀበሉት ወገኖችም አሉ። በተለይ ቀደም ባሉት ዓመታት በብዙ መቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ በድህነት አዘቅት ውስጥ የነበሩ ዜጎቻቸውን ነፃ ያወጡት እንደ ቻይና፣ ህንድና ቬትናም ያሉ ሀገራትን  በመጥቀስ እነዚህን ሀገራት የአለማችን የገቢና የሀብት ልዩነት እሰፋ ከመሄድ ይልቅ እየጠበበ መሄዱ ማሳያ ናቸው የሚሉ ወገኖች አሉ። ቢቢሲ ባሰራጨው በዚሁ ዘገባ እንደጠቆመው “ኦክስፋም ጥናቱን ሲያካሂድ የወሰዳቸው የግብዓት መረጃዎች በመጨረሻ ወደ ተጋነነ ድምዳሜ እንዲደርስ አድርጎታል” በማለት የሰላ ትችታቸውን የሚሰነዝሩም ወገኖች አሉ። ይሄንን ትችት የኦክስፋም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ማርክ ጎልድሪንግ አይቀበሉትም።

 

እንደሳቸው አባባል ጥናቱን በወቅታዊ አሃዝ አስደግፎ ለማካሄድ በተሰራው ሥራም ብዙ የቁጥር ለውጦች ተካሂደዋል።  የኦክስፋም የመጨረሻ የጥናቱ ሪፖርት ይፋ መሆን በዳቮስ ከሚካሄደው የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ጋር የገጠመ ሲሆን ይህም ጉዳይ አንዱ የፎረሙ መነጋገሪያ አጀንዳ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑን ይሄው የቢቢሲ ዘገባ ጨምሮ ያመለክታል።

 

ጥናቶችእንደሚያመለክቱት፤በዓለማችንያለውየሃብትናየገቢልዩነትመስፋትለድህነትመስፋፋትብሎምለግጭቶችመበራከትአይነተኛምክንያትእየሆነነው።በዚህዙሪያበዓለማችንታላላቅኮንፍረንሶችናመድረኮችላይበርካታውይይቶችየተካሄዱበትሁኔታቢኖርምአንድምውጤትየተገኘበትሁኔታ   የለም።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
148 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 587 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us