ትኩረት ለአዲስ አበባ መናፈሻ ስፍራዎች

Wednesday, 26 February 2014 12:51

የአዲስ አበባ ከተማ ከተቆረቆረች ጀምሮ እስካሁን በማደግ ላይ ትገኛለች። የህዝቧ ቁጥር ወደ አራት ሚሊዮን ይጠጋል። በ54 ሽህ ሄክታር መሬት ላይ የተንጣለለችው ይህች ከተማ ከባህር ወለል በ2500 ሜተር ላይ ትገኛለች። በኢኮኖሚው ዘርፍ በየአመቱ አዳዲስ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው። የአገልግሎቱን ዘርፍ የሚያግዘው የኮንስትራክሽን ዘርፍ በእድገት ላይ የሚገኝ ስሆን ለበርካታ ወገኖችም የስራ እድል እየፈጠረ ነው። የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ማለትም የመንገድ ጎዳና የባቡር መስመሮች የጤና ኬላዎችና ሆስፒታሎች ትምህርትቤቶች የአረንጓዴ ስፍራዎች እየተስፋፋ ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪ ከተማዋ የአፍርካ የአለም መዲናነትዋ በየጊዜ እየጨመረ መጥቶ በርካታ ዲፕሎማቶች የቱርስቶች መድረሻ ለመሆን በቅታለች። በዚህ ደረጃ ላይ የየምትገኘው አዲስ አበባ ለመኖርያነትና ለእንግዶች ማረፊያነት በይበልጥ ተመራጭ እንድትሆን የከተማዋን ፅዳት ውበትና ተስማሚ አየር የማግኘት ጉዳይ ለነገ የሚተው ስለሚሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ለውጡ ግድ ይላል።

የአዲስ አበባ ከተማ የውበት መናፈሻና ዘላቂ ልማት ኤጀንሲ ከዚህ አኳያ በተቋቋመበት ህግና ደንብ እንዲሁም ይዘት በተነሳው ራዕይ መሠረት የነዋርዎችንና ተገላጋዩን ህብረተሰብ ፋላጎት ለማርካት የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን የስራሂደት የሆኑት አቶ ሀብታሙ ፀጋዬ ይገልፃሉ። እንደ እርሳቸው ገለፃ መስርያ ቤታቸው በስራ አስኪያጀፅህፈት ቤት ስር የሚገኝ ሲሆን ተልዕኮውን ለማሳካት ሚዛናዊ የምዘና ስርአት ዘርግቶ ይንቀሳቀሳል የዕድገትን ትራንስፎርሜሽኑን ለመተግበር የበኩሉን ጥረት እያደረገ ይገኛል። ኤጀንሲው በክፍለ ከተሞችና በወረዳ ደረጃ የራሱ የሆነ መዋቀር የዘረጋ ሲሆን በእነርሱ ስር የሚገኙትን ወደ 22 የሚጠጉ መናፈሻዎችን ያስተዳድራል፤ ይቆጣጠራልም። በዚህ ሂደትም የትኛዎቹ አካላት በተሰጣቸው የስልጣን መጠን ሃላፊነታቸውን ይወጣሉ ከዚሁ ጋር ተያይዛም እንደ አስፈላጊነቱ አዳዲስ መናፈሻዎች እንዲሰፋ ጥረት ያደርጋሉ።

ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው የከተማዋ ነዋሪ ቁጥር እየጨመረ ነው። ከተማዋም ወደ ጎን እየተለጠጠች ነው። ነዋሪውን ከቦታ ቦታ ለስራና ለዕለት ህይወት ከቦታ ወደ ቦታ የሚያንቀሳቅሰው የትራንስፖርት ዘርፋም ከጊዜ ወደ ጊዜ በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል። እንደዚያም ሆኖ ግን በዘርፉ ፍላጎትና አቅርቦት በጭራሽ አልተመጣጠኑም ከዚህ አኳያ የትራንስፖርቱ ዘርፍ ሰፊ የስራ እድል ሊያገኝ የሚችልበት አጋጣሚ እንዳለ መረዳት አያዳጋትም። የትራንስፖርቱ ዘርፍ መስፋፋትም መኪኖች በብዛት በካይ ጋዝን የሚለቁበትን ሁኔታ ይፈጥራል። ይህ ደግሞ የአየር ሙቀት መጨመርን ስለሚያስከትል በከተማዋ ለመኖሪያነት ተፈላጊነት ላይ የራሱን አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ለመገመት አያዳግትም። ከዚህ አኳያ ከተማዋ ነፋሻማ አየር እንድታገኝ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቁት በካይ ጋዞችም በተክሎችና ዛፎች አማካኝነት ተውጠው እንዲቀሩ ዛፎችን መትከልና መንከባከብ የአካባቢ ጥበቃ ስራ መስራትን መናፈሻ ቦታዎችን ማስፋፋትና እንዲሁም የአየር ማስተንፈሻ የሚሆኑ ክፍት ቦታዎችን ማስፋፋት ግድ ይላል። ከዚህ አኳያ የከተማችን የውበት መናፈሻና ዘላቂ ልማት ኤጀንሲ ምን እያከናወነ እንደሚገኝ አቶ ሀብታሙ ሲገልፁ በተለያዩ አካባቢዎችና በመናፈሻዎች ውስጥ ችግኝ እንዲፈሉ ተደርገው ይተከላሉ። መናፈሻዎችም ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ እንክብካቤ ይደረግላቸዋል። የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ። ለህጻናት መጫወቻ የሚሆኑ ቦታዎች ምቹ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው። ለሰርግና ለመሰል አገልግሎቶች የሚውሉ አደራሾችና ደሴቶች በቦታው ይገኛሉ። በመናፈሻዎች ውስጥ ለአይን ማራኪ የሆኑ እፅዋቶች የዱር እንስሳቶች ማለትም አንበሳ፣ ዝንጀሮ፣ ጦጣ ፣ ጥንቸልና የአእዋፍት ዘሮች የሚገኙ ሲሆን የውጭ ሀገር እንግዶችና የከተማዋ ነዋሪም መናፈሻዎችን ይጎበኛሉ። ከዚሁ ጋር ግልፅ መሆን ያለበት ጉዳይ ቢኖር መናፈሻዎች በሁለት የሚከፈሉ መሆናቸው ነው። ዝግና ክፍት መናፈሻዎች ይባላሉ። ዝግ መናፈሻዎች ሰዎች አስፈላጊውን የአገልግሎት ክፍያ ፈፅመው የሚስተናገዱበት ሲሆን ክፍቱ ግን ሰዎች ያለክፍያ የሚጠቀሙባቸው ናቸው። በከተማችን መናፈሻዎች በርካታ አካባቢዎች ይገኛሉ። አንዳዶች መናፈሻዎች እጅግ በጣም የተዋቡ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ደከም ያሉ ጭራሹንም በቆሻሻ ተወረው ይታያሉ። ከዚህ አኳያ የመናፈሻዎቹ አያያዝን በተመለከተ አቶ ሀብታሙ ሲገልፁ አንዳንድ መናፈሻዎች ለአሰራር እንዲያመች ለግለሰቦች ወይም ድርጅቶች outsource ይደረጋሉ። ለምሳሌ ሂልተን ሆቴል ፊት ለፊት የሚገኘው መናፈሻ የሚለማውና የሚተዳደረው በሜድሮክ ኩባንያ አማካኝነት ነው። ሜድሮክ ይህን ስራ የሚሰራውም በቅድሚ በአካባቢው ካለው ቂርቆስ ክፍለከተማ ውበት መናፈሻና ዘላቂ ልማት ኤጀንሲ ጋር ለተወሰነ ጊዜ ለማስተዳደር ውል ገብቶ ነው። በዚያም መሰረት ቦታውን እያስተዳደረ ከደንበኞች አገልግሎት በመስጠት ጥቅም የሚያገኝ ሲሆን አስፈላጊውን ግብርም ለመንግስት ይከፍላል። አምባሳደር መናፈሻ አጠገብ ያለው መናፈሻው ተመሳሳይ ነው አንድ የግል ድርጅት ከክፍለከተማው ኤጀንሲ ጋር ውል ፈፅሞ መናፈሻውን የሚያስተዳደር ሲሆን አስፈላጊውን ግብርም ለመንግስት ይከፈላል። የመናፈሻውን ደረጃ በተመለከተ ግን የክፍለከተማው ኤጀንሲ የመቆጣጠር ሃላፊነት አለበት። አንደን በቆሻሻ የተወረሩ መናፈሻዎችም ቁጥጥር እየተደረገ ወይ በባለሀብት በኮንትራት ተሰጥተው የሚለሙበት ሁኔታ የሚፈጠር ሲሆን ካልሆነም በመንግስት ስር እንዲተዳደሩ ይደረጋል። በአሁኑ ወቅት በከተማችን ከፍተኛ የኮንስትራክሽን ስራ እየተሰራ ይገኛል። በአንዳድ አካባቢዎች መናፈሻዎች በዚህ እንቅስቃሴ መነካታቸው አልቀረም። ከዚህ አኳያም መንግስት የበኩሉን የማስተካከል ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ለመረዳት ተችሏል። እንደ አቶ ሀብታሙ ገለፃ በከተማችን የሚሰሩ ማናቸውም ስራዎች በከተማዋ ማስተር ፕላን መሰረት ነው አዲስ የግንባታ ስራ ለመስራት ሲፈለግም ለግንባታ በተመረጠ ቦታ እንዲሁም በመልሶ ማልሚያ አካባቢዎች ነው። ከዚህ ውጭ ፕላኑን ከግምት ሳያስገባ የሚሰራ አንዳችም ነገር የለም። አንዳንድ አዳዲስ የመንገድና ማስፋፊያ የባቡር መስመር ዝርጋታዎች ሲከናወኑ ግን ማስተር ፕላኑ የሚከለስበት አጋጣሚ ይኖራል። ማስተር ፕላኑ በየትኛውም የመኖሪያቤቶችም ሆነ የሪል ስቴት ግንባታዎች በሚካሄድባቸው ቦታዎች ክፍትና የመናፈሻ ስፍራዎች አስቀድመው እንዲተው ይደረጋል። በአሁኑ ወቅት እየተገነቡ በሚገኙ የኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ ሰፋፊ መናፈሻና ክፍት ቦታዎች የሚዘጋጁትም የከተማዋን ውበትና መናፈሻ ስፍራት ለማጠናከር ነው። ከዚህ አንጻር በልደታ አካባቢ እንዲሁም በሀያት በተገነቡት መኖሪ ቤቶች አካባቢ የተሰራው መናፈሻ ለምሳሌነት የሚጠቀስ ነው። ከዚህ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት አዳዲስ መናፈሻዎች እየተስፋፉ ይገኛሉ። አራት ኪሎ ቀደም ሲል ባሻ ወልዴ ተብሎ ይጠራ በነበረው አካባቢ የመልሶ ማልማት ስራ በሚሰራበት ቦታ ላይ በሀገራችን በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመዋኛ ስፍራና ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ መናፈሻ በቅርቡ ይገነባል። በጎተራ አካባቢ ባለው ማሳለጫ መንገድና ብሔር ብሔረሰቦች ፓርክ ተብሎ በሚጠራውክፍት ቦታ ላይ በጣም ለአይን የሚስብና በርካታ ሰዎችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል መናፈሻም ይገነባል። በአየርላንድ ኤምባሲ አካባቢም በተመሳሳይ ትልቅ መናፈሻ ለመገንባት ዲዛይን ወጥቶለት ለተቋራጭ ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል።

     አዲስ አበባ ከተማ ፅዱ ውብና ለመኖሪያነት ምቹ ማድረግ የውበት የመናፈሻና ዘላቂ ልማት ኤጀንሲ ሃላፊነት ነው። ይህ ስራም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከባለድርሻ አካላት ጋር መከናወን ያለበት ጉዳይ ነው። በሌላ በኩል ስለከተማዋ ጽዱነትና ምቹነት ሲገለፀ ከዚህ ሁኔታ ጋር አብረው የማይሄዱ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻዎች በየአካባቢው መጥፎ ጠረን ከተማዋን በመጥፎ ሽታ ሊሰነፍጥ ይስተዋላል። በአንድ በኩል የአፍሪካ መዲናነትዋ እየጎላ መጥቷል በሚባልበት በአሁኑ ወቅት የፅዳት ጉዳይ እጅግ ትኩረት ሊያገኝ የሚገባው ነው። በርግጥ ደረቅ ቆሻሻንም ሆነ ፍሳሽ ቆሻሻን ለማስወገድ ከመንግስት በኩል አቅም ውስንነት ቢስተዋልም በየሰፈሩ ቆሻሻን ለማንሳት የተደራጁ ወገኖች እየከናወኑት ያለው ስራም ይበል የሚያሰኝ ነው። ነገር ግን ስለውበትና መናፈሻ ሲወሳ የዚህ ተቃራኒ የሆነውን የቆሻሻ ብክለትን ለማስቀረት እየተሰራ ያለውን በተመለከተ አቶ ሀብታሙ ሲናገሩ ደረቅና ፍሳሽ ለማዳበሪያነት ወይም ቆሻሻን በተመለከተ ስልጣን የተሰጠው አካል በመስተዳድሩ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት ስር የሚገኘው የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አስወጋጅ ኤጀንሲ ሲሆን ደረቅ ቆሻሻን ከየቤቱ በመውሰድና ወደሌላ አካባቢ በማከማቸት እንደሚያስወገድ ፈሳሽ ቆሻሻንም በቦቴ መኪና በመምጠጥ ወደተመደበለት ቦታ በመውሰድ ያፈሳል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቆሻሻ ሀብት ነው የሚለውን መርህ ለመተግበር ደረቅ ቆሻሻን ለቀልዝነትና ለመሰል ስራዎች እንዲሁም እንደፕላስቲክና ጠርሙስ የመሳሰሉትን አሻሽሎ በመፈብረክ መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረጋል። ይህም ከተማዋን ከማፅዳት ባለፈ ለበርካቶች የስራ እድል ፈጥሯል። ፍሳሽ ቆሻሻም ቢሆን ታክሞ እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረጋል። በሌላም በኩል ስለ ዘላቂ ልማት መናፈሻ ጉዳይ ሲወሳ በውጭ ሀገር አንዳንድ ከተሞች የመቃብር ስፍራዎች በስርዓት ተይዘው ለፓርክነትና ለዘላቂ ማረፊያነት ውለው ከፍተኛ ጥቅም እየሰጡ ይገኛል። ይህን ተሞክሮ በመውሰድም በከተማችን የዚሁ መሰል ጥረት ተጀምሯል። በአዲስ አበባ ከተማ ውበትና መናፈሻ ዘላቂ ማረፊያ ልማት ኤጀንሲ ስር ወደ 16 የሚጠጉ ዘላቂ ማረፊያዎች ይገኛሉ። 9ኙ አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን ሌሎቹም እየተሻሻሉና እየታደሱ ይገኛሉ። የመቃብር አጠቃቀምም እንቀድሞው ዘመን በሰፋፊ ቦታዎች ላይ ሳይሆን በውስን በሆነ መሬት ላይ ሆኖ ቦታው እንደ ፓርክ እንዲያገለግል እየተደረገ ይገኛል። ከዚህ አንፃር በቀጨኔ መድሃኒአለም አካባቢ ያለው የመቃብር ስፍራ በምሳሌነት ሊጠቀስ የሚችል ነው። ከዚህ ቀደም እነኚህ አካባቢዎች ለአደገኛ ቦዘኔዎችና ቀማኞች መጠለያ ነበሩ። አሁን ግን ለከተማዋ ውበት አጋር በመሆን ላይ ናቸው። ይህ መሰሉ ስራ ሊበታታ ይገባዋል። የከተማችን ነዋሪ እየጨመረ በሄደ ቁጥር ብክለትም የዚያኑ ያህል ሊጨምር ይችላል። ስለሆንም ከተማዋን ውብ የማድረጉ ስራ ለኤጀንሲው ብቻ የሚተው ሳይሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃለፊነት ሊወጡ ግድ ይላል።

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
1579 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 968 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us