አዝናኝ እና አፅናኝ ግጥሞች

Thursday, 07 May 2015 17:29

ከዓመታት በፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዘወትር ረቡዕ አመሻሽ ላይ በባህል ማዕከል አዳራሽ መድረክ ተፈልጎ የማይታጣ ወጣት ገጣሚ ነበር። ከዚያም በኋላ በተለያዩ የግጥም ምሽቶች እና መገናኛ ብዙሃን አማካኝነት የግጥም ስራዎቹን አስደምጧል። እነሆ ቢዘገይም እንኳን ዘንድሮ አንድ ብሎ “ያማል!” የተሰኘ የግጥም ስብስቡን ለንባብ አብቅቷል፤ ወጣቱ ገጣሚ ሰለሞን ሳህለ።

“ያማል!” የግጥም ስብስቦች የወጣቱን ምልከታ፣ ትዝብት፣ ጨዋታና ቁምነገር በማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መነፅሮች የሚያሳይ ስራ ነው። ስራዎቹ ለራስ የሚጋብዙት፤ ለሌሎችም የሚያወሩት አዝናኝ እና አፅናኝ ሀሳቦች የተንሰራፋባቸው ናቸው። በመፅሐፉ ውስጥ 49 ግጥሞች የቀረቡ ሲሆን፤ ገሚሶቹ ረጅምና የአጭር ልቦለድ ዓይነት ታሪክ የሚነግሩን ናቸው፣ ግን አይሰለቹም። ገሚሶቹም በጥቂት መስመሮች የረጅም ልቦለድ ሃሳብ የሚወጣቸውና እምቅ ሃሳቦች ያነገቱ ናቸው።

በዛሬው በዚህ መዝናኛ አምድ ስር ለመዳሰስ ያቀረብናቸው የገጣሚውን አዝናኝ አገላለፆችና አፅናኝ እይታዎች ነው። ገጣሚው ሲወድ፣ ገጣሚው ሲበደል፣ ገጣሚው ግራ ሲገባው፤ እንዲሁም ገጣሚው አገሩን ሲያስብ የሚሰሙትን ስሜቶች በ “ያማል!” እያመመንም ቢሆን እንድናነባቸውና እንድንፅናናባቸው ይጋብዘናል።

በፍቅር ይታበዳል እንጂ ፍቅር በራሱ እብድ አይደለም እንድንል ፍንጭ የሚሰጠን ገጣሚው፤ የወደዳትን ልጅ ክፉዋን ተመኝቶ መልሶ ፀሎቱን ሲያጥፍ እናያለን በ “ሁለት ፀሎት” ስራው አፍቃሪው እያነሳ የሚያፈርጠኝ የልጅቷ አይን ነውና ፈጣሪ ሆይ አጥፋልኝ ሲል ይፀልያል። መልሶ ግን በሁለተኛ ፀሎቱ እንዲህ ማስተካከያ ያደርጋሉ።

ሁለተኛው. . .

ምንም እንኳን ቢከፋኝም

ምንም እንኳን ብፀልይም

አደራ ፀሎቴን እርሳው። (ገፅ-78)

ሰዎች ሲዋደዱ ያኔ ዓለም ገነት ትሆናለች፤ ሁሉም ነገር ሰላም ሁሉም ነገር ፍቅር ይሆናል የሚለው ገጣሚው “አሁን . . . በዚች . . . አሁን” የተሰኘ ግጥሙ እንዲህ ይላል።

ረሞጩ ጠፋ በረዶው ወረደ፤

ዓለም እፎይ አለች ጦስ ጥምቡሳስ ሄደ፣

ንፋስ ዜማ ሆነ ሀሩሩ በረደ፣

የኔ ልብ እሳቱ አንቺን በወደደ

ካፈርና ከውሃሽ ህይወት የወሰደ

አምሮ የሚመራ ፍቅር ተወለደ። (ገፅ -10)

ገጣሚው የመፅሐፍ ርዕስ ያደረገው “ያማል!” የሚተርከው የሚወዳትን ሴት ቀጥሮ በእርሷ መቆየት ውስጥ ያለውን ስቃይና ህመም ማሳየት ነው። ይህ ግጥም ከሁሉም ረጅምና አራት ገፅ ተረከ ያለው ሲሆን፤ ሁሉም ነገር ያማል ያላል። በስተመጨረሻ ግን የሚከተለውን አስፍሯል።

ግን. . .

እኔ አንቺን ስወድሽ እኔ አንቺን ስወድሽ

ይሄን ሁሉ ችዬ ነው የምጠብቅሽ።

ቢሆንም ግን ያማል!!! (ገፅ-20)

“ያማል!” አገርና ፖለቲካን ሸንቆጥ፣ ቆንጠጥና ኮርኮር የሚያደርጉ ስንኞችን ያስነብበናል። የመፀሐፉ የመጀመሪያ ግጥም ሆኖ የተቀመጠው “ሁለት ሞት” የፖለቲካችንን ጉራማይሌነት በስላቅ የሚያሳይ ነው።

ስለ “ወንበር” ስንፅፍ. . . “ሥልጣን” ነው እያሉ

ስለ “መንገድ” ስንፅፍ . . . “ ስደት” ነው እያሉ

ስለ “መጮህ” ስንፅፍ. . . “አመፅ” ነው እያሉ

ስለ “መሳቅ” ስንጽፍ . . . “ምፀት” ነው እያሉ

ቅኔ ሳንናገር ቅኔ እያናገሩ

በብረት ካቴና እኛን አሳሰሩ (ገፅ -7)

ገጣሚው ሀገር ለእርሱ የድልና የታላቅነት ምልክት ስለመሆኗ ሲተርክ አስቸጋሪ ጊዜያቶቿን የዘነጋ በሚመስል መልኩ ደጋግ ጊዜቶችን ብቻ የሀሳቡ ማጠንጠኛ አድርጎ የሚከተለውን “አንቺ ማለት እኮ” ሲል ይናገራል። በግጥሙ ውስጥ በርካታ ተምሳሌቶች የተነሱ ሲሆን፤ ሲድህ የቆየ ህጻን በቆመበት ቅፅበት፤ ኃይሌ ፖልቴርጋትን ባሸነፈበት ቅፅበት፤ በአፍሪካ ዋንጫ በሱዳን ላይ ውጤት ባገኘንበት ዕለት ያለውን የድልና የብርታት ወቅት ስሜት ይተርክና 97ን ያስታውሰናል።

አንቺ ማለት እኮ . . .

የዘጠና ሰባት ያገራችን ምርጫ

ሚያዚያ ሰላሳ መስቀል አደባባይ

የታየው ተአምር

የነበረው ተስፋ የነበረው ሲሳይ

የፍቅር ምልክት የአዲስ ዘመን ምኞት

በወኔ ቀስቅሶት በይነጋል ሞልቶት

የነበረች ሰዓት የነበረች ቅፅበት

አንቺ ማለት ያ ነሽ. . .

ታሪክ የማይረሳሽ የታሪክ ምልክት

አንቺ ማለት እኮ . . . አለ

ብዕሩን ጨብቶ ሰለሞን ሳህለ። (ገፅ-55)

ለገጣሚው ሀገሩን ለሁሉም ነገር መለኪያው ሲያደርጋት እናነባለን። ለዚህ እንደማሳያ የሚሆነው ቃል ባጠረው ጊዜ ጥልቅ ስሜቱን ሀገሩን በመውደዱ ልክ ለማሳየት ሲሞክር “ያቺን ልጅ ንገሯት” በተሰኘ ግጥሙ ውስጥ ለልጅቱ ፍቅሩን ለመግለፅ እንዲህ ይላል፤

የምጠብቃት ልጅ የመጣች እንደሆን

መስከረምን አልፋ . . .

ጥቅምትን ተሻግራ ህዳሩ ሲታጠን

ገላዬ ቆሽሾ አካላቴ ዝሎ

ገዴ ተጎሳቁሎ

ድንገት አልፋኝ ብትሄድ. . .

ፍቅሬ ተዘንግቷት

ማንነቴ ጠፍቷት

እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያቺን ልጅ ንገሯት

እንዳገሩ ነበር የሚወድሽ በሏት! (ገፅ -102)

ሌላኛው በመፅሐፉ ውስጥ ያለው ረጅም በብሶትና በስላቅ የተሞላው ግጥም ደግሞ “ወንበርና ወንበርተኞች” ይሰኛል። በዚህ ግጥም ውስጥ መሪና አመራርነት በሹፌርና በዳኛ ተመስለው ተቀምጠዋል። ሹፌሩን ሲያነሳ

ሹፌር ወንበርተኛው

ግራ ቀኙን ሳያይ መንገዱን አሻግሮ

ሰውን ያህል ፍጡር. . .

አውራ ጎዳናው ላይ በጎማ ጠቅልሎ

ሸቅብ ይነዳዋል መሪውን ጠምዝዞ

የሞቀን የሰው ነብስ ድንገት አቀዝቅዞ (ገፅ - 59)

በዚህ ሾፌር ታክሲ ውስጥ ተማሪ፣ አስተማሪ፣ ነጋዴ፣ ደራሲ ላብአደር በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን አሉ። ሲቀጥል ገጣሚው ዳኛውን ያነሳል። በፍትህ ወንበር ላይ ተቀምጦ የድምፅ አልባዎችን ፍትህ እንዴት እንደሚቀጭ በጉልህ ያሳያል። በሙስና አይኑ የተሸበበውን ዳኛ አንዲትን አሮጊት እንዴት ፍትህ እንደነሳት ሲተርክ እንዲህ ይላል።

ፍትህ የሚጠይቅ የእውነት ያለህ የሚል

ሶስት ትላልቅ ዶሴ ፊት ለፊት ይታያል

የላይኛው ዶሴ የዚያች አሮጊት ነው

ዳኛው ፊት ከነሳው አራት ዓመት ሞላው (ገፅ 59)

ገጣሚው ሌላም ታሪክ በዚህ ግጥም ውስጥ ይተርካል። እውነት የተናገረ እውነትን የዘገበ ጋዜጠኛ አሸባሪ ተብሎ ፍርድ ይወርድበታል፤ ህግ ይናድበታል ይለናል። ይህንንም ሲያሳይ

ይህ ሶስተኛ ዶሴ

የሀተታው አይነት የክስ ብዛቱ

የቃለ ተውኔት የጀርባ ድርሰቱ

የመስካሪው ውሸት የቃል መምታታቱ

በዝግ ችሎት ይሁን ይቅረብ ለነገ አድሮ

የሰኞ ማክሰኞ የአርብ ቀጠሮ

የጠያቂው ብዛት በጩኸት ታውሮ

ትንሽ የሚመስለው እያደር ተካሮ

አልጀዚራ መጥቶ እፍ እያለ አራግቦት

ቢቢሲ ዘግቦት ሲኤን ኤን አይቶት

ያለው ይሄ ዶሴ. . .

ከወንበሩ አጠገብ. . .

ከጠረጴዛው ላይ የምናየው እኛ

የማንም አይደለም ነው የጋዜጠኛ (ገፅ -61)

በስተመጨረሻ ግን ገጣሚው አፍሪካን ጠቅልሎ የሚከተለውን ምክር ያቀብላል። ወንበር የሚጠይቅ እንዳይኖር ወንበሩን ሰበሩት ይለናል።

ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ

ወደደኝ ያለውን ሰላሙን ይነሳል

መረጠኝ ያለውን ህዝብ ያተራምሳል

ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ

መኖሪያን አይደለም መቆሚያን ያሳጣል

በጭቁን አፍሪቃ ጭቁን አፍሪቃዊ

ሕዝብ ሆይ ይህን ስማው

ከወንበርተኛው ጋር ከመጣላት በፊት

ችግር ያለበትን ወንበር ስበረው

ያኔ. . . .

ወንበር አምጡ ብሎ ማንም አይጠይቅም

ወንበር በሌለበት ወንበርተኛ የለም። (ገፅ - 64)

“ያማል!” የግጥም ስብስቦ ታሪክ፣ ቁጭት፣ ፍቅርና ምኞት በውብ ቋንቋና አተራረክ የግጥም ለዛውን እንደጠበቀ የሚቀርብበት መፅሐፍ ነውና አንብበን ስንጨርስ ለሌሎች የምንተርከውን እናገኝበታለን።n

Entertainment 504                                         Shewa

አዝናኝ እና አፅናኝ ግጥሞች

በአሸናፊ ደምሴ

“ያማል!” የግጥም ስብስቦ ታሪክ፣ ቁጭት፣ ፍቅርና ምኞት በውብ ቋንቋና አተራረክ የግጥም ለዛውን እንደጠበቀ የሚቀርብበት መፅሐፍ ነውና አንብበን ስንጨርስ ለሌሎች የምንተርከውን እናገኝበታለን።

ይምረጡ
(70 ሰዎች መርጠዋል)
38702 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us