“አብሮ አደግ” ሰው ከነስህተቱ. . .

Wednesday, 08 February 2017 14:37

የቴአትሩ ርዕስ - “አብሮ አደግ”

ደራሲ       - ክላይድ ፊች

ትርጉም      - ዘካሪያ መሐመድ

አዘጋጅ       - ተስፋዬ ገ/ማርያም

ስቴጅማኔጀር   - ጌታቸው ስለሺ

ድራማተር     - እቴነሽ ካሳ

                   ተዋንያን    - ሽመልስ አበራ (ጆሮ)፣ እታፈራሁ መብራቱ፣ ትዕግስት ባዩ፣ ህንፀተ ታደሰ፣                  ፀጋዬ ብርሃኔ፣ ሔኖክ በርሁን፣ ራሄል ተሾመና ሽታዬ አብርሃ

“ሰዎችን የምንወዳቸው ፍፁም ስለሆኑ ሳይሆን ራሳቸውን ሲሆኑ ነው” ይላል የ“አብሮ አደግ” ቴአትር ዋና ባለታሪክ ታረቀኝ (ሽመልስ አበራ) ይህም በቴአትሩ ውስጥ እንደአብይ መልዕክትና ማሳረጊያ የሆነ ሃሳብ ነው ለማለት ያስደፍራል። የአብሮ አደጎችን ታሪክ፣ የአብሮ አደጎችን ገመና፣ የአብሮ አደጎችን ፍቅርና የአብሮ አደጎችን ግጭት የሚተርክ እና ዘወትር ቅዳሜ በ11፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በመታየት ላይ ያው “አብሮ አደግ”

የተንገዳገደን ትዳር ለመጠገንና ለማስታረቅ በሚል ሰበብ የራሳቸውን ድብቅ ግንኙነት የጀመሩት ባለትዳሮቹ አዲስ (እታፈራሁ መብራቱ) እና ሚስቱን ትቶ በአስታራቂው ፍቅር እፍ ክንፍ ያለው እስጢፋኖስ (ሔኖክ በሪሁን) የተመልካችን ስሜት በሚቆነጥጥ መልኩ የድብብቆሹን መጨረሻ ለማየት የሚያስመኝ ትወናን አሳይተዋል። በሚስቱ ላይ ፅኑ እምነት ያለው አቶ ታረቀኝ (ሽመልስ አበራ) “ያገባሽው ሰው ባንቺ ፅኑ እምነት ያለው ነው” እያለ ቢፎክርም፤ በሚያየውና በሚሰማው ነገር በፍቅሩ ላይ ያለው እምነት ሲፈተንና ግራ ሲገባው እንመለከታለን። በዚህም ላይ ባሏን በአስታራቂ ጓደኛዋ ሸፍጥ እንዳጣች ክፉኛ የምትጠረጥረው ማህሌት (ትዕግስት ባዩ) “ጠርጥር ከገንፎም ውስጥ አይጠፋም ስንጥር” እያለች በታረቀኝ እምነት ላይ የጥርጣሬ ነዳጅና እሳት ስትነሰንስበት እንመለከታለን። ለዚህ ሁሉ ትርምስ መንስኤ ተደርጋ የተቀመጠችው አዲስ (እታፈራው መብራቱ) ግን የማህሌትን ጥያቄና ጥርጣሬ ለማርከስ ይሁን ለማደስ አይታወቅም፤ “ሰው አናት ላይ ወጥቶ ፊጢጥ ከማለት ቀድሞ ነበር ባልን ጠበቅ አድርጎ መያዝ” ትላለች።

በሶስት ትዕይንቶች ተከፋፍሎ ለመድረክ የበቃው “አብሮ አደግ” ቴአትር የጓደኛን ብቻ ሳይሆን የቤተሰብንም ምስጢርና አስቂኝ የጥቅም ግንኙነት ማሳየት ችሏል። በቴአትሩ ውስጥ ብዙ አብረውን ያደጉ ነገሮች በኋለኛው ህይወታችን ውስጥ ያላቸውን ተጽዕኖ እንመለከታለን። ውሸት፣ አስመሳይነት፣ ለራስ ጥቅም ሲባል የሚደረጉ ሸፍጦችን ሁሉ እንመለከታን። . . . በአንጻሩ ደግሞ ከጥርጣሬ የፀዳ ፍቅርን፣ እምነትንና ቀና ጓደኝነትን ያሳየናል። እናም የ“አብሮ አደግ” ቴአትር ባለታሪኮች እነማን እንደሆኑ እንድናውቅ ገና በመጀመሪያው ትዕይንት ሃይማኖት (ራሄል ተሾመ) “ሁላችንም ጓደኛሞች ነን” ትላለች።

“አብሮ አደግ” ቴአትር ገና በመጀመሪያው ትዕይንት ቢያንስ አምስቱን ገጸ ባህሪያት በአካል እንድንተዋወቃቸው አድርጓል። ከዚህም ባለፈ የተመልካችን ስሜት መያዝ በሚችል መልኩ ታሪክ የሚጀምረው ባሌን ተቀምቻለሁ ብላ የምታስበው ማህሌት (ትዕግስት ባዩ) ጓደኛዬ ወደምትለው አዲስ (እታፈራሁ መብራቱ) ቤት መጥታ በምትከፍተው ዱላ ቀረሽ ግጭት መሆኑ ነው። ሰው ያለአንድ አመል አይፈጠርም እንዲሉ በፍቅር (በትዳር) ውስጥም ቢሆን ሰዎች ሰውን መውደድ ያለባቸው ፍፁም እንዲሆኑላቸው በመጠበቅ ሳይሆን፤ ራሳቸውን ሆነው እንዲቀርቧቸው በመፈለግ እንደሆነ ቴአትሩ በባለታሪኮቹ ግንኙነት ላይ ተመስርቶ ይተርክልናል።

አንጋፋና ወጣት ተዋንያን ተጣምረው የሰሩት “አብሮ አደግ” ቴአትር የገፀ-ባህሪያት አሳሳልም ሆነ የትወና ክፍተት እንደችግር የሚጠቀስበት አይደለም። የገፀ-ባህሪያቱ የአካልና የስሜት ውህደት ድንቅ ነው፡፡ በእንባ ጭምር ባለቤቷን ለማሳመን የምትጣጣረው አዲስ፤ ከሳቅ አውድ ወደለቅሶ የምትመጣበት ፍጥነት ይገርማል። በፍፁም ልቡ ሚስቱን የሚያምነው ባል (ሽመልስ አበራ) ድንገት የበደሉን ከፍታ አይቶ በውሸት ላይ ውሸት የምትደራርብበት ሚስቱን “ምናምን ውስጥ ስንት ምናምን አለ መሰለሽ” ሲል ቁጣውን የሚገልፅበት መንገድ ሌላው በቴአትሩ ውስጥ የተዋንያኑ የትወና ከፍታ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

በአብሮ አደጎቹ መካከል የተፈጠረው ችግር መፍትሄ እንዲያገኝና የተበተኑትም ትዳሮች ወደነበሩበት ይመለሱ ዘንድ የተፈጠረው የአዛውንቶቹ መላ (የአቶ በላይነህ እና የወ/ሮ ታጉ) መሆኑ ነው። አስቂኝነቱ እንደተጠበቀ ነው። ይሁን እንጂ በ“አብሮ አደግ” ቴአትር ውስጥ ለተመልካቹ ጥያቄን የሚያጭር ክስተት አልጠፋውም። ይህውም በመጨረሻው የቴአትሩ ትዕይንት ላይ ከመኝታ ክፍሏ ወጥታ በሳሎኑ መውጫ በኩል ከቤቷ የሄደችው አዲስ ድንገት ሳትታሰብ ባሏን ለማሳመን በተቀነባበረው የህመም ድራማ ውስጥ ለመሳተፍ የመጣችው ከመኝታ ቤቷ መሆኑ እንዴት ነው ነገሩ? የሚያሰኝ ነው።

በቴአትሩ ውስጥ የሰው ልጆች ታሪክ፣ ፍቅር፣ ቅናት፣ ጥላቻ፣ ተንኮልና ሴራ በይቅርታ ሲጋረዱ እንመለከታለን። የአንዱን ገመና አንዱ እየሸፈነ፤ የአንዱን ውሸት አንዱ እያሳመነ ከተመልካች ስሜት ጋር መቆየት የቻለ ስራ ነው ማለትም ያስደፍራል። በተረፈ ግን የአዳዲስ ቴአትሮች እጥረት እንዲህ ገኖ በሚታይበት በአሁኑ ወቅት “አብሮ አደግ” ቴአትርን የመሳሰሉ ዘመን አይሽሬ ስራዎች ተመልሰው የመታየት ዕድልን ቢያገኙ መልካም ነው ለማለት እንወዳለን። መልካም የመዝናኛ ሳምንት!!!

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
16034 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1080 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us