ባህርዳር የጫት የሸማቾችን አቅም ለማዳከም ቀረጥ ጣለች

Wednesday, 25 April 2018 12:14

 

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከዛሬ ሚያዚያ 17 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ልዩ ቀረጥን በጫት ላይ ተግባራዊ የሚያደርግ መሆኑን አመልክቷል። የከተማ አስተዳደሩ የኮሙኒኬሽን ቢሮ የከተማውን አስተዳደር ገቢዎች ፅህፈት ቤት ጠቅሶ እንዳመለከተው ከሆነ ቀረጡን ለመጣል የተወሰነው በሁለት መልኩ ነው። አንደኛው በጫት ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የሸማቾችን አቅም ማዳከም ሲሆን በሌላ መልኩ ደግሞ በዚሁ ተጨማሪ ታክስ ከሚገኘው ገቢ የከተማዋን ልማት መደገፍ ነው። የከተማው አስተዳደር ገቢዎች ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘውዱ ክፍሌ እንደገለፁት፤ በቀን ከተለያዩ አካባቢዎች ከ5 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የጫት ምርት ወደ ባህርዳር ከተማ ይገባል። በተወሰነው ውሳኔ መሰረትም ለባህርዳር አካባቢ በአንድ ኪሎ ግራም ጫት ላይ 5 ብር ቀረጥ የተጣለ ሲሆን ከባህርዳር ውጪ በሚጫኑን የጫት ምርት ላይ በኪሎ ግራም 30 ብር ታክስ የተጣለ መሆኑ ተመልክቷል።

 

ባህርዳር ከተማ ጫት በተለይ በወጣቱ ክፍል በከፍተኛ ደረጃ ከሚቃምባቸው የሀገሪቱ ከተሞች አንዷ ስትሆን፤ በቅርቡ የከተማው አስተዳደር ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ጫት ከቤት ውጪ በአደባባይና በመንገዶች ላይ እንዳይቃም ማገዱ ይታወሳል። ከዚህም በተጨማሪ ጫት በክልሉ እያደረሰ ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስን በተመለከተም በተለያዩ ጊዜያት ጥናቶች ሲደረጉ ቆይተዋል።

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
180 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 618 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us