ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞቹ 64 ነጥብ 4 ሚሊዮን መድረሳቸውን ገለፀ

Wednesday, 21 February 2018 11:11

 

ኢትዮቴሌኮም የደንበኞቹ ቁጥር 64 ነጥብ 4 ሚሊዮን የደረሰ መሆኑን ኩባንያው ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ አስታውቋል። ይህም የደንበኞች ቁጥር ካለፈው 2009 ዓ.ም አንፃር ሲታይ የ7 ነጥብ 5 በመቶ እድገት ያሳየ መሆኑንም መግለጫው ጨምሮ ያመለክታል። የሞባይል ስልክ ደንበኞቹ ቁጥርም 62 ነጥብ 6 ደርሷል ተብሏል። ይህም ከእቅዱ አንፃር 99 ነጥብ 9 በመቶ መሆኑን መግለጫው ጨምሮ ያመለክታል።

 

የኢንተርኔት ዳታ ተጠቃሚዎች ቁጥርም 16 ነጥብ 05 ሚሊዮን የደረሰ መሆኑን ይሄው መግለጫ ጨምሮ ያመለክታል። ከገቢ አንፃርም ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 19 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለማስገባት አቅዶ 18 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱ ታውቋል። ከተገኘው ገቢ ውስጥም ከሞባይል አገልግሎት የተገኘው ገቢ ከጠቅላላው 73 ነጥብ 1 በመቶውን የሚሸፍን መሆኑን መረጃው ያመለክታል። ኩባንያው ባለፉት ጊዜያት አዳዲስ ደንበኞችን ማስገባት የሚያስችሉ አገልግሎቶችን በማስተካከል የዳታ ሮሚግ ታሪፍን ሳይቀር ያሻሻለ መሆኑን ይገልፃል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
949 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us