የዓይናለም “ዐይኖች” በዘይት ቀለም ላይ

Friday, 12 January 2018 16:51

 

በይርጋአበበ

ለ41 ዓመታት የሥዕል አስተማሪዋ ሠዓሊ ዓይናለም ገብረማርያም ለመጀመሪያ ጊዜ የግሏን የሥዕል አውደ-ርዕይ የፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ ሙዝየም ማሳየት ትጀምራለች። ከጥር 5 እስከ ጥር 25 ቀን 2010 ዓ.ም በሚቆየው ዐውደ ርዕይ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሠዓሊዋ ለሰንደቅ ጋዜጣ አስተያየቷን ሰጥታለች። የሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ አድናቂ እንደሆነች የገለፀችው ሠዓሊ ዓይናለም ለሰንደቅ ጋዜጣ የሰጠችውን ቃለ ምልልስ ከዚህ በታች አቅርበነዋል። የሁለት ልጆች እናት እና አምስት የልጅ ልጆች ያሏት አርቲስት ዓይናለም፤ አንቱታውን ትተን አንቺ ብለን እንድንጠራት ስለፈቀደችልን “አንቺ” እያልን መጥራቱን መርጠናል።

ትውልድናእድገት

አርቲስት ዓይናለም የክብር ዘበኛ ወታደር አባል ከሆኑት አባቷ በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ መኮንኖች መንደር ነው የተወለደችው። ፊደልን ከግል የቄስ ትምህርት አስተማሪዋ አንደበት መማር የጀመረች ሲሆን፤ ከአንደኛ ደረጃ እስከ 12 ክፍል ያለውን ትምህርት የተከታተለችው በእቴጌ መነን ትምህርት ቤት ነው።

12 ክፍል በኋላ ያለውን ጊዜ ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኪነ-ጥበባት /ቤት (Art School) ለአምስት ዓመታት ተከታትላለች። ለሁለት ዓመታት ደግሞ እድገት በኅብረት ዘመቻ ተሳትፋ አገራዊ ግዴታዋን ተወጥታለች። ከፍተኛ ትምህርቷን ለአምሥት ዓመታት ተከታትላ ከተመረቀች በኋላም በደብረዘይት ሁለተኛ ደረጃ /ቤት የሥዕል አስተማሪ ሆና አገሯን አገልግላለች።

ጉዞወደሥዕል

ሥዕልን ከመጀመሯ በፊት ሳታውቀው ፍላጐቷ በውስጧ እንደነበረ የምትናገረው አርቲስት ዓይናለም ከልጅነቷ ጀምሮ ለሰፈር እኩዮቿ የተለያዩ ሥዕሎችን እየሳለች ችሎታዋን አሳደገች። ከዚህ በተጨማሪም የትምህርት ቤት ጓደኞቿ በአስተማሪዎቻቸው የሚሰጣቸውን የሥዕል የቤት ሥራ ሁሉ እየሳለች ትተባበራቸው እንደነበር ተናግራለች። በዚያ የልጅነት የት/ቤት ቆይታዋ ከተባበረቻቸው የትምህርት ቤት ጓደኞቿ መካከል አንዷ ከረጅም ዓመታት በኋላ አግኝታ የነገረቻትን ስትገልጽም፤እኔ የረሳኋት የትምህርት ቤታችን ተማሪ የነበረች ሴት መንገድ ላይ አግኝታኝ፤አንቺ በሰጠሽኝ ሥዕል ከክፍል አንደኛ ወጥቻለሁ። ይህን ውለታሽን መቼም አልረሳውምስትል ነገረችንትላለች ሠዓሊ ዓይናለም ገብረማርያም።

ቀደም ብሎ እንደተገለፀው ሠዓሊ ዓይናለም የሥዕል ችሎታዋን በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ገብታ ማሳደግ የቻለችበትን አጋጣሚ ስታስታውስ ደግሞአሁን ጣሊያን አገር የምትገኝ እጅጋየሁ ተስፋዬ የምትባል ጓደኛዬ ጋር ክረምቱን ለማሳለፍ ወደ አርት ስኩል (... ኪነ-ጥበብ /ቤት) ገብተን ተማርን። ትምህርቱን ተከታትለን ስንጨርስ የተሰጠንን ፈተና በብቃት ስላለፍን ውጤታችንን ሊሰጡን አልቻሉም። ምክንያቱም በዚያው ገፍተንበት እንድንማር ነውበማለት ተናግራለች። አጋጣሚ ደግሞ የሥዕል ችሎታዋን ከማሳደጉም በላይ እሷን መሰል ሠዓሊያንን እንድታፈራ መንገድ ከፍቶላታል።

ሥዕልለአርቲስትዓይናለም

ጥበብ መንፈስ ነውየምትለው አርቲስት ዓይናለም፤ ከአስተማሪነት ሙያዋ ወጥታ በሌላ የመንግሥት ሥራ ስትሰራ የቆየች ሲሆን 15 ዓመት ወዲህ ግን ሌሎች ሥራዎችን ሙሉ በሙሉ በመተውየሙሉ ጊዜ ሠዓሊ ወይም ስቱዲዮ አርቲስትመሆኗን ትናገራለች። የሥዕል ስራ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ላለ አገር ፈታኝ ሲሆን በተለይ ሁሉም የሥዕል መሳያ ግብአቶች ከውጭ አገር የሚመጡ በመሆናቸው ዋጋቸው የሚቀመስ አይደለም። ወደ ኢትዮጵያም ቢሆን ግብአቶቹን የሚያስመጣ ድርጅት የለም። ይህ መሆኑ ደግሞ የግብአቶቹ ዋጋ ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ እንደልብ የሚገኙ አይደሉም። በዚህ የተነሳ የሥቱዲዮ አርቲስት መሆን ያዋጣል ወይ? ተብላ የተጠየቀችው ሠዓሊዋ ስትመልስ፤ሥዕል ለዳቦ አይሆንም። ቤት አስተዳድርበታለሁ የምትለውም አይደለም። ነገር ግን ውስጥህ ስለሚታገልህ ያንን ለማሸነፍ የምትሰራው ሥራ ነው። ምክንያቱም ቅርስ ማቆየት አለብህ። የምታየውን፣ የምትሰማውንና የምታነበውን ሁሉ በሥዕል ማስቀመጥ አለብህ። ይህ ደግሞ የሙያ ግዴታ ነው አይለቅህም። እኛን የሚያስረንም (ሙያውን እንድንሰራው የሚያደርገን) እሱ ነው። አባቶቻችን አያቶቻችን ለአገራቸውና ለቤተክርስቲያን ዘመን አይሽሬ ውለታዎችን በሥዕል ሲያበረክቱ ቤሳቤስቲን አልተከፈላቸውም። ሲያልፉም ደልቷቸው ሳይሆን ተቸግረው ነውበማለት ሥዕል ለእሷ ያለውን ትርጉም ተናግራለች።

ሥዕልእናሴትነት

በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የሴት ልጅ የሥራ ድርሻ ከወንዱ የበለጠ ነው። ከተፈጥሯዊ ጫናው (መውለድ፣ ማጥባት…) በተጨማሪ ባህላችን ራሱ በሴቶች ላይ ዱላውን ሲያበረታ ምህረት አልባ ነው።

የሥዕል ሙያ ደግሞ ከፍተኛ ትኩረት (Concentration) የሚፈልግ ሙያ ነው። ሰዓሊ ዓይናለም /ማርያም ባለ ትዳርና የሁለት ልጆች እናት መሆኗን ከግምት በማስገባት ሴትነትና ሠዓሊነት በእሷ በኩል እንዴት እንደሚስተናገዱ ጠይቀናት ነበር። በጣም ፈተና እንደሆነ የምትናገረው አርቲስቷ፤ እሷ ወደ ዩኒቨርስቲ ገብታ የሥዕል ትምህርት በምትማርበት ወቅት ከቤተሰብ በተለይ ከአባቷ እና ከማኅበረሰቡ የገጠማት ተቃርኖ ከፍተኛ እንደነበረ ተናግራለች። ነገር ግን እንደ ሠዓሊ ሐጎስ ደስታ ያሉ ጠንካራ ሴት ሠዓሊያን ሞራል እንደሆነቻት ገልፃ በተለይ በትምህርቷ የመጨረሻ ዓመት ላይ አማካሪ (Advisor) የነበሩት የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ሥራዎቻቸው ሞራል እንደሆኗት ተናግራለች። በቤት ውስጥ ያለውን የሴትነት ፈተና ለማለፍም ቤተሰቦቿ (ባለቤቷ እና ልጆቿ) ሙያዋን አክብረው እንዳበረታቷት ገልፃለች። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ደጋፊዎች ከጐኗ ባይኖሩ ኖሮ እሷም እንደ ብዙሃኑ ሴቶች በጅምር ትቀር እንደነበር አፅንኦት ሰጥታ ተናግራለች።

የሥዕልዋጋመናር

ተፈጥሯዊ (Realistic) የተባለውን የሥዕል ዘዴ በዘይት ቀለም አሳሳል መንገድ በመሳል ከጓደኞቿ ጋር ሰባት የሥዕል አውደ ርዕዮች ያካሄደችው አርቲስት ዓይናለም፤ የሥዕል ዋጋ ኢትዮጵያ ውስጥ ተገቢ ዋጋውን እያገኘ እንዳልሆነ ትናገራለች። በዓለም ላይ በሚሊየን ዶላር የሚቆጠር ዋጋ ያላቸው ሥዕሎች መኖራቸውን ገልፃ፤ በኢትዮጵያ ግን ዋጋቸው አነስተኛ ሊባል እንደሚችል ተናግራለች። ሆኖም ከሕዝቡ የመግዛት አቅም ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ሊባል የሚችል እንደሆነ የምታምን ሲሆን፤ ለዚህ ያበቃው ደግሞ አገሪቱ ውስጥ ሥዕልን ለማበረታታት የፖሊሲ ድጋፍ አለመኖሩ እንደሆነ ገልፃለች።

በማኅበር ደረጃ ጥረት የተደረገ ቢሆንም፤ እስካሁን መፍትሔ አልተገኘምበማለት ተናግራለች። እሷ የምትስላቸውን ሥዕሎች ዋጋ ስትገልፅም የግራፊክስ ሥዕሎቿ ዝቅተኞቹ ከሦስት ሺህ ብር ጀምሮ እንደሆነ እንዲሁም የዘይት ቀለም ሥዕሎቿ 8,300 ብር ጀምሮ እንደሆነ አሳውቃለች። ይህ ገንዘብም ተጨማሪ ሥዕሎችን ለማሳል ገቢ እንዲሆናት እንጂ አትራፊ እንዳልሆነ ነው የተናገረችው።

የዓይናለምፊተኛእናኋለኛ

እንደማንኛውም ሠዓሊ (የጥበብ ሰው) ከእሷ በፊት የነበሩትን ባለሙያዎች (ሠዓሊያን) ሥራ በተመለከተ ስትናገር፤አባቶቻችን በዋሻ እና በቤተክርስቲያን የሳሏቸው ዘመን ተሻጋሪ ሥዕሎች ይማርኩኛል። ሥዕል ዘመን ተሻጋሪ ቢሆንም፤ እንደየዘመኑ የሚቀያየር በመሆኑ ከእኛ በፊት የነበሩ ሥዕሎች በብዛት ትኩረት ያደርጉ የነበረው የሰው ሥዕሎች (ፖርትሬይት) ነበርትላለች። በግለሰብ ደረጃ ደግሞ የሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ አድናቂ መሆኗን ተናግራለች።

ከእሷ በኋላ ስለመጡት የዘመኑ ሠዓሊያን ሥትናገርምወጣቱ ሥዕልን ከቴክኖሎጂ ጋር አዋህዶታል። ጥሩ ስራ እየሰሩ ነው። ነገር ግን የልጆቹን የፈጠራ ችሎታ እንዳይጎዳው ያሰጋኛል። ምክንያቱም በቴክኖሎጂ ላይ ጥገኛ በሆኑ ቁጥር ወደፊት ይፈታተናቸዋል። ከዚያ ውጭ ግን የሥዕል ችሎታቸው እጅግ በጣም ማራኪ ነውበማለት የሁለቱን ዘመን ሠዓሊያን ልዩነት አነፃፅራለች።

ሠዓሊ ዓይናለም የሙሉ ጊዜ ሠዓሊ ሆና ሙሉ ጊዜዋን የምታሳልፈው በተለምዶ ጃፓን ኮንደሚኒየም በሚባለው ሠፈር ከሚገኘው የሥዕል ቦታዋ ሲሆን፤ታሪክን ተፈጥሯዊ በሆነ የአሳሳል ጥበብ ለትውልድ አስተላልፋለሁስትል ትገልፃለች። የፊታችን ቅዳሜ የሚከፈተውን የሥዕል አውደ-ርዕይ በተመለከተ ስትናገርም፤ የሥዕል አውደ-ርዕዩን በክብር እንግድነት ተገኝተው የሚከፍቱት ተማሪዎቼ ናቸው ስትል ትናገራለች። ከዚህ ውሳኔ የደረሳቸው ደግሞ በእሷ ሥር ቀለምንና ብሩሽን ማዋሃድ የጀመሩ ተማሪዎቿ ስኬት ስለማረካት እንደሆነ ገልፃ፤ ተማሪዎቿም የእሷን ፈለግ እንዲከተሉ ለማሳሰብ ጭምርም ነው።              

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
15667 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 892 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us