ሀዋሳ አንድ ተጨማሪ ሆቴል አገኘች

Wednesday, 31 January 2018 12:33

 

ሀዋሳ ከተማ የበርካታ ሆቴሎች ባለቤት ስትሆን ከሰሞኑም አንድ ተጨማሪ ሆቴልን አስመርቃለች። ባለፈው ቅዳሜ ጥር 19 ቀን 2010 ዓ.ም የተመረቀው ሮሪ ሆቴል ከአራት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት መሆኑን የሆቴሉ ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ሲላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። ሆቴሉ አንድ መቶ የመኝታ ክፍሎች ያሉትና በባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ደረጃ የተገነባ መሆኑም ተመልክቷል። በምግብ አገልግሎት በኩል ከሚሰጣቸው በርካታ አገልግሎቶች መካከል የሀገር ውስጥ እንደዚሁም የአውሮፓና የእስያ ባህላዊ ምግቦች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው የሚያዘጋጁ መሆኑም ተመልክቷል።

 

ሆቴሉ በሃዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክ አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን ይህም ሁኔታ  በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ ላሉ የእስያና የሌሎች ሀገራት ዜጎች በቂ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል። በተለይ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ በርካታ የእስያ ሀገራት ዜጎች መኖራቸውን ታሳቢ በማድረግ ለዚያ አካባቢ ባህላዊ ምግብ ልዩ ትኩረት የተሰጠ መሆኑ ተመልክቷል።

 

 ሆቴሉ ከዚህም በተጨማሪ የህፃናትና የአዋቂዎች መዋኛ ገንዳዎችና  ጂምናዚየምን፣ የሴትና የወንድ የውበት ሳሎኖችን፣ ስቲም እና የህፃናት መጫወቻን ጭምር እንዲያካትት ተደርጓል። ሆቴሉ አንድ መቶ አልጋዎችንም አካቶ የያዘ ነው። 3 መቶ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን ሁሉም የሆቴሉ ሰራተኞች በዜሮ የሥራ ልምድ በቀጥታ ከአዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተወሰደውና ተጨማሪ የሥራ ላይ ሥልጠና ተሰጥቷቸው ሥራ እንዲጀምሩ የተደረጉ መሆኑን አቶ ሀብታሙ አመልክተዋል።

 

ሮሪ ሆቴል አለታላንድ በመባል የሚታወቅ ዘርፈ ብዙ የንግድ ተቋም እህት ኩባንያ መሆኑ ታውቋል። አለታላንድ ኩባንያ በአስመጪና ላኪነት በተለይም በቡና ምርትና መላክ ሥራ፣ በፕላስቲክ ምርት በሪዞርትና ሆቴሎች የተሰማራ ኩባንያ ነው።  አረንጓዴ ሻይንም ለማምረት በዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል።

 

እንደ አቶ ሀብታሙ ገለፃ ኩባንያው ከሀገር ውስጥ የኢንቨስትመንት ሥራው ባለፈ በውጭ ሀገራትም ጭምር የኢንቨስትመንት ህልውናው የማስፋፋት እቅድ አለው። ኩባንያው በአሁኑ ሰዓትም በአጠቃላይ ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ መሆኑ ታውቋል።

 

ይህንን የስራ እድልም የኢንቨስትመንት ዘርፎቹን በማስፋት ወደ 20 ሺህ ለማሳደግ እቅድ ተይዟል። ሆቴሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬና የአዋሳ ከተማ እንደዚሁም የተለያዩ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቦታው በመገኘት መርቀዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
661 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 796 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us