ደቡብ ሱዳን የነዳጅ ምርት ኤክስፖርቷን ልትጀምር ነው

Wednesday, 27 June 2018 12:31

 

 በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው ደቡብ ሱዳን ነዳጅ አምርታ ወደ ውጭ መላክ ካቆመች ዓመታትን ያስቆጠረች ሲሆን አሁን በሀገሪቱ የተገኘውን አንፃራዊ ሰላ ተከትሎ የነዳጅ ምርቷን ወደ ውጭ ለመላክ እንቅስቃሴ የጀመረች መሆኗን የሱዳን ትሪብዩን ዘገባ ያመለክታል። ደቡብ ሱዳን ወደብ አልባ ሀገር በመሆኗ ነዳጇን የምትልከው በተዘረጋው ቱቦ የሱዳን ንብረት በሆነው ፖርት ሱዳን ሲሆን ይሄንኑ ጉዳይ በዝርዝር የሚመለከት ልዑካን ቡድንን አዋቅራ ወደ ሱዳን የላከች መሆኗን የሱዳን ትሪብዩን ዘገባ ጨምሮ ያመለክታል።

እንደዘገባው ከሆነ ከሥራ ውጭ ሆነው የቆዩት ቱቦችና ማሽኖችም አስፈለጊው ጥገና ይደረግላቸዋል። በዚህም ደቡብ ሱዳን አሁን እያመረተች ያለውን እጅግ አነስተኛ የነዳጅ ድፍድፍ መጠን በቀን 290 ሺህ በርሚል ከፍ የማደረግ እቅድ አላትም ተብሏል። የደቡብ ሱዳን 98 በመቶው የሚሆነው ገቢ ከነዳጅ ምርት ሽያጭ የሚገኝ ሲሆን ይሁንና ጦርነቱ መቀስቀሱን ተከትሎ ይህ ገቢ ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ሁኔታ የቆመበት ሁኔታ ነበር።

 

ደቡብ ሱዳን የነዳጅ ምርቷን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦን እንደዚሁም ወደብን ጭምር ከሱዳን የምትጠቀም በመሆኑ የሱዳንንም ኢኮኖሚ ጭምር ያነቃቃዋል እየተባለ ነው። ሱዳን በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ እጥረት የገጠማት ሲሆን የደቡብ ሱዳን ሰላም መሆን ብሎም ሀገሪቱ የነዳጅ ምርት ወደ ውጭ ለመላክ እንቅስቃሴ መጀመሯ የምስራች ሆኖላታል። በዚህ ዙሪያ የሁለቱ ሀገራት ሚኒስትሮች የጋራ ውይይት ማድረጋቸውን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
83 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 443 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us