ሙስናን ለመዋጋት አፍሪካ ከቻይና ትምህርት መውሰድ አለባት

Wednesday, 24 January 2018 13:57

 

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ጋር በተያያዘ በአፍሪካ ህብረት የህብረቱ አባል ሀገራት አምባሳደሮች ስብሰባ አስቀድሞ የተካሄደ ሲሆን የስብሰባው ዋነኛ አጀንዳም ሙስና ነበር። በሳለፍነው ሰኞ በተካሄደው በዚሁ ስብሰባ ላይ በአፍሪካ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ ከመጣው ሙስና ጋር በተያያዘ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

 

በመጪው የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት መሪዎች ላይ ዋነኛ የስብሰባው አጀንዳ ሙስና ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። በዚሁ ዙሪያ ንግግር ያደረጉት በአፍሪካ ህብረት የግብፁ አምባሳደር አቡበከር ሄንፊ ማሀሙድ አፍሪካ ሙስናን ለመዋጋት ከቻይና ብዙ መማር ያለባት መሆኑን ገልፀዋል። በዚህም ዙሪያ ቻይና እና አፍሪካ በጋራ መስራት የሚገባቸው መሆኑንም አምባሳደሩ ጨምረው አመልክተዋል።

 

በአፍሪካ ህብረት የኬኒያ አምባሳደር የሆኑት ካትሪንማውንጌ በበኩላቸው ሙስና የአፍሪካዊያንን እድገት ወደኋላ እየጎተተ መሆኑን ገልፀው በዚህ ሙስናን ለመዋጋት አፍሪካዊያን ከቻይና ብዙ ሊማሩ የሚገባ መሆኑን አመልክተዋል። ቻይና ሙስናን በመዋጋቱ ረገድ በሙስና በተዘፈቁ አመራሮች ላይ ከእድሜ ልክ እስራት እስከ ሞት ቅጣት የሚደርስ እርምጃን በመውሰድ የምትታወቅ ሀገር ናት።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
130 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1031 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us