የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ጉዳይ በአፍሪካ ህብረት ተመከረበት

Wednesday, 31 January 2018 12:23

 

አፍሪካዊያንን ይበልጥ እርስ በእርሳቸው የተሳሰሩ ለማድረግ የጋራ የአየር በረራ፣ የጋራ ፓስፖርትና ከቪዛ ውጭ የሆነ ግንኙነት እንዲኖራቸው ለማድረግ በአፍሪካ ህብረት በኩል ሲሰራበት ቆይቷል። ይህ እቅድ የ2063 አጀንዳ ተቀርፆለት እየተሰራበት ይገኛል። አፍሪካ በድንበር የታጠረች፣ በመሰረተ ልማት ያልተሳሰረችና የሀገራቱም የእርስ በእርስ የንግድ ግንኙነትም እጅግ ደካማ ሲሆን በዚህ ዓመት በአዲስ አበባ በተካሄደው 30ኛው መደበኛ የህብረቱ አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ አንደኛው የውይይት አጀንዳ በአህጉሪቱ ነፃ የንግድ ቀጠና እንዲስፋፋ ማድረግ ነበር። ህብረቱ ለዚህ ለውጥ የተመቸ እንዲሆን ለማድረግ አንዳንድ ለውጦች ማድረግ የሚያስፈልገው መሆኑ ተመልክቷል።

 

በእርግጥ አህጉር አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና እንዲፈጠር በማድረጉ ረገድ በአህጉሪቱ አራት መሰረታዊ ጉዳዮች ሊሟሉ የሚገባ መሆኑን ይገልፃሉ። አንደኛው ሰላም ሲሆን ሌላኛው የሀገራት የእርስ በእርስ የመሰረተ ልማት ትስስር ነው። ከዚህ ውጭ ተመሳሳይ ምርትን ከማምረት መውጣትና የሀገራት የምርታማነት ደረጃ ማደግ ነው። ከምርት ተወዳዳሪነትና ከምርታማነት ጋር በተያያዘ ጋር በእቅዱ ተግባራዊነት ዙሪያ ከሚያቅማሙ ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት።

 

ሀገራቱ በየቀጠናቸው ባለው ነፃ የንግድ ቀጠና ግንኙነት ራሳቸውን ለሰፊው አፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና በማለማመድ ላይ ሲሆኑ በዚህ ረገድ ደካማ እንቅስቃሴ ያለው በምስራቅ ነው። የደቡብ አፍሪካ ሀገራት የተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። አፍሪካ በዚህ ረገድ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ትግበራ ላይ ኬኒያ በሀሳቡ ደስተኛ መሆኗን በፕሬዝዳንቷ በኩል ገልፃለች። እንደ ዤኑዋ ዘገባ ከሆነ አፍሪካዊያን ሀገራት ከሌላው የዓለም ክፍል ጋር ካላቸው የንግድ ግንኙነት አንፃር ሲታይ የእርስ በእርስ የንግድ ግንኙነታቸው 18 በመቶ ብቻ ነው። አፍሪካ በማደግ ላይ ካሉት ሀገራት ማለትም እንደ ጆርጂያ፣ አዘርባጃን እና ከመሳሰሉት ሀገራት የእርስ በእርስ የንግድ ግንኙነት አንፃር እንኳን ሲታይ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ መሆኑን ይሄው የሰሞኑ የዤኑዋ ዘገባ ጨምሮ ያመለክታል።

 

 በዚህ ረገድ አፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናን በማስፋፋት ኢኮኖሚዋን ለመገንባት በባቡር መስመር፣ በመንገድ ብሎም በአየር ትራንስፖርት ጭምር ይበልጥ ለመተሳሰር በሥራ ላይ ብትሆንም በ2063 ከተቀመጠው አጀንዳ አንፃር ግን ብዙ መስራት የሚጠበቅባት መሆኑን በርካቶች ይገልፃሉ።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
139 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 805 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us