ኬኒያና ኢትየጵያ ግዙፍ የትስስር ፕሮጀክቶቻቸውን እውን ማድረግ አልቻሉም

Wednesday, 09 May 2018 13:08

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ከሰሞኑ በኬኒያ ይፋዊ ጉብኝት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኬኒያ በነበራቸው ቆይታ ከኬኒያው ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬኒያታ ጋር በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት ማድረጋቸውን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚሁ  የኬኒያ ጉብኝታቸው ዋነኛ አጀንዳዎች መካከል ተጠቃሹ ሁለቱን ሀገራት የሚያስተሳሰሩት መሰረተ ልማት ጉዳዮች ነው።

 

ኢትዮጵያና ኬኒያን በመንገድ፣ በወደብ ልማት፣ በባቡር እንደዚሁም በኤሌክትሪክ ኃይል ለማገናኘት የተጀመሩ ሥራዎች ነበሩ። ሆኖም እስከዛሬም ድረስ አንዱም ፕሮጀክት እውን ሆኖ ወደ ተግባር የገባበት ሁኔታ የለም።  ከኤሌክትሪክ ኃይል ጀምሮ አዲስ አበባን እስከ ናይሮቢ የሚያገናኘው የባቡር መስመር ዝርጋታ ድረስ የተፈረሙ የሁለትዮሽ ሥምምነቶች ቢኖሩም በተግባር የተመዘገበ ውጤት ግን የለም።

 

ኬኒያ በወደብ አልባ ሀገራት የተከበበች ሀገር ናት። ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳንና ኡጋንዳ ኬኒያን የሚያዋስኑ ነገር ግን ወደብ አልባ የሆኑ ሀገራት ናቸው። ይህ ለኬኒያ እንደ መልካም የኢኮኖሚ ትስስር አጋጣሚ ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው። ይህንንም ተከትሎ ኬኒያን የአካባቢው የኢኮኖሚ ማዕከል (Economic Hub) ባደረገ መልኩ የልማት ሥራን ለማከናወን የላሙ ወደብ ፕሮጀክት ይፋ የተደረገበት ሁኔታ ነበር።

 

የኬኒያ ዋነኛ የትራንስፖርት ኮሪደር ሆኖ እያገለገለ ያለው ከሞምባሳ ኡጋንዳ ያለው ዋነኛ መስመር ነው።

ከዚያ በመቀጠል የኬኒያውን ወደብ አልምቶ ለደቡብ ሱዳንና ለኢትዮጵያ ምቹ ለማድረግ የተጀመሩ አንዳንድ ስራዎች ነበሩ። አዲስ ግዙፍ ወደብን፣ መንገድን፣የባቡር መስመርንና ሌሎች በርካታ መሰረተ ልማቶችን ያካተተ በመሆኑ በሊዮን ዶላሮችን የሚጠይቅ ነው። ፕሮጀክቱ ሲጠነሰስ 16 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን አሁን ባለው የግብዓቶች ዋጋና ቴክኖሎጂ የገንዘቡ መጠን ወደ 22 ቢሊዮን ዶላር ተስፈንጥሯል።

 

ይህ ፕሮጀክት በአንድ መልኩ በሞባሳ ወደብ ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ በሌላ መልኩ ደግሞ በአካባቢው ያሉ ወደብ አልባ ሀገራትንም አማራጭ የወደብ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ አካባቢያዊ የኢኮኖሚ ትስስርን እውን ማድረግ ዋነኛ አላማው አድርጎ የተነሳ ነው። ሆኖም የሚጠይቀው የፕሮጀክት የገንዘብ መጠን ከፍተኛነት እቅዱ መሬት እንዳይወርድ አድርጎተታል። ይህ ብቻ ሳይሆን የዚሁ ፕሮጀክት አካል የሆነችው ደቡብ ሱዳንም ብትሆን የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ መዘፈቋ ሌላኛው የፕሮጀክቱ እንቅፋት ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው።

 

ሁለቱን ሀገራት በመሰረተ ልማት በማገናኘቱ በኩል  የተለያዩ ሥምምነቶች የተደረጉት በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ዘመን ነበር። ሆኖም ከተፈረሙት ሥምምነቶች መካከል አንዳቸውም እውን የሆኑበት ሁኔታ የለም። አሁንም ቢሆን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ ጉብኝት ወቅት የተነሱት ጉዳዮች የቀድሞዎቹ ሥምምነቶች ተግባራዊነት ላይ ነው። ኢትዮጵያን ከኬኒያ የሚያገናኘው ግዙፍ የኤሌክትሪ ኃይል ፕሮጀክት ወደ ተግባር የገባበት ሁኔታ የለም። ከሞያሌ ሀዋሳ፣ አዲስ አበባ እየተዘረጋ ያለው ረዥም የመንገድ ፕሮጀክት እውን የሆነበት ሁኔታ የለም።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
559 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 605 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us