“ቼ በለው!” መፅሐፍ ተመረቀ

Wednesday, 16 August 2017 12:37

 

በደራሲ እዮብ ምህረትአብ ዮሐንስ የተፃፈው “ቼ በለው!” “የተሰኘ የኛ ዘመን ወሬዎችና ቀደዳዎች” የተሰነደበት መፅሐፍ ባሳለፍነው ሳምንት ተመርቆ፤ በስፋት በመነበብ ላይ ይገኛል። በማኅበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በሚያስነብባቸው ፅሁፎቹ የሚታወቀው እዮብ ምህረትአብ ዮሐንስ በመፅሐፉ ውስጥ ባቀረባቸው ፅሁፎች በአሽሟጣጭ መልኩ ማኅበራዊ ሂሶችን የሰነዘረባቸው ናቸው። ምክር፣ ምርቃት፣ አባትየው፣ አውደዓመት እና እኛ የተሰኙ ስራዎችን ጨምሮ አስራ ዘጠኝ አጫጭር ፅሁፎችን የያዘው “ቼ በለው!” የተሰኘው የደራሲው የበኩር መፅሐፍ በ179 ገጾች የቀረበ ሲሆን፤ ዋጋው 60 ብር እንደሆነም ተጠቅሷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
611 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us