“መሰናክልህን ውደደው” መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Wednesday, 11 October 2017 13:30

በሪያን ሆሊዴይ ተፅፎ በአካሉ ቢረዳ የተተረጐመው “መሰናክልህን ውደደው” የተሰኘ ሥነ-ልቦናዊ ይዘት ያለው መፅሐፍ ለንባብ በቃ። መከራን ወደጠቃሚነት የመለወጥን የጥንታዊያንን ታላላቅ ጥበቦች የሚያትተው ይህ መፅሐፍ፤ “የሚገጥመን መሰናክል ለበለጠ እርምጃ አነሳስቶ ለብቃት ያደርሳል። … ብዙ መከራን በፅናት የተሻገሩ ሰዎች ታሪክ በብዛት እንደሚገኝበትም ተርጓሚው በመግቢያቸው ይጠቁማል። “መሰናክልህን ውደደው” መፅሐፍ በሦስት ክፍሎች እና በበርካታ ንዑስ አርዕስቶች በዝርዝር ቀርቧል። መፅሐፉ በ200 ገጾች የተዘጋጀ ሲሆን፤ ባልተጠቀሰ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

ይምረጡ
(9 ሰዎች መርጠዋል)
792 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us