ፎር ዩ ስታይል ፕላቲኒየም እና ሞዴል ዮሐንስ አስፋው የሁለት ዓመት ስምምነት ተፈራረሙ

Wednesday, 11 July 2018 12:13

 

በይርጋ አበበ

ኢትዮጵያዊው ዓለም አቀፍ ሞዴል ዮሀንስ አስፋው ለሁለት ዓመት በ300 ሺህ ብር ከአበበ ሀብቴ አስመጪ ኩባንያ ፎርዩ ስታይል ፕላቲኒየም ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ።

ከአውሮፓና ምዕራባዊያን አገሮች የወንዶች ሙሉ ልብሶችን (ሱፍ) በማስመጣት ስራ የተሰማራው አበበ ሀብቴ አስመጪ፤ በኢትዮጵያ ስራ የጀመረው በመስከረም ወር 2010 ዓ.ም ነበር። ድርጅቱ ከዓለም አቀፍ ሞዴሉ ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ለሰንደቅ ጋዜጣ የገለጹት የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪጅ አቶ አበበ ሀብቴ፤ ስምምነቱን የተፈራረሙት የፋሽን ኢንዱስትሪውን በአገር ውስጥ ለማሳደግና እግረ መንገዱንም ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት መሆኑን ተናግረዋል።

ዓለም አቀፍ ሞዴል ዮሐንስ አስፋው በበኩሉ፤ ‹‹በሀገራችን የሞዴሊንግና ፋሽን ኢንዱስትሪ መስክ የተሰማሩ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን በሀገራቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ማስተዋወቃቸው ለሀገራችን ሞዴሊንግና ፋሽን እድገት ተስፋ ሰጪ ነው›› ብሏል። የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ በመመረጡ የተሰማውን ደስታም ገልጿል።

የሁለቱ ወገኖች ስምምነት ስራ ላይ የሚውለው የፊታችን ሀሙስ ሀምሌ 5 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ይሆናል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
74 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 932 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us