የዳሸን ባንክ የሀዋላ ሽልማት የዓረብ ሀገር የቤት ሠራተኛዋን ለሀገሯ አበቃ

Wednesday, 21 March 2018 12:26

 

ዳሸን ባንክ የዓለም አቀፍ ሀዋላ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ለማበረታታት ከነሃሴ 29 ቀን 2009 ዓ.ም እስከ ጥር 16 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ሲያካሂድ ለነበረው እጣ ባለፈው ሐሙስ መጋቢት 6 ቀን 2010 ዓ.ም ለአሸናፊዎች ሽልማትን አስረክቧል። ባንኩ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ መልኩ ከሸለማቸው ተሸላሚዎች በተለየ ሁኔታ አንድ ለየት ያለ ባለእድል አጋጥሞታል።

 

አዳነች ጡሜባ ትባላለች። በደቡብ ክልል የሆሳዕና ነዋሪ ናት። እሷና ባለቤቷ ኑሯቸውን የሚገፉት በባለቤቷ የሽመና ገቢ ነበር። ሆኖም ገቢው ወጪን ለመሸፈን በቂ ሆኖ አልተገኘም። ኑሮውም እየከበደ ይሄዳል። በዚህ መሃል ኑሮን ለማሸነፍ የተለያዩ አማራጮችን ማፈላለግ ግድ ሆነ። በጊዜው የተገኘው አማራጭ ወደ ዓረብ ሀገር መሄድ ነበር። በዚህ ጉዳይም ቀድማ ቤይሩት ከሄደችው እህቷ ጋር በስልክ መነጋገር ይጀምራሉ።

 

አዳነች ወደ ቤይሩት በመሄድ በሰው ቤት በሰራተኝነት ተቀጥራ መስራት እንደሚገባት መግባባት ላይ ከተደረሰ በኋላ፤ ሌላኛው ፈተና የነበረው የትኬትና አንዳንድ ለጉዞ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ማሟላት ነበር። ለዚህ ደግሞ ገንዘብ ያስፈልጋል። ቀድሞ ቤይሩት በሰው ቤት ሰራተኝነት ያለችው እህቷም ይህንን ወጪ የሚሸፍን ገንዘብን ለአዳነች ለመላክ ቃል ትገባለች። እሷም በገባችው ቃል መሰረት ለአዳነች ከአስር ሺህ ብር ጋር የተመጣጠነ ገንዘብን በውጭ ምንዛሪ ትልክላታለች። አዳነችም ገንዘቡን በዳሸን ባንክ በኩል ትቀበላለች። ብዙም ሳትቆይ ጉዞዋን ወደ ቤይሩት አድርጋ በቤት ሰራተኝነት ትቀጠራለች።

 

በዚያም ሁለት ያህል ወራትን ካስቆጠረች በኋላ አንድ ቀን ባለቤቷ ስልክ ይደውልላትና የዳሸን ባንክ የሀዋላ ሽልማት መኪና የደረሳት መሆኑን ያበስራታል። እሷ ግን የባለቤቷን ብስራት አላመነችም። በስተመጨረሻ በብዙ ማግባባት ካመነች በኋላ የቅጥር ኮንትራቷን አቋርጣ ኢትዮጵያ ገባች። ሁኔታውን ስታጣራም በትክከል እውን መሆኑን ተረዳች። ዳሸን ባንክም በእጣው መሰረት ባለፈው ሐሙስ መጋቢት 6 ቀን 2010 ዓ.ም በጌትፋም ሆቴል በተካሄደ ሥነ ሥርዓት አዳነችን ጨምሮ ሁሉም ባለዕድለኞች ሽልማታቸውን አስረክቧል።

 

Last modified on Wednesday, 21 March 2018 13:22
ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
1254 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 684 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us