ሩዋንዳ የቻይ እና የህንድን ትኩረት እየሳበች ነው

Wednesday, 25 July 2018 13:19

ከአስከፊ የእርስ በእርስ ጦርነትና የዘር ማጥፋት እልቂት ውስጥ በመውጣት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ያለችው ሩዋንዳ የቻይናና የህንድን ትኩረት የሳበች መሆኗን ከሰሞኑ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። ቀደም ሲል በሩዋንዳ የጉብኝት ቆይታ ያደረጉት የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ከሩዋንዳ ጋር ዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ ትስስር ሊያመጡ የሁለትዮሽ ግንኙነት ፊርማዎችን የተፈራረሙ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢፒንግ በሩዋዳ ኪጋሊ በመገኘት በተመሳሳይ መልኩ በዘርፈ ብዙ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር የመከሩ መሆናቸውን የሲ ኤን ኤን ዘገባ ያመለክታል።

 

ፕሬዝዳንት ዢፒንግ በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው በበሪክስ ህብረት ስብሰባ ላይ ከመገኘታቸው በፊት በአፍሪካ አህጉር በሚኖራቸው ቆይታ ከሩዋንዳ በተጨማሪ በሞሪሸስ ቆይታ የሚያደርጉ መሆኑን ዘገባው ጨምሮ ያመለክታል። ቻይና በሩዋንዳ ኢኮኖሚ ውስጥ ከብድር አቅርቦት እስከ መሰረተ ልማት ግንባታ ብሎም እስከ ግዙፍ ኢንቨስትመንቶች ድረስ በስፋት የተሰማራች ሀገር ናት።ህንድም ቢሆን በሩዋንዳ ያላት የብድር አቅርቦትና የኢንቨስትመንት ድርሻ በቀላሉ የሚታይ አይደለም።

 

እንደ ዘገባው ከሆነ በሩዋንዳ ከተገነባው መንገድ ውስጥ 70 በመቶው የሚሆነው የተገነባው በቻይና ኩባንያዎች ነው። ቻይና በሩዋንዳ ባለፉት 12 ዓመታት በ16 ፕሮጀክቶች 4 መቶ ሚሊዮን የኢንቨስትመንት ሥራወዎች ውስጥ በመሰማራት በሩዋንዳ ኢኮኖሚ ውስጥ ሰፊ ሚናን ተጫውታለች።

 

ዘገባው ጨምሮም በአፍሪካና በቻይና መካከል ያለው የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት እስከ 2014 ባለው ጊዜ ውስጥ 220 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ መሆኑን አመልክቶ እንደ ሩዋንዳ ያሉ ሀገራትም ለቻይና አፍሪካ ግንኙነት ሰፊ ሚና ያላቸው መሆኑን አትቷል።

 

በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጀመሪያ የሩዋንዳ የኢኮኖሚ እድገት በአፍሪካ ሶስተኛው ፈጣን እድገት መሆኑን ዘገባው የዓለም ባንክን ዋቢ በማድረግ አትቷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
37 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 71 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us