Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 391

ጄኦተርማል ሌላው ታዳሽ የኃይል ምንጭ

Wednesday, 13 November 2013 13:01

የኢትዮጵያ መንግስት የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት መርህን ዕቅድ አውጥቶ መተግበር ከጀመረ አንድ ዓመት አልፏል። ዕቅዱ በCOP ሀገሮች ተቀባይነት ከማግኘቱ በሻገር ለጋሽ ሀገሮችም ተገቢውን ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብተዋል። ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ምቹ ሁኔታን ሊፈጥሩ ከሚችሉ በርካታ ስልቶች መካከል አንደኛው የኢነርጂው ሴክተር በታዳሽ ኃይል እንዲመራ ማድረግ ነው። ባለፉት አስር ዓመታትም በርካታ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫዎች ተገንብተው ወደ ስራ ገብተዋል። የፀሐይና የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችም በመጠኑም ቢሆን ተገንብተው ኃይል እያመነጩ ነው። ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ በተትረፈረፈ መልኩ እንደሚገኝ የሚጠቀሰው የጂኦተርማል ኃይል ምንጭ ይገኝበታል። እንደሙያተኞች ገለፃ ይህ ዘርፍ በተለይ ምስራቅ አፍሪካን ለሁለት ከፍሎ በሚያልፈው የስምጥ ሸለቆ ውስጥ በብዛት እንዳለ ይገለፃል። ከዚህ አኳያ በተለይ በደቡብ ክልል ርዕሰ ከተማ በግምት 30 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው የአርቤቲ የጂኦተርማል ጣቢያ በጉልህነቱ የታወቀ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜም ዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን፣ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦንና የኢትዮጵያ መንግስትንና የሀገር ውስጥ ባለሙያዎችን በአንድ ላይ ማሰባሰብ የቻለ እና ወደ ስራ የተገባበት አካባቢ ነው።

በቅርቡም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምን ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች በተገኙበት በኒውዮርክ ከተማ በመንግስትና በሬክየቪክ የጂኦ ተርማል ኩባንያ አማካኝነት ቁፈራው እየተካሄደ የሚገኘውን የከርቤቲ ጂኦተርማል ጣቢያን በስፋት ለማልማት የመግባቢያ ሰነድ ሊፈርም በቅቷል። ፕሮጀክቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ በግል የጂኦተርማል ኩባንያ እንዲለማ በመደረጉ በሀገራችን ታሪክ ግንባር ቀደም ነው። በፕሮጀክቱ እስከ 1000 ሜጋዋት የኃይል እንዲመነጭ ይደረጋል። አካሄዱና አመራረቱም በሁለት እያንዳንዳቸው 500 ሜጋዋት በሚያመነጩ ግንባታዎች የሚከናወን ነው። ይህ የጂኦተርማል ታዳሽ ኃይል ማመንጫም በአፍሪካ በትልቅነቱ የመጀመሪያው ነው። ግንባታው 4 ቢሊዮን ዶላር የሚፈጅ ሲሆን የመጠናቀቂያ ጊዜው ከ8 እስከ 10 ዓመት እንደሚፈጅ በቅርቡ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጽህፈት ቤት አመልክቷል። የሌኪያቪክ ኩባንያ በአሜሪካውያንና በአይስላንድ ዜጎች ሽርክና የተቋቋመ ሲሆን ቀደም ሲል የኮርቤቲን አካባቢ የጎበኙ የአሜሪካ የአይስላንድ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጂኦ ሳይንቲስቶች እንዲመለከቱት በቦታው የተትረፈረፉ የእንፋሎት ክምችት እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የከርቤቲ ፕሮጀክት ወደ ስራ ከተገባበት ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም አምና ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ አፍሪካን በታዳሽ ኃይል አቅርቦት ለመደገፍ በሚል ያቋቋሙት የፓወር አፍሪካ ዕቅድ አካል ለመሆን በቅቷል። በዚህ ዕቅድ ለ6 የተመረጡ ከሰሃራ በታች ለሚገኙ የአፍሪካ ሀገሮች እስከ 10ሺህ ሜጋዋት የሚደርስ ታዳሽ ኃይል ለማቅረብ ጥረት ያደርጋል። ፓወር አፍሪካ ካካተታቸው የአፍሪካ ሀገሮች መካል በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያና ኬንያ የሚጠቀሱ ናቸው። በአካባቢው የተትረፈረፈ የጆኦተርማል ኃይል እንደሚገኝ ተረጋግጧል። ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገሮች የኃይድሮ ኤሌትሪክ ኃይል ብቻ ሳይሆን የጆኦተርማል ኃይል ለማቀረብ ዕቅድ ያላት ሲሆን ለዚህ እንዲያግዝም ሁለቱ ሀገሮች ኃይል አቅርቦት እንዲያግዝ የ25 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ፈንድ ማግኘታቸው በቅርቡ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ባለስልጣን ማስታወቁ የሚዘነጋ አይደለም።

የከርቤቱ አካባቢ የጂኦተርማል ጣቢያ በቅድሚያ እገዛው የተገኘው በአሜሪካው ዓለም አቀፍ ርዳታ USAID አማካኝነት ሲሆን ይህም በአካባቢው ታላላቅ የኃይል ማመንጫ ግንባታዎችን ማካሄድ እንደሚቻል ምሳሌ ለመሆን በቅቷል። ፕሮጀክቱ እንደ ሬኪያሺክ ባሉ የግል ተቋማትና በአሜሪካ መንግስት ኢንቨስትሜንት የሚተገበር ሲሆን ፕሮጀክቱም ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ከወዲሁ ለመቅረፍ በሚያስችል መልኩ የተቀረፀ ነው። የሀገር ውስጥ የግንባታ አቅምንም ያጠናክራል የአሜሪካ አለም አቀፍ ርዳታ ፕሮጀክቱን በተመለከተ የሰጠው አገልግሎት በኢትዮጵያ መንግስትና በሬክየቪክ የጆኦተርማል ኩባንያ መካል የቁፋሮች የግንባታ ስራ ውል ተፈፅሞ ወደ ስራ እንዲገባ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል። ፕሮጀክቱ ችግር ወይም risk ቢገጥመው ይህን ለማስወገድ የገንዘብ ድጋፍ የሚሰጠው KFW የተባለ ድርጅት ሲሆን የአፍሪካ ህብረትም ለአሰሳውና ለቁፋሮ የበኩሉን ድጋፍ አድርጓል። የከርቤቲ ፕሮጀክት ለዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮችና የግል ተቋማት ተስፋ የሚሰጥ ሆኗል። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ መንግስት በሚከተለው የኢነርጂ ፖሊሲ ምክንያት የግል ተቋማት በዘርፉ ሙሉ በሙሉ መግባት አይችሉም ነበር። ይህ ፕሮጀክት ግን ይህን አሰራር ለመጀመሪያ ጊዜ በመስመር ሙሉ በሙሉ በውጭ ኩባንያዎች ወደ ስራ እንዲገባበት የተደረገ ነው። የፓወር አፍሪካ ፕሮጀክት ዋንኛ አላማም እስካሁን በመንግስት ሞኖፖል ተይዞ የቆየውን የአፍሪካ የኢነርጂ ሴክተር ደረጃ በደረጃ በግሉ ዘርፍ እንደሆነ ማድረግ ነው።

ለዚህ እንዲረዳም የአፍሪካ መንግስታት አመቺ ሁኔታን ለግሉ ዘርፍ እዲፈጥር የበኩሉን እገዛ ያደርጋል። የሬኪያቪክ ኩባንያ በመጀመሪያ ዕቅዱ ማለትም በ2015 10 ሜጋዋት የጂኦትርማል ኃይል ያመነጫል በመቀጠልም በ2016 100 ሜጋ ዋት ኃይል ያመነጫል። ከዚያም በ2018 500 ሜጋዋት ኃይል ያመነጫል። በአሁኑ ወቅት አፍሪካ የተትረፈረፈ የውሃ፣ የነፋስ፣ የፀሐይና የጆኦትርማል ታዳሽ ኃይል ቢኖራትም 61 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ግን ቤቱ በኩራዝ ብርሃን ይታደጋል። በምግብ ማብሰያም ማገዶን ስለሚጠቀም አካባቢን ከማራቆት በዘለለ በራሱ ጤና ላይም አደጋን እያስከተለ ይገኛል። ፓወር አፍሪካ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር የግሉን ዘርፍና መንግስታትን በማስተባበር ለ20 ሚሊዮን ቤተሰቦች በመጭው አስር ዓመታት ታዳሽ ኃይል ለማቅረብ ጥረት ያደርጋል።

አቶ ማርቆስ መላኩ በሙያቸው የጂኦተርማል መሀንዲስ ሲሆኑ በስራአለም በርካታ ዓመታትን አስቆጥረዋል። በአሁኑ ወቅትም ከላይ በተጠቀሰው ከርቤቲ አካባቢ በሚሰራው በሬኪያቪክ ኩባንያ ተቀጥረው በመስራት ላይ ይገኛሉ። እንደ እርሳቸው ገለፃ ኩባንያው በኢትዮጵያ ውስጥ የጂኦተርማል ጥናት ቁፋሮና ማምረት ስራ ለመስራት የሚያስችለውን ፈቃድ ወይም ላይሰንስ አግኝቷል። ኩባንያው በግል ላለፉት ሁለት ዓመታት የእንፋሎት ኃይልን በመፈለግና በመቆፈር ስራ ተሰማርቷል። እንደርሳቸው ገለፃ ኢትዮጵያ በጂኦትራማል ኃይል ማመንጨትና ኢኮኖሚዋን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ተስፋ ያላት ሀገር ነች። ይህን ይበልጥ ጥቅም ላይ ለማዋል ጠቀም ያለ ገንዘብ በመመደብ ጥናትና ምርምር ማካሄድ ያስፈልጋል። የሬኪያቪክ ኩባንያ የጂኦተርማል ፕሮጀክት የራሱን አሰራር ስርዓት በመዘርጋት እጅግ የተራቀቁ የአፈር የመመርመሪያ እና ጉድጓድ የመቆፈርያ መሳሪያዎችን ይጠቀማል። ፕሮጀክቱ በተለምዶና ተለምዶአዊ ባልሆነ መልኩ ስራውን ያከናውናል። በመሬት አቆፋፈርና በእንፋሎት ፍለጋ ዙሪያ ለሃይሉ መገኘት ምክንያት የሆነውን ለማወቅ በከርሰ ምድር ያለውን የቀለጠ አለት (ማግማ) አካባቢ በጥልቀት ይፈትሻል። ከዚያም በከርሰ ምድር የሚገኘው ውሃ በማግማ ወይም የቀለጠ ድንጋይ አማካኝነት ሞቆ እንፋሎት ሰርቶ ወደ ገፀ ምድር እንዴት እንደሚያፈተልክ ቴክኒካዊ ዘዴን ተጠቅመው እንዲወጣ ያደርጋል። እንደአቶ ማርቆስ ገለፃ በአንድ ከርሰምድር ውስጥ የጂኦተርማል ኃይል እንዲገኝ ከተፈለገ በመሬት ውስጥ የሚገኘው ማግማ ውስጥ የሚዘዋወር ውሃ እና እንፋለጎት መገኘት ወሳኝ ነው።

ከዚህ ጋር ግፊት የሚፈጥር ኃይል መኖር ይኖርበታል። የጂኦተርማል ስርዓት እንዲፈጠር በከርሰ ምድር ውስጥ እስከ 300 ዲግሪ ሴን ቲግሬድ የሚደርስ ሙቀት የግድ መኖር አለበት። እንደ አቶ ማርቆስ ገለፃ የእንፋሎት ኃይል አቅርቦት በሁለት አይነት አካሄዶች ማግኘት ይቻላል። አንደኛው ከፍተኛ የሙቀት መጠን ባለው ማለትም ከ200 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ሙቀት አማካኝነት የሚገኝ የኤሌትሪክ ኃይል ነው። ይህ ሊሆን የሚችልበት ምክንያቱም ሙቀት ከፍተኛ የእንፋሎት መጠን ስለሚያመነጭ ነው። ሁለተኛው ዓይነት ኃይል ደግሞ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ባለው ከርሰምድር የሚካሄድ ነው። ይህም በአጠቃላ ከ200 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያነሰ መሆን አለበት። በዚህ ሁኔታ የሚገኘው እንፋሎት የኤሌትሪክ ኃይልን ለማመንጨት አያስችልም። ይህ እንፋሎት የሚያገለግለው ለማቀዝቀዣ ወይም ለማሞቂያ ወይም ደግሞ ለመዋኛ ገንዳ ነው። እንደ አቶ ማርቆስ ገለፃ አለም በሁለት ቴክቶኒክ ከርሰ ምድር የተሰራች ናት። አፍሪካ አንደኛውን የቴክቶኒክ ንጣፍ አግኝታለች።

የመካከለኛው ምስራቅ ደቡብ ኢስያ ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ እንዲሁም የፓስፊክ ደሴቶች አንደኛውን ንጣፍ አግኝተዋል። እነኚህ ንጣፎችም የጂኦተርማል ኃይልን ለመፍጠር የሚያስችላቸውን ያልተቋረጠ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ ግጭት ፍጭቱም እሳተጎመራ ወይም የድንጋይ መቅለጥ ተከስቶ ጂኦተርማል ኃይል እንዲገኝ ምክንያት ይሆናሉ። ወደ ምስራቅ አፍሪካ ሲመጣም አብዛኛው የጂኦተርማል እንቅስቃሴ የሚፈጠረው በታላቁ የስምጥ ሸለቆ ውስጥ ነው። በዚህ አካባቢ የእንፋሎት ኃይል የሚመነጨው ከሌሎች የሸለቆው የመጀመሪያ እንቅስቃሴ የሚነሳው ከደቡብ ቀይባህር ሲሆን ከዚያም ኢትዮጵያን ሰንጥቆ በኬንያ በኩል ወደ ታንዛኒያ ያመራል።

በኢትዮጵያ የጂኦተርማል እንፋሎት ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ መዋሉን የታሪክ ድርሳናት ያመለክታሉ በአብዛኛውም ለህክምና እና ለፀበል አገልግሎት ውለዋል። የሶደሬና የወንዶገነት አካባቢዎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ፍልውሃ እየሰጠ ያለው ጥቅም ከዚህ ከጂኦተርማል ከመነጨ ኃይል ነው። ለአዲስ አበባ ከተማ መቆርቆር ምክንያት የሆነውም በእቴጌ ጣይቱ አማካኝነት በፍልውሃ አካባቢ የጅኦትርማል ምንጭ ውሃ በመገኘቱ ሲሆን ይህም በራሱ በታሪካዊነቱ የሚጠቀስ ነው። በአሁኑ ወቅት የጂኦተርማል ኃይል አረንጓዴ እጽዋቶችን ወይም የአበባ እርሻዎን ለማልማት በተለይ በኬንያ ጥቅም ላይ ውሏል በአሜሪካ እንዲሁም በተባበሩት አረብ ኢሜሬትስ የጂኦተርማል ኃይል ከተሞችን ለማቀዝቀዣ ጥቅም ላይ ውሏል። እንደ አቶ ማርቆስ ገለፃ በአጠቃላይ ታዳሽ ኃይል በአፍሪካ የተትረፈረፈ ቢሆንም ኃይሉን ለማምረት ወደ ስራ ሲገባ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ማፍሰሰን ይጠይቃል ስለዚህ የውጭ ኢንቨስትሜነት የግድ አስፈላጊ ነው።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
1158 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1037 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us