የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ለበርካታ ጥያቄዎች ጥቂት ምላሽ የሰጠበት መድረክ

Wednesday, 14 February 2018 11:27

 

የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ባሳለፍነው ዓርብ የካቲት 2 ቀን 2010 ዓ.ም ከደረቅ ጭነት ባለንብረቶችና ከህዝብ ክንፍ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል። ከውይይቱ ቀደም ብሎ የባለስልጣኑ የስድስት ወራት አፈፃፀምና ቀጣይ እቅድም ለተሰብሳቢዎች ቀርቧል። ሪፖርቱ ከመቅረቡ በፊት በጥሪና አጀንዳን ቀድሞ በማሳወቅ ዙሪያ ላይ በተሰብሳቢዎች በኩል ቅሬታ ቀርቧል። ባለስልጣን መስሪያቤቱ ቀድሞ ከባለድርሻ አካላት ጋር ባልመከረበት እቅድ ሪፖርት የማቅረቡ ትርጉም ምንድን ነው? የሚል ጥያቄን አስነስቷል። በተነሳው የአካሄድ ጥያቄም፤ “ቆጥራችሁ ሰጥታችሁን ቆጥራችሁ በማትረከቡን ሁኔታ ለምን የእናተን የአፈፃፀም ሪፖርት እንድንሰማ ይደረጋል።” በሚል በዘርፉ ባሉት ችግሮች ዙሪያ ብቻ ውይይቶች እንዲደረጉም ጥያቄዎች የቀረቡበት ሁኔታ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ አንዳንዶቹ ተወያዮች በስሚ ስሚ እንጂ ጥሪ ደርሷቸው በቦታው ያልተገኙ መሆናቸውን በመግለፅ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት በተሰብሳቢዎች በኩል ለዋና ዳይሬክተሩ ግልፅ መሆን የሚገባው ጥያቄ ተጠይቆ ሪፖርት የ6 ወር ግምገማ ከሆነ መጀመሪያ በተቀመጠው አሰራር መሰረት ከስራ ሂደት መሪው ጋር በየወሩ እየተገናኘ የተሰራና ያልተሰራውን ባልተገመገመበት ሁኔታ ከባለድርሻ አካሉ ዛሬ የስድስት ወር ሪፖርት ይዞ ቀርቦ አዳምጦ ከመውጣት ውጪ ሌላ ትርጉም እንደሌለው ለተሰብሳቢ ግልፅ ነው በማለት ሃሳብ ቀርቧል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ሪፖርቱ ለመንግስት ቀርቦ ከሆነ ወይም ገና የሚቀርብ ከሆነ በግልፅ መልስ እንዲሰጡበት ተጠይቀው ቀርበዋል አልቀረቡም ሳይሉ አልፈውታል፡፡


ነገር ግን ጥያቄ አቅራቢው ለመንግስት ከቀረበ እዚህ ጋር እኛ የምንወያይበት ምን ለመፍጠር ነው ባለድርሻው አሳትፈናል ከማለት ውጪ የሚያመጣው ለውጥ እንደሌለ በጥያቄው ቀርቧል፡፡ መንግስት አሁን ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት የህዝብ ብሶት ካለባቸው አራት ተቋማት አንዱ ትራንስፖርት ባለስልጣን በመሆኑ በአስቸኳይ በስድስት ወር ውስጥ ያሉትን ቅሬታ በመፍታት ውጤት እንዲያመጣ የሚያስችል ሰነድ በባለስልጣኑ የቀረበ ሲሆን ተሰብሳቢዎች የቀረቡትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ቀደም ባሉት ጊዜያት የተለዩ የሚታወቁ ሲሆን አሁን በዚህ መልኩ መቅረቡ አዲስ ችግር ተብሎ የሚወሰድ መሆን እንደሌለበትና ይልቁንም በቁርጠኝነት ችግሮችን ለመፍታት ተቋሙ ቁርጠኛ አለመሆኑና ሁል ጊዜ ችግሮች በማድበስበስ ለማለፍ መሞከር ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍል እና የባለድርሻ አካላት ከምንጊዜውም በላይ ሞጋች በመሆኑ መብታችንን ማስጠበቅ እንዳለብን የምናውቅ ዜጎች ነን በማለት ተቃውሞአቸውን ገልፀዋል፡፡ ሪፖርቱም የተቋሙ የራሱ ብቻ እንደሆነ ተወስዶ መታየት አለበት እንጂ የህዝብ ክንፍን ባካተተ መልኩ በጋራ የተሰራ ሪፖርት እንዳልሆነ መታወቅ አለበት ሲሉ ተሰብሳቢዎቹ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡


ይህ ብቻ ሳይሆን ሪፖርቱ ከቀረበ በኋላም በተለይ በአቀራረቡ በኩል ካለፈው ሪፖርት አንፃር ታይቶ ሊገመገም በሚችልበት ደረጃ ሪፖርቱ አልቀረበም የሚል ቅሬታም ቀርቦበታል። ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወክለው የመጡ ወኪልም የትራፊክ አደጋ ጉዳትን በተመለከተ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ለህዝብ ተወካዮች ያቀረበው ሪፖርት “አደጋው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንፃር ሲታይ የቀነሰ ነው” ቢልም በዕለቱ በመድረኩ ላይ የቀረበው ሪፖርት ግን አደጋው እየጨመረ መሄዱን የሚያሳይ መሆኑ ግራ ያጋባቸው መሆኑን ገልፀዋል።


የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ኃይለ ማርያም በአካሄድ ዙሪያ ለተነሳው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የጭነት ትራንስፖርቱ ዘርፍ ላይ የሚታዩ ችግሮችን በተመለከተ በቅርቡ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የሚደረግ መሆኑን በመግለፅ አልፈውታል። ለተሰብሳቢዎች በሙሉ ተገቢው ጥሪ አለመድረሱን በተመለከተም በቢሮው ጥሪ አስተላላፊ ሠራተኞች በኩል የተፈጠረ ስህተት መሆኑን በመግለፅ ተሰብሳቢውን ይቅርታ ጠይቀዋል።


ከዚያ በኋላም ሪፖርቱና እቅዱ ተሰምቶ በተወያዮች ሰፋ ያለ አስተያየት ተሰጥቶበታል። ሪፖርቱ ከተሽከርካሪ አደጋ ጋር በተያያዘ በሰውና በንብረት ከደረሰው የስድስት ወራት አደጋ ጀምሮ በትራንስፖርቱ ዘርፍ እየታዩ ያሉትን ችግሮች ዳሷል።


በዚህ ሪፖርት የኢትዮጵያ መንጃ ፈቃድ ያላቸውና ውጭ ሀገር የሚኖሩ ዜጎች የያዙት መንጃ ፈቃድ ጊዜ ያለፈበት ቢሆንም ውጪ በሚኖሩበት ወቅት ጊዜ ያላለፈበት የውጭ መንጃ ፈቃድ ካላቸው የኢትዮጵያ መንጃ ፈቃድን ያለምንም ቅድመ ሁኔታው እንዲታደስላቸው እየተደረገ መሆኑን ተመልክቷል።


በመላ ሀገሪቱ በ2010 ዓ.ም በስድስት ወራት ውስጥ በሰዎች ላይ የደረሰው የሞትና የአካል ጉዳት ከ2009 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት አንፃር ሲታይ መቀነስ ሲገባው እንዲያውም የጨመረ መሆኑን በሪፖርቱ ተመልክቷል። በ2009 ስድስት ወራት በተሽከርካሪ አደጋ 2 ሺ 46 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ የተመለከተ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2010 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ወደ 2 ሺህ 3 መቶ 15 ከፍ ማለቱን ሪፖርቱ ያመለክታል። በአጠቃላይ በሞት፣ በቀላልና በከባድ የአካል ጉዳት ባለፈው 2009 ዓ.ም ስድስት ወራት ውስጥ በ8 ሺህ 462 ዜጎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2010 ዓ.ም ወደ 10 ሺህ አሻቅቧል።


ሪፖርቱ ከቀረበ በኋላ ከተሰብሳቢዎች በተነሱ ሃሳቦች፤ “ሪፖርቶችና እቅዶች ሁልጊዜም ይቀርባሉ፤ ነገር ግን ወደ ተግባር ሲገባ ግን አፈፃፀሙ ደካማ ነው። የፌደራልና የክልል ትራንስፖርት አሰራር መቀናጀት አለመቻል በተሽከርካሪ ባለቤቶችና ሰራተኞች ላይ ችግር እየፈጠረ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሀገር አቋራጭ አውቶብሶች ከመለስተኛና ከአክስዮን ተሽከርካሪዎች በተለየ ሁኔታ በየክልሉ ባሉ መናኸሪያዎች እየተገፉ ነው። በኢንሹራንሶች በኩልም አሁን ካለው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ተሸከርካሪዎች ሊቃጠሉ ይችላሉ በሚል ስጋት ችግር እየተፈጠረ ነው።


አንድ ተሽከርካሪ ጂቡቲ ከገባ በኋላ ጎማ ቀይሮ ሀገር ውስጥ ሲገባ ድርጊቱ የሀገር ውስጥ ጎማ አስመጪዎችን ያከስራል በሚል ተሽከርካሪዎች አዲስ የገጠሙትን ጎማ እንዲፈቱ የሚደረግ ከመሆኑም ባሻገር ጎማዎቹም እንዲወረሱ ይደረጋል። ከምንዛሪ ለውጥ ጋር በተያያዘ የበርካታ አገልግሎቶችና ሸቀጦች ዋጋ እየናረ ቢሄድም የትራንስፖርት ተመን ግን ባለበት እንዲቀጥል ነው የተደረገው። ባቡሩ ጭነቱን ሰብስቦ እየወሰደ በመሆኑ ገበያውን እየተሻማን ነው” የሚሉና በርካታ ቅሬታዎችና አስተያየቶች ቀርበዋል።


ከጅቡቲ ጎማ ቀይረው ሀገር ውሰጥ የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ መፍትሄ በመስጠቱ በኩል በቀጣይ የሚታይ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል። ባቡሩን በተመለከተ አቶ ካሳሁን በሰጡት ምላሽ ባቡሩ በብድር የተገነባና ያለበትንም ዕዳ መክፈል ስለሚገባው አሁን ካለው በላይ በሰፊው ሊሰራ የሚገባው መሆኑን ገልፀዋል። ሆኖም ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ራሳቸውን ከባቡር ትራንስፖርት ጋር በምን መልኩ አጣጥመው መጓዝ እንደሚችሉ በገበያው ውስጥ ተወዳዳሪ ለመሆን ራስን በተገቢው መንገድ ማደራጀት የሚገባው መሆኑን ገልፀዋል። በመድረኩ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል። ሆኖም ስብሰባው የተጀመረው እጅግ አርፍዶ ስለነበር ለተነሱት በርካታ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ መስጠት አልታቸልም። በዚህ ዙሪያም በተሰብሳቢዎች በኩል ቅሬታ ተስምቷል። አቶ ካሳሁንም በቀጣይ ተመሳሳይ መድረክ የሚዘጋጅ መሆኑን ቃል ገብቷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
950 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 839 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us