የሱዳን መገበያያ ገንዘብ በማሽቆልቆል ላይ ነው

Wednesday, 31 January 2018 12:23

 

የሱዳን መገበያያ ገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ በማሽቆልቆል ላይ ነው። እንደ ሱዳን ትሪብዩን ዘገባ ከሆነ በአሁኑ ሰዓት በካርቱም ጥቁር ገበያ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ37 የሱዳን ፓውንድ በመመንዘር ላይ ነው። ሮይተርስ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ሀምሌ ወር ባሰራጨው ዘገባ በወቅቱ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ19 የሱዳን ፓውንድ ይመነዘር ነበር። የሱዳን ፓውንድ የምንዛሪ ዋጋ ቀስ በቀስ እያሽቆለቆለ መሄዱን ተከትሎ በሀገሪቱ የምርቶችና የአገልግሎት ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው።


ይህንንም የዋጋ መናር ተከትሎ በኢኮኖሚው ውስጥ ግሽበት እየተከሰተ መሆኑን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ሱዳን ትሪብዩን በዚሁ ዘገባው እንዳሰራጨው ከሆነ በአሁኑ ሰዓት የሱዳን ፓውንድ ዋጋ ከቀን ወደ ቀን በማሽቆልቆል ላይ በመሆኑ ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት አይታይም። መንግስት ይህንን የሱዳን ፓውንድ መውደቅ ለመከላከል ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ምንዛሪን በማዕከላዊ ባንኩ አማካኝነት ለንግድ ባንኮች ማሰራጨት ቢጠበቅበትም መንግስት በቂ የውጭ ምንዛሪ የሌለው በመሆኑ ይህንን የማድረግ እድሉ ጠባብ መሆኑን በዚሁ ዙሪያ የሚወጡት ዘገባዎች ያመለክታሉ።


የሀገሪቱ ነጋዴዎች የሱዳን ፓውንድ ዋጋ የበለጠ እየወደቀ ይሄዳል በሚል ግምት በጥቁር ገበያው ውስጥ የዶላር ግዢ እያከናወኑ ማከማቸት መጀመራቸው አንዱ የመንግስት ራስ ምታት ሆኗል። ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ ባለሀብቶች በውጭ ምንዛሪ ሀብታቸውን እየመነዘሩ በመካከለኛው ምስራቅ ባሉ አንዳንድ ባንኮች ገንዘባቸውን የማስቀመጣቸውም ጉዳይ ሌላኛው ለኢኮኖሚው አለመረጋጋት ምክንያት ተደርጎ በመጠቀስ ላይ ነው። የሱዳን መንግስት አሁን እየታየ ያለውን የመገበያያ የጥቁር ገበያ መስፋፋት ለመቆጣጠር በፀጥታ ኃይሉ አማካኝነት በተከታታይ እርምጃዎች ሲወስድ ቢቆይም ይህ ነው የሚባል መፍትሄን ግን ማምጣት ሳይችል ቀርቷል።


የሱዳን መንግስት የውጭ ምንዛሪ ገቢ በዋነኝነት የተንጠለጠለው በነዳጅ ኤክስፖርት ገቢ ላይ ሲሆን ይሁንና 80 በመቶውን የለማ የነዳጅ ሀብት የያዘችው ደቡብ ሱዳን ነፃቷን ካወጀች በኋላ የሱዳን የውጭ ምንዛሪ ገቢ በከፍተኛ ደረጃ አሽቆልቁሏል። መንግስት በዚህ በኩል ያጣውን ገቢ በሌሎች የኤክስፖርት ምርቶች ለመተካት በወሰዳቸው እርምጃዎች በወርቅ ምርቱ ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ላይ ነው። በዚህም ሀገሪቱ የወርቅ ምርቷን በመጨመር፣ በዘርፉ የሚታየውን የኮንትሮባንድ ንግድ በመቆጣጠርና በመሳሰሉት እርምጃዎች ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት እምርታዊ ለውጦችን አስመዝግባለች። ሆኖም የወርቅ ገቢው ያለውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመቅረፉ ረገድ ገና ብዙ ወደፊት ሊሰራበት የሚገባ መሆኑን ዘገባዎች ያመለክታሉ።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
101 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 834 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us