ቻይና የዓለማችን ትልቋ ሸማች ሀገር ለመሆን እየተንደረደረች ነው

Wednesday, 28 February 2018 12:14

 

ቻይና ለበርካታ ዓመታት በኤክስፖርት መር ኢኮኖሚ የምትታወቅ ሀገር ስትሆን ከዓምስት ዓመታት በኋላ ግን የዓለማችን ታላቋ ሸማች ሀገር እንደምትሆን የቻይና የዜና ወኪል ዤኑዋ ባሰራጨው ዘገባ አመልክቷል። እስከ አሁን ባለው ሂደት የዓለማችን ታላቋ ሸማች ሀገር አሜሪካ መሆኗን ይሄው ዘገባ ያመለክታል።


ባለፉት አስር ዓመታት የሀገሪቱ የገቢ ምርት ከጊዜ ወደ ጊዜ በየዓመቱ በ 6 በመቶ እየጨመረ የመጣ መሆኑን ያመለከተው ይሄው ዘገባ ይህም የኢምፖርት እድገት ሲታይ ከአሜሪካ እየበለጠ መሄዱን አመላካች ነው ተብሏል። ቻይና እስከዛሬ የምትታወቀው በዓለማችን ከፍተኛ ላኪ ሀገርነት ሲሆን አሁን ባለው ሂደት በቀጣይ የሸማችነቱን ደረጃ ከአሜሪካ የምትረከብ ከሆነ ሀገሪቱ በኢምፖርትም ሆነ በኤክስፖርት የአንደኝነት ደረጃን የምትይዝ ይሆናል። ቻይና የኢምፖርት ፍጆታዋ እያደገ እንዲሄድ ያደረገው የዜጎቿ የመግዛት አቅም በየጊዜው በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ መሆኑን ዘገባው ጨምሮ ያመለክታል።


ቻይና እ.ኤ.አ ከ2009 ጀምሮ የዓለማችን ከፍተኛዋ ኤክስፖርተር ሀገር ስትሆን እ.ኤ.አ የቻይና አጠቃላይ የኤክስፖርት መጠን አንድ ነጥብ ዘጠኝ ትሪሊዮን ዶላር የደረሰ መሆኑን የተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ቻይና ከፍተኛ አምራች ሀገርም ስትሆን ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ የታየው የዜጎች የመግዛት አቅም ማደግ ደግሞ ሀገሪቱ ከመሸጥ ባለፈ ከፍተኛ ሸማችም ሀገር እንድትሆን እያደረጋት ነው፡፡
ይህም የቻይናን አለም አቀፍ የኢኮኖሚ ትስስርና ተፅዕኖ ፈጣሪነትም በዚያው መጠን የሚያሳድገው መሆኑን የቻይና ደይሊ ዘገባ ያመለክታል፡፡ ይህም ቀደም ብሎ በራሳቸው በቻይናዊያን የተያዘ የኢኮኖሚ እቅድ ሲሆን ከጥቂት ዓመታት በኋላም ሙሉ በሙሉ ስኬትን ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
2321 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 714 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us