ኢትዮጵያ የ1 ነጥብ 66 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ያስፈልጋታል

Wednesday, 11 April 2018 14:05

 

ኢትዮጵያ የ1 ነጥብ 66 ቢሊዮን ዶላር የዕርዳታ ጥያቄ አቀረበች፡፡ የዩኒሴፍ ኢትዮጵያ አጠቃላይ የሰብአዊ እርዳታ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከሆነ ይህ የዕርዳታ ገንዘብ የሚያስፈለገው 7 ነጥብ 9 የሚሆኑ ዜጎችን በምግብ አቅርቦት ለመደገፍ ነው፡፡ ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው ከሆነ የእርዳታ እገዛ ከሚያስፈልጋቸው ዜጎች መካከል በተለያዩ ግጭቶች የተፈናቀሉ ይገኙበታል፡፡


በሞያሌ በተፈጠረው ግድያ አስር ሺ የሚሆኑ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ወደ ኬኒያ የተሰደዱ ሲሆን የኬኒያ ቀይ መስቀልም እርዳታ እያቀረበላቸው መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የኢትዮጵያን መንግስት ዋቢ ያደረገው ይሄው መረጃ ወደ ኬኒያ የተሰደዱት ዜጎች በመመለስ ላይ ናቸው፡፡ ሆኖም እነዚህን ዜጎች ለማቋቋም እገዛን ይጠይቃል ተብሏል፡፡


የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን የዕርዳታ ጥሪ ያቀረበው ለግብርና ሥራ፣ ለከብት እርባታ፣ ለትምህርት፣ ለአስቸኳይ መጠለያዎች ግንባታ፣ ለጤና አገልግሎት የሚውል መሆኑ ታውቋል፡፡ እድርዳታና እገዛ ከሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መካልም ግማሽ ያህሉ ህፃናት መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት የህፃናት ፈንድ መረጃ ያመለክታል፡፡


እገዛ የሚያስፈልጋቸው በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ከተነሱት ግጭቶች ጋር ለተፈናቀሉ ወገኖች ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱ ከጎረቤቶቿ ለተቀበለቻቸው ስደተኞችም ጭምር መሆኑ ታውቋል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ከተለያዩ የጎረቤት ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ገብተው የተጠለሉ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ስደተኞች መኖራቸውንና ስደተኞቹም በዋነኝነት ከደቡብ ሱዳን እና ከኤርትራ የሚገቡ መሆናቸውን የሪሊፍ ድረ ገጽ መረጃ ያመለክታል፡፡

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
86 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 138 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us