የግብርናው ዘርፍ ኤግዚብሽን

Wednesday, 25 April 2018 12:19

 

የኢትዮጵያ የግብርና፣ ምግብና መጠጥ ማቀነባባር እና ተያያዥ የሆኑ የፕላስቲክ ህትመትና ማሸግ ዘርፍ የንግድ ትርዒት ከመጪው ሚያዚያ 25 እስከ 27 ዓ.ም 2010 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑን አዘጋጆቹ በትላንትናው እለት በጎልደንቱሊፕ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አመልክተዋል። ዝግጅቱ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን፣ በፈረንሳዩ የምግብ ማቀነባበሪያ ቴክኖሎጂዎች ዓለም አቀፍ ትብብር (adepta)፣ በጀርመኑ ዓለም አቀፍ ትብብር (giz)፣ በጀርመን ኢኒጂነሪግ ፌደሬሽን (VDMA) እና በጣሊያኑ የንግድ ኤጀንሲ (ITA) አጋዥነት የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል።

 

በኢትዮጵያ በኩልም ኤግዚቭሽኑ የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር፣ የምግብ መጠጥና የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እንደዚሁም የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ማቴሪያልስ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ድጋፍና ያገኘና እውቅናም ጭምር የተሰጠው መሆኑ ታውቋል። በኤግዚብሽኑ ላይ ከሚቀርቡት ምርቶች መካከልም ከግብርና ሥራ ጋር የተያያዙ ማሽነሪዎች፣ የእንስሳት መመገቢያ መሳሪያዎች፣ የተለያዩ የምርት ማሸጊያ መሳሪያዎችና ልዩ ልዩ የግብርና ምርቶች ይገኙበታል ተብሏል።

 

በንግድ ትርዒቱ ላይ ከ17 ሀገራት የተውጣጡ ኩባንያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ። ከተሳታፊ ሀገራት መካከልም ቻይና፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ጣሊያን፣ ኳታር፣ ስፔን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቱኒዝያና፣ ታይዋን ይገኙበታል።

 

ባለፈው ዓመት ከ14 ሀገራት የተውጣጡ 60 የኤግዚብሽን አቅራቢዎች የነበሩ መሆኑ ታውቋል። ከዚህም ውስጥ 94 በመቶው የሚሆኑት ተሳታፊዎች በመጨረሻ በነበረው መጠይቅ በጎብኚዎች ተሳትፎ የረኩ መሆናቸውን እንደገለፁ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተመልክቷል። ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ኤግዚብሽን አንፃር ሲታይ የዚህ ዓመት የሀገር ውስጥ ተሳታፊዎች ቁጥር ቀንሶ የታየ መሆኑን የሀገር ውስጥ የኤግዚሽኑ ተባባሪ አዘጋጅ ፕራና ኢቬንትስ ማኔጂግ ዳይሬክተር አቶ ነቢዩ ለማ ገልፀዋል። እንደሳቸው ገለፃ ባለፈው ዓመት የሀገር ውስጥ ተሳታፊ ኩባንያዎች ቁጥር 18 የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥር በዚህ ዓመት ወደ 7 አሽቆልቁሏል። ለዚህም ምክንያቱ በሀገሪቱ ካለው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ጋር በተያያዘ ተሳታፊዎች ለኤግዚብሽኑ የሚሆኑ እቃዎችን ሀገር ውስጥ ማስገባት ባለመቻላቸው መሆኑ ተመልክቷል።

 

ኤግዚብሽኑ ከግብርና ምርቶች፣ ግብዓቶችና የዘርፉ ማሽነሪዎች በተጨማሪ የፕላስቲክ ህትመትና ማሸጊያዎችም ጭምር የሚቀርብበት ሲሆን ባለፉት አስርት ዓመታትም የኢትዮጵያዊያን የነፍስ ወከፍ የፕላስቲክ ተጠቃሚነት በየዓመቱ በ15 በመቶ እያደገ መምጣቱ ተመልክቷል።

 

ኢትዮጵያ በምስራቅና መካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ ሁለተኛዋ በመጀመሪያ ደረጃ ያለ የፕላስቲክ ምርት አስገቢ ሀገር ናት። በኢትዮጵያ ኤግዚብሽኑን ለማዘጋጀት የሚያስችሉ በርካታ ምክንያቶች በመኖራቸው ሀገሪቱን ከሌሎች መሰል ሀገራት ተመራጭ ያደረጋት መሆኑ ተመልክቷል።

 

ለዚህም ከተጠቀሱት ምክንያቶች መካከል የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በዓመት ከ7 ነጥብ 5 እስከ 10 በመቶ የሚሆን እድገትን የሚያስመዘግብ መሆኑ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የያዘች መሆኗ፣ የህዝቡ የግብዓት ምርቶችን ተጠቃሚነት ከፍተኛ መሆኑ ይገኙበታል። አቶ ነብዩ ኤግዚብሽኑ ለቴክኖሎጂና እውቀት ሽግግር፣ ለኢንቨስትመንት መስህብነትና ለንግድ ትስስር ጭምር የሚያገለግል መድረክ መሆኑን አመልክተዋል። በኢትዮጵያ በፈረንሳይ ኢምባሲ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ ሚስተር ፒሪ ሴንትኔክ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ሰፊ ገበያ ያላት ሀገር መሆኗን በመግለፅ ተሳታፊዎችም በብዙ መልኩ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልፀዋል።

 

በኢትዮጵያ የጀርመን ኢምባሲ የኢኮኖሚና የባህል ጉዳዮች ዋና ፀሐፊ ሚስተር ስቴፈን ዌንዲት በበኩላቸው ጀርመናዊያን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያለውን የገበያ እድል በሚገባ ፈትሸው እንዲጠቀሙበት ኢምባሲው የሚያበረታታ መሆኑን አመልክተዋል።

 

“ከገበሬው ማሳ እስከ ኢንዱስትሪው ከዚያም እስከ ኤክስፖርት ድረስ ባለው ሂደት የምርት ማሽጊያዎች ወሳኝነት አላቸው” ያሉት የኬሚካናል ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ደይሳ ሌታ በበኩላቸው፤በዚህ በኩል የማሸጊያ ግብዓቶች ዋጋ ከምርቱ ዋጋ በላይ እየናረ የሚሄድበት ሁኔታ መኖሩንም አመልክተዋል። የምግብ፣ መጠጥና ፋርማሲዮቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በቀለ መኩሪያ በኢትዮጵያ የአግሮ ኢንዱስትሪው ዘርፍ ገና በእድገት ላይ መሆኑን አመልክተው፤ በአሁኑ ሰዓትም መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት 17 የግብርና የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን የሚያቀነባብሩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መኖራቸውን አመልክተዋል። አቶ ደያሳ በበኩላቸው ሀገሪቱ 21 የወረቀት ፋብሪካዎች ያሏት መሆኑን ገልፀው፤ እነዚህም ፋብሪካዎች በአጠቃላይ ዓመታዊ የወረቀት የምርት መጠናቸው ወደ 90ሺህ ቶን መሆኑን አመልክተዋል። ሆኖም ይህ የምርት መጠን ከሀገሪቱ ፍላጎት አንፃር ሲታይ እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑን ኃላፊው ጨምረው አመልክተዋል። በመሆኑም በዚህ ዘርፍ የውጭ ባለሀብችም ጭምር መሳተፍ ያለባቸው መሆኑን ኃላፊው አሳሰበዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
564 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 758 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us