የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ያሸሹት ገንዘብ እንዲመረመር ጥሪ ቀረበ

Wednesday, 20 June 2018 12:34

 

የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ወደ ውጪ ያሸሹት ገንዘብ በተመለከተ ምርመራ እንዲደረግበት አሜሪካ ጠየቀች። ሰሞኑን የአሜሪካ የፀረ ሽብር የፋየናስ ደህንነት ክትትል ሚስ ሲጋል ማንዳልከር በኬኒያ፣ በኡጋንዳና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባደረጉት ጉብኝት የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣናትን የገንዘብ ሽሽት በተመለከተ ክትትል ይደረግበት ዘንድ ማሳሳቢያ ሰጥተዋል።

 

ኃላፊዋ እንዳሉት የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ከሀገሪቱ ያሸሹትን ገንዘብ በኬኒያ ሪል ስቴት የኢንቨስትመንት ሥራ ውስጥ እየሰሩበት ይገኛሉ። በዚሁ በናይሮቢ በሰጡት ጋዜጣዊ “ከሰብዓዊ መብት ጥሰትና ከሙስና ያተረፉ ኃይሎች በእናቶችና በህፃናት እንደዚሁም በምስኪኖችና በንፁኃን ህይወት የተጫወቱ ሰዎች ይህንን ማስጠንቀቂያችን ሊሰሙ ይገባል” በማለት ተናግረዋል።

 

ለዚሁ የኃላፊዋ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ምላሽ የሰጠው የኬኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሱዳን ወደ ኬኒያ ሸሸ የተባለውን ገንዘብ በተመለከተ በጉዳዩ ዙሪያ ክትትል ለማድረግ ኬኒያ ከአሜሪካ ጋር የመረጃ ልውውጥ የምታደርግ መሆኗን አስታውቋል። የኬኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይሁንና የአሜሪካው ባለስልጣን የሰጡት ሀሳብ በምርመራ ሊረጋገጥ የሚገባው መሆኑን አመልክቷል። አንድ የኬኒያ ባለስልጣን በዚሁ ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ ኬኒያ ከደቡብ ሱዳን ተዘርፎ በሀገሪቱ የፈሰሰ መዋዕለ ነዋይ ካለ ንብረቱን በቁጥጥር ሥር ማዋል የምትችል መሆኑን አመልክተው፤ ይሁንና ሂደቱ ግን ዓለም አቀፍ ህግንና አሰራርን የተከተለ እንደሚሆን ገልፀዋል።

የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች በሀገሪቱ የተከሰተውን የእርስ በእርስ ጦርነት ተከትሎ በርካታ የሀገሪቱ ዜጎች የውጭ ሰብዓዊ እርዳታ እጅ እየጠበቁ ባለበት ሁኔታ ከፍተኛ ገንዘብ ወደ ውጭ እያሸሹ ነው የሚል ክስ በተደጋጋሚ ሲቀርብባቸው ቆይቷል። ይህንንም ጉዳይ በተመለከተ መቀመጫቸውን በአውሮፓና በአሜሪካ ያደረጉ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሲከታተሉትና የየግላቸውን የመረጃ ልውውጥ ሲያደርጉበት የቆዩ መሆኑን የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
92 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 473 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us