“ዝነኛ አይደለሁም!” ተዋናይ አብዱልከሪም ጀማል

Monday, 03 February 2014 16:09

የዛሬው እንግዳችን የጅማ ልጅ ነው። የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እዛው ተከታትሏል። የመጀመሪያ ዲግሪውን ለመስራትም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት  ትምህርት ክፍለ- ገብቷል። የማስተርስ ዲግሪውንም በዚሁ ክፍለ ትምህርት ውስጥ በማታው ጊዜ በመከታተል ላይ የሚገኘው ወጣቱ ተዋናይ፣ ዳይሬክተርና ፕሮዲዩሰር፤ አብዱልከሪም ጀማል። በአሁኑ ወቅት በአንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በተዋናይነት፣ በቴአትር ገምጋሚነትና በአዘጋጅነት እየሰራ ይገኛል። ተዋናይ አብዱል ከሪም ጀማል፤ ከተሳተፈባቸው ስራዎቹ መካከል ከቴአትር ረመጥ፣ የበዓል እንግዶችና ብር አምባር ሲጠቀሱለት፤ ከፊልም ደግሞ “ስርየት” እና “ኮመን ኮርስ” አይረሴዎቹ ናቸው። የአፍታ ቆይታችንን እነሆ በንባብ፤
ሰንደቅ፡- ዝነኛ ነኝ ብለህ ታስባለህ፤ ከሆነስ ዝናው ነፃነትህን ነፍጎሃል?
አብዱልከሪም፡- ኖ! ዝነኛ አይደለሁም፤ ነፃነቴንም አልነፈገኝም። እርግጥ ነው የተወሰኑ ሰዎች ያውቁኛል፡፤ በመድረክ፣ በሲኒማና በቪሲዲ የወጡ ስራዎቼን የተከታተሉ ሰዎች ሊያውቁኝ ይችላሉ። በተወሰነ ደረጃ እታወቅ ይሆናል እንጂ ዝነኛ አይደለሁም። ከሚያውቁኝ ሰው ይልቅ የማያውቀኝ ሰው ይበልጣል።
ሰንደቅ፡- በፕሮፌሽናል መድረክ ላይ የመተወን አጋጣሚውን እንዴት አገኘህ?
አብዱልከሪም፡- በፕሮፌሽናል መድረክ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረብኩት “የ13 ወር ፀጋ” በሚል ተውኔት ላይ በብሔራዊ ቴአትር ነው። ከዚያ በኋላ እዛው ቴአትር ቤት በ1999 ዓ.ም አካባቢ “ክሊዮፓትራ” በተሰኘው የተስፋዬ ገ/ማርያም ቴአትር ላይ ተሳትፎ ነበረኝ። ከዚያ በኋላ ደግሞ ሀገር ፍቅር ቴአትር ከመቀጠሬ በፊት “የቬኑሱ ነጋዴ”ን በተጋባዥ ተዋናይነት ሰራሁ፤ ተቀጥሬ ደግሞ የመጀመሪያ ስራዬ የሆነው “ረመጥ” የተሰኘው ቴአትር ነው። ከዚያ በኋላ “የበዓል እንግዶች” እና “ብር አምባር” በተሰኙ ቴአትሮች ላይ እየተወንኩ ነው። በዝግጅት ደረጃ “ገፅሁለት” የተሰኘ ቴአትር አዘጋጅቻለሁ፡ ከዚህ ውጪ በቀጣዮቹ ሳምንታት ለመድረክ የሚበቃና በእስጢፋኖስ ከበደ በተዘጋጀው “የጉድ ቀን” የተሰኘ ቴአትር ላይ ሰርቻለሁ ማለት ነው። ለዚህ ሁሉ ስራ አጋጣሚውን ያገኘሁት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እየተማርኩኝ ሳለ ለተጨማሪ እውቀት “ሆሌ ላንድ አካዳሚ” ስሄድ ተስፋዬ ገ/ማርያምን በመተዋወቄ እርሱ ነው አቅሜን አይቶ ለአንድ ገፀ ባህሪይ አጨኝ ከዚያ በኋላ ነው የቀጠለው።
ሰንደቅ፡- ተማሪ እያለህ አጋጣሚውን አግኝተህ ቀጥታ ወደቴአትር ቤት መድረክ ስትሄድ በወቅቱ ምን ነበር የተሰማህ?
አብዱልከሪም፡- ትልቅ እድል ነው። ተማሪ ሆኜ፤ አማተር ሳለሁ ያንን የመሰለ ዕድል ማግኘቴ ለኔ ትልቅ ነገር ነው። የሚገርምህ “የ13 ወር ፀጋ” ቴአትር ላይ ትላልቅ ከሚባሉት ሙሉአለም ታደሰ፣ ፀጋዬ ገ/ሀና፣ ቴዎድሮስ ተስፋዬን ከመሳሰሉ አርቲስቶች ጋር ነበር መድረክ ላይ የወጣሁት። ከእነርሱ ጋር መድረክ ላይ እኩል ቆሞ መተወን በዚያን ሰዓት ለኔ ትልቅ እድል ነበረ።
ሰንደቅ፡- ከትወናው ውጪ በፅሁፍና በዝግጅት ያለህ ተሳትፎ ምን ይመስላል?
አብዱልከሪም፡- በፅሁፍ ደረጃ ሰነፍ ነኝ። አለመቻል ሳይሆን ፅሁፍ ብዙ መቀመጥና ተመስጦ (concentration) ይፈልጋል። ስራው በጣም ከባድ ነው። በርግጥ ሌሎቹ ስራዎችን ለማቅለል ፈልጌ አይደለም። ድርሰት ግን የተለየ ፈጠራ ነው። በዝግጅት ደረጃ ግን በዚሁ መድረክ ላይ “ገጽ ሁለት” የተሰኘ ቴአትር አዘጋጅቻለሁ። እሁድ ማታ ይታያል። ከቴአትር ውጪ ደግሞ “ቢ.አይፒ” እና “ፎርጅዱ” የተሰኙ ፊልሞችን አዘጋጅቻለሁ። “ፎርጅዱ” ገና ያልወጣ ስራ ነው። በተረፈ ግን ከወዳጄ ጋር በመተባበር ፊልም እና ቴአትር ፕሮዲዩስ አደርጋለሁ።
ሰንደቅ፡- እስቲ ስለተዋናይ እና ስለሚተውነው ገፀ ባህሪ መመሳሰል ንገረኝ፣ “አክተርና ካራክተር” ምንናምን ናቸው? አንተን ምሳሌ አድርገህ ንገረን አክተርና ካራክተር ምን ያህል ይሳሳባሉ?
አብዱልከሪም፡- በርግጥም ይሳሳባሉ ብዬ አምናለሁ። ምን ጊዜም አንድ አዘጋጅ የአንድን ገፀ ባህሪይ ውስጡን ሲያስብና ወደመድረክ ሊያመጣው ሲፈልግ ከሚያስበው ገፀባህሪይ ጋር ሊስማማና ሊሳሳብ የሚችልን ተዋናይ መፈለግ ግዴታው ነው። የተዋናዩን ተክለ ሰውነቱን፣ ድምጹንና አንዳንዴም ባህሪውን ማየት መቻል አለበት። እኔም ብዙ ጊዜ ዳይሬክተሮች ሲፈልጉኝ ከኔ ቁጠን ያለ ተክለ ሰውነት ጋር ተቀራራቢ የሆነ ገፀ ባህሪይ ነው የሚሰጡኝ። ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ አከተርና ካራክተር ይመሳሰሉት።
ሰንደቅ፡- የምትሰራቸው ገፀ-ባህሪያት ከሞላ ጎደል ከመመሳሰላቸው የተነሳ በህይወት ተፅዕኖ አላሳደረብህም?
አብዱልከሪም፡- ይሄን ያህል የከፋ ነገር አልገጠመኝም። ነገር ግን በቴአትሩም፣ በሲኒማውም ሆነ በቪሲዲ ስራዎችህ ገፀ-ባህሪያት ስም ልትጠራ ትችላለህ። ምናልባትም ከገፀ-ባህሪው ጉዳይ ተነስተው እንደቀልድ አንድ ነገር ጣል ሊደረግብህ ይችላል። በየመንገዱ ማለቴ ነው። ለምሳሌ በቅርቡ የወጣው “ኮመን ኮርስ” በተሰኘው ፊልም ላይ አትሌት ሆኜ ነው የምሰራው፤ ያ አትሌት ከምንም ተነስቶ የሆነችን ልጅ ጠበሰ። በኋላ ተወዳድሮ ብዙ ብር አገኘ። ወዲያው ብር ከማግኘቱ የድሮ ወዳጁን ከዳት። እና አንዳንድ ሰዎች መንገድ ላይ ሲያገኙኝ “ያው ናችሁ እኮ እናንተ ብር ስታገኙ ሰው ትከዳላችሁ!” ይልሃል። አንዳንዴ  እንደዚህ አይነት ነገር ያጋጥማል።
ሰንደቅ፡- እስቲ ስለፊልምና ቴአትር የምታስበውን ነገር ንገረኝ?
አብዱልከሪም፡- ፊልም በጣም አሪፍ ነው። ነገር ግን እኔ አንዱን ምረጥ ብትለኝ ቴአትርን አስበልጣለሁ። ምክንያቱም የምዝናናበት የምረካውም ቴአትር ስሰራ ነው። መድረክ ላይ ስህተት ካንተ አይጠበቅም ብትሳሳት እንኳን የፈጠራ ሰው መሆን ይጠበቅብሃል። በዚህ ላይ ተመልካች ፊት መስራት በጣም ነው የሚያስደስተው። ፊልም እንግዲህ እንደምታየው በብዛት እየተሰራ ነው። ስለዚህ ወደፊት በርካታ የተሻሉ ስራዎችን የምናይበት አጋጣሚ ይመጣል ማለት ነው። በአሁኑ ወቅት የቱንም ያህል በርካታ ፊልሞች ይመረቱ እንጂ ተመልካቹ መምረጥ ጀምሯል። ይህ ደግሞ የተመልካቹን የማጣጣም አቅም መጨመር ያሳይሃል። ይህም የሆነው ብዙ ፊልሞች በመታየታቸው ይመስለኛል። ስለዚህ የፊልም ባለሙያዎች ስለሚሰሩት ፊልም ዕውቀት ሊኖራቸው ይገባል። የተሻለ ነገር ሰርተው ለመምጣትና ተመልካቹን ለማርካት።
ሰንደቅ፡- አንተ ፊልም ሰርተሃል ትርፋማ ነበር?
አብዱልከሪም፡- ለኔ የመጀመሪያ ስራ ምንጊዜም መማሪያዬ ነው። “ቪ.አይ.ፒ” ፊልምን ሰርቻለሁ በገንዘብ ደረጃ አልከሰርኩም፤ አላተረፍኩም። ነገር ግን ብዙ የፊልም አሰራር መንገዶችን ተምሬበታለሁ። ለኔ ትርፌ መማሬ ነው። ለቀጣይ ስራዎቼ እጠቀምበታለሁ ብዬ አስባለሁ።
ሰንደቅ፡- ከሰራሃቸው መካከል የማትረሳቸውን ስራዎችና ገጸ -ባህሪያት ንገረኝ እስቲ?
አብዱልከሪም፡- የሰራኋቸው ስራዎች ሁሉ ደስ ይሉኛል። ነገር ግን በተለየ መልኩ የማስታውሳቸው ለምሳሌ ከፊልም ከብዙ ሰው ጋር ያስተዋወቀኝ “ስርየት” ፊልም ነው። እሱ ፊልም ላይ የተጫወትኩትን ገጸ-ባህሪይ አሁን ድረስ ሳየው ደስ ይለኛል። በነገራችን ላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለሁ ነው የሰራሁት። ትንሽ ቦታ ያለው ነገር ግን የማይረሳ “ካራከተር” በመሆኑ እወደዋለሁ። ከቴአትር አንፃር ደግሞ “የበዓል እንግዶች” ላይ የሰራሁት አጥናፉ የሚባለው ካራክተር እስረኛ ነው፤ 10 አመት ታስሮ የተፈታ ሰው ነው። እምወደውም በጣም የፈተነኝም ገፀ-ባህሪይ ነው። በዚህ ላይ ከማከበራቸው ከእነተስፋ ብርሃኔ፣ ሃና ተረፈ፣ ትዕግስት ግርማ፣ ሸዊት ከበደና ዮናስ ጌታቸው ጋር ነው የምሰራው፤ ሊሸፍነህ በሚችሉ ተዋንያን መካከል ሰርተህ መታየት በጣም መታደል ነው። በዚህ ላይ ገፀ-ባህሪይ በጣም ተወርቶለት ትዕይንት ሁለት ላይ ተጠብቆ የሚመጣ ነው። በአጋጣሚ ደግሞ እርሱን ካራክተር ሰለሞን ቦጋለ ነበር ሰራውን የጀመረው። ድንገት ለስራ ወደውጪ ሀገር ሲሄድ ነው እኔ የተተካሁት። ለሰለሞንን ካራክተር ወክዬ መጫወቱና ተቀባይነት ማግኘቱ ለኔ ፈተና ነበር። ነገር ግን የተመልካቹ ምላሽ ጥሩ ነው።
ሰንደቅ፡- እስካሁን አጋጣሚውን ያላገኘህው ነገር ግን አብሬው መድረክ ላይ ብተውን ደስ ይለኛል የምትለው ሰው ማነው?
አብዱልከሪም፡- ብዙ አሉ፤ ነገር ግን ሁሌ የማስበው ከአርቲስት አለማየሁ ታደሰ ጋር አብሬ መስራትን ነው። እርግጠኛ ነኝ አንድ ቀን በሆነ ስራ እንገናኛለን ብዬ አስባለሁ፡፤ በፊልም በኩል ግን አበበ ባልቻን፣ ሙሉአለም ታደሰን፣ ማክዳ አፈወርቅን እድሉ ቢገኝና አብሬያቸው ብሰራ ደስ ይለኛል።
ሰንደቅ፡- ከገፀ-ባህሪስ አንፃር የተለየ ልሞክረው እፈልጋለሁ የምትለው አይነት ገፀ-ባህሪይ አለ?
አብዱልከሪም፡- እስካሁን አሳዛኝ (ትራጂክ) የሆነ ገፀ-ባህሪይ አጋጥሞኝ አያውቅም፡፤ አሁን እንደሱ አይነት ብሰራ ደስ ይለኛል። እንዳልኩህ “የበዓል እንግዶች” ላይ ትንሽ የሚያሳዝን ገፀ-ባህሪይ ነው። ግን የበለጠ አሳዛኝ የሆነ ካራክተር ብሰራ ደስ ይለኛል።
ሰንደቅ፡- በቴአትር ስራህ የማትረሳውን አጋጣሚ ካለ አጫውተኝ?
አብዱልከሪም፡- የመድረክ ስራ በየሳምንቱ አንድ ነገር ሊያጋጥምህ ይችላል። ቃለ-ተውኔት ሊጠፋህ ይችላል። ወይ ድርጊት ሊጠፋህ ይችላል ወይም ደግሞ ዕቃ ረስተህ ወደመድረክ ልትገባ ትችላለህ። አንተም ባትሆን ጓደኛህ ሊሳሳት ይችላል። ብዙ ገጠመኞች አሉ። ግን እኔ ሁሌ የማልረሳውን አንድ አጋጣሚ ላጫውትህ። በአንድ ወቅት “ስውር ዕዳ” የተሰኘ ቴአትር ለማሳየት ወደክፍለሀገር ሄድን። ከዚያ አንድ በከተማዋ አለ የተባለ ሆቴል ውስጥ የማረፊያ ቦታ ያዝን እና ቴአትሩ በሚታይበት አዳራሽ መድረኩን ስንገጣጥም ዋልን። በጣም ርቦን ስለደከመን ምሳ እንብላ ተባባልንና ሁላችንም አለ ወደተባለው ሆቴል ገባን። ከፓስታ ወጪ ምንም የለም ተባልን። አማራጭ አልነበረንም፤ ይምጣልን ብለን መብላት ጀመርን። ፓስታው ለየት ያለ ነው፤ በዚህ ላይ ስጎው ሸንኩር በቃ እንደነገሩ ነበር። ሁሉም ርቦታል፤ መስራት አለበት። ቶሎ በልተን ወደአዳራሹ ሄደን። ተመልካች ገብቶ ስራው ተጀመረ። ይሄኔ የሁላችንም ሆድ በአንድ ጊዜ መጮኸ ጀመረ። ሁሉም “ሆዴን! ሆዴን”ይላል። ተመልካች እየጠበቀን ስለነበረ በቃ እንደምንም ስራው ይሰራ ብለን ጀመርነው።
ስራው ሲደመር መብራትና ድምፅ የሚራልን ልጅ አንድ ብቻ ነው። ቴአትሩ መታየት ቀጥሎ አንድ ሁለት ትዕይንቶች ከታዩ በኋላ የሆነ ግርማ የተባለው ጓደኛዬ የሚሞትበት ቦታ ደረስን፤ ገፀ-ባህሪው ተገደለ ከዚያ መብራት ይጠፋል ብለን ብንጠብቅ የለም። ብንጠብቅ መብራቱ አይጠፋም ሬሳው አይነሳ ነገር ህዝቡ እያየ ነው። ብዙ ሰዓት ቆምን፤ ለካ መብራትና ድምፁን የሚሰራው ልጅ በጣም አሞት ወደመፀዳጃ ቤት ሄዷል። ከኛ ጋር አብረው የሚሰሩት ተዋኒያን ተሯሩጠው ሄደው መብራቱን አጠፋልንና ከጉድ ወጣን እልሃለሁ።
ሰንደቅ፡- እስቲ ደግሞ “ብር አምባር” ላይ ስላለው ያንተ ገፀ-ባህሪይ እናውራ እንደተመልካች ስታየው ምኑ ይገርምሃል?
አብዱልከሪም፡- የሚገርም ገፀ -ባህሪይ ነው። እንዳየሀው ቤተሰቡም እርሱም ልጅ ይፈልጋሉ፡፤ ከተለያዩ ሰዎች እንዲሁም የኔ ሀኪም ነው ከሚለው ሰው በተደጋጋሚ ወሲብ እንዲፈፅም መክረውታል። እናምይህንን ለማድረግ ከስራ ቦታው የዓመት እረፍት ይወስናል። የሚገርመው ነገር ሚስቱ ደግሞ በጣም ስልችት ያለች ነች። ያ ግጭት ነው በተመልካቹ ዘንድ ሳቅን የሚያጭረው። ቤት ያቃታቸውን ነገር እስቲ ደግሞ ቦታ እንቀይር ብለው ሆቴል ይዘው ሁሉ እንሞክር ሲሉ ታያቸዋለህ። እርሱ ገፀ-ባህሪያ ብዙጊዜ በተለምዶም ስንሰማ ወሲብ የሚያዘወትሩ ሰዎች ቀጭን ነው ተብሎ ይታመናል። እናም የኔም ሰውነት እንደምታየው ስለሆነ ገና ብቅ ስል ሰው የሚስቀው። በኔ እና በባለቤቴ ፍላጎት አለመጣጣም ምክንያት ተመልካቹ ይስቃል። እኔ ገፀ-ባህሪውን ወድጄው ነው የምሰራው።
ሰንደቅ፡- ስለወደፊት ምን ለመስራት አስበሃል?
አብዱልከሪም፡- ወደፊት በትወናው እገፋበታለሁ። ቴያትሮችን ይዘን የመዞር ሀሳብ አለ። በተጨማሪ ደግሞ ፊልሞችን በመስራትና ፕሮዲዮስ ማድረግ እመርጣለሁ፤ ፈጣሪ ካለ። አመሰግናለሁ።የዛሬው እንግዳችን የጅማ ልጅ ነው። የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እዛው ተከታትሏል። የመጀመሪያ ዲግሪውን ለመስራትም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት  ትምህርት ክፍለ- ገብቷል። የማስተርስ ዲግሪውንም በዚሁ ክፍለ ትምህርት ውስጥ በማታው ጊዜ በመከታተል ላይ የሚገኘው ወጣቱ ተዋናይ፣ ዳይሬክተርና ፕሮዲዩሰር፤ አብዱልከሪም ጀማል። በአሁኑ ወቅት በአንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በተዋናይነት፣ በቴአትር ገምጋሚነትና በአዘጋጅነት እየሰራ ይገኛል። ተዋናይ አብዱል ከሪም ጀማል፤ ከተሳተፈባቸው ስራዎቹ መካከል ከቴአትር ረመጥ፣ የበዓል እንግዶችና ብር አምባር ሲጠቀሱለት፤ ከፊልም ደግሞ “ስርየት” እና “ኮመን ኮርስ” አይረሴዎቹ ናቸው። የአፍታ ቆይታችንን እነሆ በንባብ፤

አብዱልከሪም፡- ወደፊት በትወናው እገፋበታለሁ። ቴያትሮችን ይዘን የመዞር ሀሳብ አለ። በተጨማሪ ደግሞ ፊልሞችን በመስራትና ፕሮዲዮስ ማድረግ እመርጣለሁ፤ ፈጣሪ ካለ። አመሰግናለሁ፡

Last modified on Monday, 03 February 2014 16:53
ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
11727 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us