ሱዳን እና ኳታር አወዛጋቢዋን ሱአኪን የወደብ ከተማ በጋራ ለማልማት ተስማሙ

Wednesday, 28 March 2018 12:14

 

ሱዳን እና ኳታር አወዛጋቢዋን ሱአኪን የወደብ ከተማ ለማልማት የአራት ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ተፈራረሙ። ይህች የቀድሞዋ የኦቶማን ቱርክ የወደብ ከተማ የነበረችው ግዛት ቱርክ ለጦር ሰፈር ልትጠቀምባት አስባለች በሚል በቅርቡ በግብፅና በሱዳን መካከል ፖለቲካዊ ውጥረት የተፈጠረበት ሁኔታ ነበር።


በዚሁ በሁለቱ ሀገራት ሥምምነት መሰረት በመጀመሪያው ዙር የአምስት መቶ ሚሊዮን ዶላር የልማትና የኢንቨስትመንት ሥራ የሚከናወን መሆኑን የሱዳን ትሪብዩን ዘገባ ያመለክታል። የወደብ ከተማ የ4 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክትም እ.ኤ.አ በ2020 ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑን ዘገባው ጨምሮ ያመለክታል።


በዚሁ ስምምነት መሰረት ሱዳን የሚኖራት ድርሻ 51 በመቶ ሲሆን ቀሪው 49 በመቶ ደግሞ የኳታር ድርሻ ይሆናል። ይህች የወደብ ከተማ በታቀደላት መሰረት ከለማች የሱዳን ትልቁ ወደብ ከሆነው ፖርት ሱዳን ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የምትቀመጥ ወደብ ትሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሪሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ባለፈው ታህሳስ ወር በሱዳን በነበራቸው ይፋዊ ጉብኝት በሰጡት መመሪያ መሰረት ይህችን ጥንታዊት ከተማ ታሪካዊነቷን በጠበቀ መልኩ ቅርሶቿ እንዲታደሱ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል።


ይህንንም ኃላፊነት አንድ የቱርክ ኩባንያ ወስዶ ሥራውን በአግባቡ እያከናወነ መሆኑ ታውቋል። ሱአኪን በተደረሰው ስምምነት መሰረት ሙሉ የልማት ስራው የሚከናወንባት ከሆነ ከወደብ ከተማነቷ ባሻገር የቱሪስት መስህብም ጭምር እንድትሆን ያደርጋታል ተብሏል። ኦቶማን ቱርኮች በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በነበራቸው ኃያልነት ይህችን የወደብ ከተማ በቀይ ባህር አካባቢ ላለው የንግድ እንቅስቃሴ እንደዚሁም በአካባቢው ይንቀሳቀሱ የነበሩትን የባህር ላይ ወንበዴዎች ለመቆጣጠር ይጠቀሙባት እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያመለክታሉ።


አንዳንዶች ኳታርና ቱርክ ይህችን ስትራቴጂክ የወደብ ከተማ ለማልማት እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ ከኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ባለፈ ፖለቲካዊ አንድምታም ጭምር እንዳለው እየገለፁ ነው።


በኳታር እና በጎረቤቶቿ አረብ ሀገራት መካከል እንደዚሁም በቱርክና በሳዑዲ አጋሮች መካከል የተፈጠረውን የሀይል አሰላለፍ ተከትሎ ቱርክ የሱአኪንን ወደብ ለጦር ሰፈርነት ልትጠቀምበት ትችላለች የሚል ሰጋት ያላቸው ግብፅና ሳዑዲ አረቢያ በጊዜው ተቃውሟቸው በከረረ መልኩ ሲገልፁ ነበር። ቱርክ ከሳዑዲና ከግብፅ ጋር ካላት የከረረ ፖለቲካ ውጥረት ጋር በተያያዘ ወደቧን ለጦር ሰፈርነት የምትጠቀም ከሆነ ሳዑዲም ሆነ ግብፅን በቀላሉ በቅርብ ርቀት ለመቆጣጠር የሚያስችላት ይሆናል። እስከአሁን ባለው ሁኔታ ግን የሱአኪን ወደብን በተመለከተ ቱርክ፣ ኳታርም ሆነች ሱዳን ጉዳዩን ከኢኮኖሚ አንፃር እንጂ ከፖለቲካና ከወታደራዊ ግንኙነት አንፃር እንዲታይ ፍላጎት ያሳዩበት ሁኔታ የለም።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
830 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 721 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us