“አንድ ቀን ብዙ ነገር ማለት ነው”“አንድ ቀን ብዙ ነገር ማለት ነው”

Wednesday, 07 May 2014 13:35

ተዋናይት ሜላት ነብዩ

ወጣት የፊልም ባለሙያ ናት። የመጀመሪያ የፊልም ስራዋ የሆነው “ቀዮ” የተሰኘውን ፊልም ተከትሎ ከበርካቶች ጋር ያስተዋወቃትን “ስሌት” ፊልም ሰርታለች። በመቀጠልም “የማትበላ ወፍ” እና “8ኛውሺ” ፊልሞች በትወና የተሳተፈችባቸው ናቸው። በቅርቡ ደግሞ በድርሰት፣ በረዳት ዳይሬክተርነትና፣ በፕሮዲዩሰርነት በትወና የተሳተፈችበትን “አንድ ቀን” የተሰኘ ፊልም ይዛ መጥታለች። ተዋናይት ሜላት ነብዩ፤ የዛሬዋ የመዝናኛ አምድ እንግዳችን አድርገናታል። መልካም ቆይታ፤

ሰንደቅ፡- በዚህ ሳምንት ለዕይታ ከሚበቃው ፊልምሽ እንነሳ። “አንድ ቀን” በተሰኘው ፊልም ውስጥ አራት የስራ ዘርፎችን ደራርበሽ ሰርተሻል፤ አይከብድም?

ሜላት፡- እውነቱን ለመናገር ቀላል የሚባል ነገር አይደለም። የፊልሙ ፀሐፊ እኔ ነኝ፤ ረዳት ዳይሬክት ነኝ፤ ለፕሮዲዩሰርና በትወናው ላይም ነበርኩ። በጣም ከባድ ነበር መጀመሪያ እንዳሰብኩት አይደለም። ባወጣሁት የጊዜ እቅድ መሰረት ይጠናቀቃል ብዬ ነበር። ነገር ግን በጣም ከባድ ነገሮች አሉበት። አክተሮቹን በጊዜው ላታገኝ ትችላለህ፤ ካሜራ ማን አለ። ጉዞ ይበዛ ነበር። ይህን ሁሉ ጠብቀህ ነው የምትሰራው ለኔ እንደመጀመሪያዬ በጣም ይከብዳል።

ሰንደቅ፡- ድርሰቱን በምን አይነት መነቃቃት ውስጥ ሆነሽ ነው የፃፍሽው?

ሜላት፡- ታሪኩን የፃፍኩት ትዝ ይለኛል በሆሳዕና ዕለት ነው። በፊልሙ ውስጥም በጥቂቱ ታይቷል። ላስታውስህ የምወደው ነገር እኔ ከዚህ ፊልም ፅሁፍ በፊትም አጫጭር ፅሁፎችን እሰራ ነበር። ግጥም እፅፋለሁ፤ ስዕልም እሞካክራለሁ። ይህን ፊልም ለመፃፍ ያነሳሳኝ ግን በወቅቱ ዕለተ ሆሳዕናን አክብሬ ስመለስ ስለሆሳህና ትንሽ ነገር መፃፍ ፈለኩና ጀመርኩት ድንገት ግን ታሪኩ አቅጣጫውን ለውጦ በፊልሙ እንዳየኸው አይነት መልክ ይዞ ወጣ ማለት ነው።

ሰንደቅ፡- በፊልሙ ውስጥ ስለተጫወትሻቸው ገፀ-ባህሪያት እስቲ እያነፃፀርሽ ንገሪኝ?

ሜላት፡- አብሳላት ጠንካራ ሴት ናት። አላማዋን ለማሳካት አስመስላና ችላ መኖር የምታውቅበት ዓይነት ሴት ናት። አንዳንዴ ታሪኩን ስፅፈው ከኔ ስብዕና ጋር የሚያመሳስላትም ቦታ አላት። በተቃራኒው ደግሞ ብርሃን በጣም መልካምና ስሱ የሆነች ገፀ-ባህሪይ ናት ማለት እችላለሁ። ስተውናቸው ሁለት የማመሳሰል ባህሪ ያላቸውን ሰዎች መስሎ መተወኑ በጣም ከባድ ነበር። ግን ከፈጣሪ ጋር ተወጥቼዋለሁ ብዬ አምናለሁ።

ሰንደቅ፡- የፊልሙ ርዕስ “አንድ ቀን” ነው። እስቲ አንድ ቀን በሰው ልጅ ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ተፅዕኖ አጫውቺኝ?

ሜላት፡- አዎ! አንድ ቀን በሰዎች ላይ ያለው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም። አንድ ቀን ማለት ትናንት ነው፤ ዛሬ ነው፤ ነገም ሲመጣ አንድ ቀን ነው። አንድ ቀንን ተስፋ ታደርገዋለህ ወይም ታሪክ ታደርገዋለህ። አንድ ቀንን ደግሞ ዛሬህን ትኖርበታለህ። “አንድ ቀን” ብዙ ነገር ማለት ነው ለኔ።

ሰንደቅ፡- የአንድ ቀን ስልጣን ቢኖርሽ ብለን እናስብና ምን ታደርጊ ነበር?

ሜላት፡- (ሳቅ) የአንድ ቀን ስልጣን ቢሰጠኝ የመጀመሪያ ተግባሬ የሚሆነው ጧሪና ደጋፊ ያጡ አረጋውያንን መሰብሰብና መደገፍ ነው። ሌላው በአንድ ቀን የሚቻል ከሆነ ችግር የሚባለውን ነገር ማጥፋት ብችል ደስ ይለኛል።

ሰንደቅ፡- መልካም፤ የአንድ ቀን ህይወት ብቻ ቢሰጥሽስ፤ ማለትም ያለሽ ቀን ዛሬ ብቻ ቢሆንና ነገ ትሞቻለሽ ብትባይስ?

ሜላት፡- (ሳቅ) ንሰሃ የምገባና ቤተሰቦቼን ሰብስቤ አብሬ መቆየትን የምመርጥ ይመስለኛል። ጥያቄው ግን ቀላ ይመስላል እንጂ ከባድ ነው።

ሰንደቅ፡- መልካም እስቲ ደግሞ ከአንድ ቀን ወጣ ብለን እስካሁን ከሰራሻቸው ፊልሞች ውስጥ ስለማትረሻት ገፀ-ባህሪይ ንገሪኝ?

ሜላት፡- እውነቱን ለመናገር “ስሌት” ፊልም ላይ ያለችውን ገፀ-ባህሪይ አሁን ድረስ አልረሳትም፤ ደስም ትለኛለች። “እፀጳጦስ” ትባላለች፤ ከነስሟ ልዩ ገፀ- ባህሪ ነበረች። በዚህ አጋጣሚ “እፀጳጦስ” ማለት በመፅሀፍ ቅዱስ እደተገለጠው “የማትቃጠል ዕፅ” ማለት ነው። እሳት ውስጥ ገብታም ቢሆን አትቃጠልም። ሙሴ ማርያምን “ዕፀጳጦስ” ብሏታል፤ የመከራዋን ብዛት አይቶ ማለት ነው። በስሌት ፊልም ውስጥ ያለችው ዕፀጳጦስ ግን ሴተኛ አዳሪ ሆና በትምህርቷም ሆነ በህይወቷ ጠንክራ መውጣት የቻለች ገፀ-ባህሪይ ናት። እና ይህቺህ ገፀ-ባህሪይ አሁን ድረስ በጣም ነው የምወዳት። ባይገርም “ስሌት” ፊልምን በሲኒማ ቤት ተገኝቼ ከ10 ጊዜ በላይ አይቼዋለሁ።

ሰንደቅ፡- እስቲ ደግሞ ወደመጀመሪያ ስራሽ ልመልስሽ፤ እንደጀማሪ ካሜራ ፊት ስትቆሚና ፊልሙ ተሰርቶ ሲኒማ ውስጥ ስታይው የተሰማሽን ስሜት ታስታውሽዋለሽ?

ሜላት፡- አዎ! የመጀመሪያ ስራዬ “ቀዮ” ነው። እዛ ፊልም ላይ የተጫወትኳት ገፀ-ባህሪይ ጨዋ ነርስ ናት። የሚገርመው ነገር የመጀመሪያዬ ስለሆነ ነው መሰለኝ አንድ የማልረሳው ነገር፤ ልክ ካሜራ ፊቴ ሲደቀን ያልበኝ ነበር። አስሬ እየቋረጠ በፓውደር እየታበስኩ ነው ፊልሙን ሰርቼ የጨረስኩት ማለት ይቻላል። የሚያዝናናው ነገር ደግሞ ፊልሙ ተጠናቆ በሲኒማ ሲታይም ፊልሙን እያየውት እኔን ያልበኝ ነበር (ሳቅ) . . . ጭንቀቴ ሰው ይወደው ይሆን ወይ? የሚል ነበር። እንደፈራውት አይደለም፤ ጥሩ ምላሽ ነበረው። ከዚያ በኋላ “ስሌት”ን ስሰራ ነው የካሜራ ፍርሃቴን የገፈፈልኝ ማለት እችላለሁ።

ሰንደቅ፡- አንቺ ገና ብዙ የሚጠበቅብሽ ወጣት ተዋናይት ነሽ። ወደፊት ግን ከአንጋፎቹ ጋር ከማን ጋር መስራትን ታልሚያለሽ?

ሜላት፡- በጣም የምወደው ተዋናይ አለ፤ ፍቃዱ ተ/ማርያም ከእርሱ ጋር የምሰራበት አጋጣሚ ቢኖር በጣም ነው ደስ የሚለኝ። በተጨማሪ ደግሞ ከአለማየሁ ታደሰ ጋር መስራት እፈልጋለሁ። ከእነዚህ አንጋፋ ተዋንያን ጋር ብሰራ ብዙ ነገር አተርፋለሁ ብዬ አስባለሁ።

ሰንደቅ፡- በተለየ ብሰራው ብለሽ የምትመኚው ገፀ-ባህሪስ አለ?

ሜላት፡- ባይገርምህ እስካሁን ያልሰራሁት የሃይለኛና ነገረኛ ሴት ገፀ-ባህሪይን ነው፤ ብሞክረው ደስ ይለኛል። የሰራኋቸው ገፀ-ባህሪያት ሁሉ ስርዓት ያላቸው፤ አፍቃሪዎችን የሚወክሉ ናቸው። እና ለየት ያለች ገፀ-ባህሪን ብሞክር ደስ ይለኛል።

ሰንደቅ፡- ወደ “አንድ ቀን” ፊልም ልመልስሽና የፊልሙ “ፖስተር” ተደጋግመው ከሚታዩት ለየት ያለ ነው እንዴት መረጥሽው?

ሜላት፡- በዚህ የፊልም “ፖስተር” ላይ ብዙ ሰዎች ተከራክረውበታል። አንዳንዶቹ ለምን የአርቲስቶቹን ምስል አልደረደርሽም ብለውኛል። ለምን አታጯጩሂም ያሉኝም ነበሩ። እኔ ግን የፊልም ፖስተር ከታሪኩ ጋር የሚገናኝ ነገር መያዝ አለበት ብዬ ስለማምን ይሄኛውን አይነት ግማሽ ጨለማ ግማሹ ደግሞ የሴት ምስልን የያዘ ፖስተር መርጫለሁ። ፖስተሩ ለምን እንደዛ ሆነ የሚል ካለ ፊልሙን አይቶ መረዳት ይችላል። የልጅቷን መከራና ስኬት ያሳያል። በዚህ ላይ “አንድ ቀን” የሚለው ነገር ብርሃንና ጭለማን ያካተተ ስለሆነ ነው የመረጥኩት።

ሰንደቅ፡- የመዝናኛ እንግዳችን አዘውትሬ የምጠይቃቸው ጥያቄ ልጠይቅሽ አንቺ ለፊልም ተመልካቹ የመዝናኛ ምንጭ እንደሆንሽ ሁሉ አንቺስ ምንድነው የሚያዝናናሽ?

ሜላት፡- እኔንም ፊልም ማየት ነው በጣም የሚያዝናናኝ። ኤድናሞል ለሰፈሬ ቅርብ ስለሆነ አዘውትሬ ከዚያ አልጠፋም። በተረፈ ደግሞ መፅሀፍትን አነባለሁ።

ሰንደቅ፡- ከባለሙያነትሽ በተጨማሪ ይሄን ያህል ፊልም ተመልካች ከሆነሽ እንዴት ነው የአገራችን የፊልም ሁኔታ ባንቺ አተያይ?

ሜላት፡- ስለኢትዮጵያ ፊልሞች ለመናገር በጣም እድገት እያሳዩ ነው ማለት እችላለሁ። በካሜራ ብትል፤ በዳይሬክቲንግና በኤዲቲንግም ቢሆን ጥሩ ጥሩ ባለሙያዎች እየታዩ ነው። በደፈናው ታሪኮቹ ሁሉም ጥሩ ናቸው ባይባልም አልፎ - አልፎ የሚጠቀሱ ስራዎች አሉ። ለምሳሌ በቅረቡ ከወጣው “ረቡኒ” በጣም ቆንጂ ፊልም ነው። ከዚያ በፊት ደግሞ ያየሁት “እቴጌ-2” እና “ሼፉ” እያዝናኑ የሚያስተምሩ ቆንጆ ፊልሞች ናቸው። እስካሁን ከብዛት አንፃር እድገቱ በጣም ጥሩ ነው። ከዚህ በኋላ ደግሞ ተባብረን የተሻለ እናደርገዋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

ሰንደቅ፡- ከ“አንድ ቀን” ፊልምሽ በኋላስ በቅርቡ ካንቺ ምን እንጠብቅ?

ሜላት፡- በድርሰት ትንሽ ልረፍበት (ሳቅ) ከዓመት በኋላ የራሴን ስራ ይዤ እመጣለሁ። ከዚያ በፊት ግን ሁለት በትወና የተሳተፍኩባቸውና ፕሮዳክሽናቸው የተጠናቀቁ ፊልሞች ይወጣሉ ብዬ እጠብቃለሁ። “ዛየን” የሚልና “ታስጨርሽኛለሽ-2” ይሰኛል ርዕሳቸው።

ሰንደቅ፡- እንደተዋናይ ፊልም ስትሰሪ በቂ ክፍያ ተከፍሎኛል ትያለሽ?

ሜላት፡- ያው በአገራችን እነደሚታወቀው ነው፤ ክፍያው በቂ የምንለው ሳይሆን ጥሩ ነው ብለህ አልፈህው በስራው መርካትን መምረጡ ይሻላል መሰለኝ።

ሰንደቅ፡- አሁን አንቺ ፕሮዲዩሰርም ሆነሻል፤ አብረውሽ ለተወኑት በቂ የሚባል ክፈያ ከፍለሻል?

ሜላት፡- (ሳቅ) እርሱንማ እነሱን ብትጠይቃቸው ይሻላል። እንደኔ ግን አዎ ነው መልሴ።

ሰንደቅ፡- ለራስሽስ ምን ያህል ከፈልሽ?

ሜላት፡- በጣም ነው የከፈልኩት ያው ግን በብር ሳይሆን በልፋት ማለት ነው (ሳቅ)

ሰንደቅ፡- ከመሰነባበታችን በፊት ስለ “አንድ ቀን” ፊልም አንድ የመጨረሻ ነገር በይን?

ሜላት፡- ያው “አንድ ቀን” ፊልም አንድ ቀን ተፅፏል፤ አንድ ቀን ተመርቋል፤ እናንተም አንድ ቀን መጥታችሁ ብታዩት በጣም ደስ ይለኛል (ሳቅ). . . በጣም አመሰግናለሁ።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
11861 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us