ግብፅ በኤርትራ ምድር የግብርና ልማት ጀመረች

Wednesday, 21 February 2018 11:07

 

ግብፅ ከኤርትራ ጋር የጋራ ግብርና ልማት መጀመሯን ኢጂብት ቱዳይ ከሰሞኑ ባሰራጨው ዘገባ አመልክቷል። ይህ በኤርትራ የተጀመረው የግብፅ የግብርና ልማት ፕሮጀክት ሀገሪቱ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ለመስራት ካሰበቻቸው ሰባት የግብርና ልማት ዘርፎች መካከል አንዱ መሆኑን ይሄው ዘገባ ጨምሮ ያመለክታል።

 

ፕሮጀክቱ ግብፅ በግብርናው ዘርፍ ያላትን የቴክኖሎጂ ልምድ ለኤርትራ የምታካፍልበት የልማት ፕሮግራም መሆኑን ኢጂብት ቱደይ ገልጿል። ግብፅ ይህንን መሰል የግብርና ልማት ፕሮጀክት በኤርትራ ከመጀመሯ ቀደም ብሎ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ በማሊ፣ በታንዛኒያ፣ በዛምቢያ እንደዚሁም በኒጀርና በኮንጎ የጀመረች መሆኗን ዘገባው ያመለክታል። የሀገራቱን የግብርና ልማት በቀጥታ ከመደገፍ ባሻገር ግብፅ በምላሹ ምን ቀጥተኛ ትርፍ ታገኛለች? የሚለው ጉዳይ ግን ግልፅ አይደለም።

    

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
77 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us