የዓመቱን የመዝናኛ እንግዶች በጥቂቱ

Wednesday, 10 September 2014 10:37

ባሳለፍነው የ2006 ዓ.ም በርካታ እንግዶችን በመዝናኛ አምድ ስር፤ የመፅሐፍ፣ የፊልምና የቴአትር ዳሰሳዎችን ጨምሮ ከዝነኞችና ከአንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎች ጋር ቆይታ ማድረጋችን ይታወሳል፤ እነሆ በአዲስ አመትም እንዲሁ በርካታ እንግዶችንና ስራዎችን ወደናንተ ማቅረባችን እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ለዛሬ ግን አሮጌውን አመት ሸኝተን አዲሱን ስንቀበል፤ በ2006 ዓ.ም በመዝናኛ አምድ ካቀረብናቸው ዝነኞች መካከል አለፍ- አለፍ ብለን ከአዝናኝ ቁምነገሮቻቸው ቀነጫጭበን አቅርበልናችኋል፡፡

 

 

  • በርካታ ፊልሞች ላይ የሚያዩህ ሰዎች ዋጋው አነስ ያለ ነው ይሉሃል?. . .

“ክፍያን በተመለከተ እስካሁን የሚገባኝን አግኝቻለሁ ብዬ አላስብም። ይኸው እንደምታየኝ በእግሬ ሯጭ ነኝ። የሚገርምህ ክፍያው በቂ ሳይሆን እንኳን የተነጋገርከውን የማይከፍልህም አለ። በጭቅጭቅና በሽምግልና የሚከፍልህም አለ። ይህን ስልህ ደግሞ ጥሩዎችም መኖራቸው መዘንጋት የለበትም”


                                    ተዋናይ መኮንን ላዕከn


  • ራስህን እንዴት አስተማርከው?. . .

“እውነቱን ለመናገር አንዳንድ ጊዜ ሳስበው ዩኒቨርስቲ ብገባ ኖሮ ይሄን ያህል ላነብ እችል ነበር? ብዬ ራሴን እጠይቃለሁ። እናም አልደረስኩም ብለህ ባሰብክ ቁጥር ማንበብህ ይጨምራል። አሁን ደግሞ ቅርብ ጊዜ አካባቢ ያነበብኳቸውን ፅሁፎች ለሌላ ሰው ማስነበብ ስጀምር የበለጠ አቅም ለመፍጠር አነባለሁ። ልክ አንድ መኪና ነዳጅ እንደሚያስፈልገው ሁሉ በጥበብ ስራ ውስጥ ስትሆን በሁሉም ዘርፍ ማንበብ ያስፈልጋል።”

                                   

አርቲስት ፈለቀ የማርውሃ አበበn


  • የሰራሃቸው ፊልሞች ሁሉ በአንተ ዕይታ የተዋጣላቸው ነበሩ?. . .

“ፊልም የቴአትርን ያህል ጥራት የለውም። ያለህ ዕድል ምንድነው መሰለህ፤ አንድ እንዳትጠፋ ትሰራበታለህ። ሁለተኛ ደግሞ ኢንደስትሪውን (ዘርፉን) እየለመድከውና እያወከው መሄድ ስለሚያስፈልግ ከደከሙት ትንሽ ሻል ያሉትን ሰርቻለሁ እንጂ እኔ የሰረኋቸው ሁሉ ፍፁም ናቸው እያልኩህ አይደለም።”

                                                       

አርቲስት ሽመልስ አበራ (ጆሮ)n


 

 

 

  • ስዕል ላንቺ ምንድነው?. . .

“ሃሳብ ሲበዛብኝ የሚያስጨንቁና የሚያሳዝኑ ሁኔታዎች ሲገጥሙኝ ነፃ የምሆንበት ነገር ነው። ሁለተኛው ደግሞ በውስጤ ያከማቸሁትንና ለሌሎች ይጠቅማሉ የምላቸውን ሃሳቦች በሙሉ የምገልፅበት መሳሪያ ነው ማለት እችላለሁ። በአፌ መናገር የማልፈልገውንም ነገር ጭምር በሥዕል ማሳየት ይቀናኛል። ሥዕል የራሱ ቋንቋ አለው፤ ሀሳቤን በደንብ ነው የምገልጽበት።”

                             

ሰዓሊ ዓለምፀሐይ ንባበn


  • ኮሜዲን ለየት የሚያደርገው ነገር ምንድነው?

“በቀልድ (በኮሜዲ) የሚነገር ነገር ብዙ ሰዎች ሊሰሙትና አይረሴነትም ሊኖረው መቻሉ ለኔ የኮሜዲ ልዩ ባህሪይ ይመስለኛል። ኮሜዲ ቀልደኛ መሆንን ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ደረጃ ተሰጥኦን የሚጠይቅና ፈጠራን የሚሻ ነገር ነው።”

                             

ኮሜዲያን ምትኩ ፈንቴn


  • ድክመት ያለባቸውን ፊልሞች ደፍረህ አልሰራም ያልክበት ጊዜ አለ?. . .

“እውነቱን ለመናገር ሳይመጥኑኝ ወይ ይሉኝታ ይዞኝ፤ ወይ ብር ቸግሮች የሰራሁት ፊልምም አለ። አሁን ያ ጊዜ አልፏል፤ ጥሩነቱ አሁን-አሁን ፊልም ማክሰርም ጀምሯል። ለምን ቢባል የተመልካችም የእይታ አቅም እያደገ ነው።”

                             

አርቲስት ሚካኤል ታምሬn


  • በፃፍካቸው ታሪካዊ ተውኔቶች ውስጥ ስላሉት ግጭቶች እስቲ ንገረኝ?. . .

“አብዛኛው የኢትዮጵያ ታሪክ የጦርነት ታሪክ ነው። ሁሉም ኢትዮጵያ ውስጥ የተደረጉት ጦርነቶች ፍትሐዊ ወይም ተገቢ ጦርነቶች ናቸው ብዬ አላምንም። አንዳንዱን ታሪክ አገላብጠህ ወደኋላ ስታይ የሚያስቁ አይነት የጦርነት ምክንያቶችን ታገኛለህ። እንዲያው ከመሬት ተነስቶ “ሄደን እንያዘው፤ ሄደን እንውጋው” የሚል አይነት ቀልድ መሰል ምክንያቶች የተከሰቱ ጦርነቶች አሉ።”

                             

 

    መልካሙ ዘርይሁ

 

የ“ንጉስ አርማህ” እና የ“ህንደኬ” ቴያትሮች ደራሲn


  • ከሰራሃቸው ገፀ-ባህሪያት መካከል ፈታኝ የነበረው የቱ ነው?

“እስካሁን ባለውም ቢሆን የሚመጡት ከዚህ ቀደም ያልተጫወትኳቸው አዳዲስ ገፀ-ባህሪያት በመሆናቸው አንዱን ብቻ መምረጥ ይከብደኛል። ለኔ የመጨረሻው ስራ የመጨረሻው ፈተናዬ ነው። ግን አዲስ ስራ ሲመጣ ደግሞ እርሱ አዲሱ የመጨረሻ ፈተናዬ ይሆናል ማለት ነው።”

                             

አርቲስት ተስፉ ብርሃኔn


  • የመጀመሪያ ትወናሽ ትዝ ይልሻል?

“የሚገርምህ ነገር የመጀመሪያ የመድረክ ስራዬን የጀመርኩት ልጅ እያለሁ በቤተክርስቲያን ውስጥ ነው። የአስር ወይም የዘጠኝ ዓመት ልጅ እያለሁ ነው፤ ደግሞ የተጫወትኩት ገፀ-ባህሪይ ስራዬ የክርስቶስ ደቀመዝሙር ሆኜ ነው። ቴአትርን የጀመርኩት ወንድ ገፀ-ባህሪይ በመጫወት ነው ማለት ይቻላል፡፡”

                                   

አርቲስት ጀንበር አሰፋn


  • ሴትና ውበት ላንቺ ምን ትርጉም ይሰቱሻል?

ለኔ ሴትና ውበት ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው፤ አይለያዩም። ውበት ሁሉ ሲገለፅ በሴት ልጅ ነው፤ ጨረቃን፣ ፀሐይን፣ ሀገርን ሁሉ በሴት ነው የምንወክላቸው። ስለዚህ ለኔ ሴትና ውበትን መለየት ያስችግረኛል።

                                   

ዲዛይነር ሳራ መሐመድ

ይምረጡ
(6 ሰዎች መርጠዋል)
15983 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us