የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመግራት የሜትሮሎጂ ጠቀሜታ

Wednesday, 05 March 2014 14:06

ሰው ልጅ የማህበራዊ ህይወቱን ይበልጥ ምቹ ለማድረግና ኢኮኖሚያዊ ዕመርታን ለማምጣት በየእለቱ ይታትራል ዕውቀቱንና ልምዱን በመጠቀማ የሚፈጥራቸውን ቴክኖሎጂዎችን በግብአትነት ተጠቅም ለብላፅግና ይተጋል ይህ እንቅስቃሴ በአብዛኛው በተፈጥሮ ሀብትን ጥቅም ላይ በማዋል የሚከናወን ሲሆን ተለዋዋጩ የተፈጥሮ ፀባይም መልስ በሰው ልጀ የልማት ተግባር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ከማድረስ አልፎ በልፋት በተገኘው የሰው ልጀ ህይወትና ሀብት ላይ ውድመትን ያስከትላል። ከዚህ አኳያ የተፈጥሮን አሉታዊ ተፅዕኖ ከመግታት አኳያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነው ሜትሮሎጂ አገልግሎት እንደ ዝናብ ሙቀት ውርጭና እርጥበታማነትን አስቀድሞ በመተንበይ ሊደርሱ የሚችሉ ተፅዕኖዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ መረጃዎችን በመስጠት የላቀ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።

ይህን ስራ እየተገበሩ ከሚገኙት ተቋማት መካከል የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ የአየር ጠባይ ተለዋዋጭ ክስተቶችን፤ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕንቅስቃሴዎች ላይ ሊያሳድሩ የሚችሉ ተፅዕኖዎችን በመከታተልና አስቀድሞ በመተንበይ የደንበኞችንና የባለድርሻ አካላትን ፍላጎት ለማካተት በትጋት በመስራት ላይ ይገኛል።

ከሰሞኑም ኤጀንሲው አገልግሎት አሰጣጥን የወቅት ግምገማ እንዲሁም የመጭውን የበልግ ወቅት ትንበያ በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። በወቅቱ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ እንደተናገሩት ኤጀንሲው የሚሰጣቸው የሜትሮሎጂ መረጃዎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ከመሆኑም በላይ በተለይ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ ለሆነው የእርሻው ዘርፍ ቅድመ ጥንቃቄ እንዳያደርግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል። በዚህ ዕንቅስቃሴውም የባለድርሻ አካላት ግብረ መልስ አስፈላጊ በመሆኑ በየጊዜው ከእነርሱ ጋር መመካከሩ ወሳኝነት አለው ሲሉ አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ በአብዛኛው የተበጣጠሰና በደሀ ገበሬዎች የሚመረት በዝናብ ላይ በእጅጉ ጥገኛ የሆነ ነው። በሌላም በኩል በተዳፋት መሬቶች ላይ ሚታረሰው እርሻ ለአፈር መሸርሸር የተጋለጠና ለምነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ የሚሄድ ነው። የመሬት ይዞታው በመንግስት ባሌትነት ስር መሆኑም ለአካባቢ ጥበቃ የሚሰጠው ትኩረትና የረጀም ጊዜ ኢንቨስትመንት በመሬት ላይ የማድረግ እንክብካቤ እንዲቀዛቀዝ የሚያደርግ ነው። እንዲያም ሆኖ ዘርፋ ለሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት ወይም /GDP/ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ 49 በመቶ ነው። ከዚህ አኳያ የአየር ንብረት ተዛብቶ ዝናብ አጥቶ ድርቅ ሲመጣ ተፅዕኖው በገበሬው ህይወት ላይ ብቻ የሚያርፍ አይደለም። ይልቁንም በጠቅላላው ኢኮኖሚ ላይ ጫና የሚያሳርፍ በመሆኑ የሜትሮሎጂን መረጃ በአግባቡ አጠናቅሮ፣ ተንትና ቀምሮ ለተጠቃሚው ማድረስ አጅግ አስፈላጊና ወሳኝ ነው።

የኢትዮጵያ የመሬት አቀማመጥም በሀገራችን ያለው የአየር ንብረት እጅግ የተዘበራረቀና ልዩነቱ የሰፋ እንዲሆነ አድርጓል። በአፋር ክልል የዳሎል አካባቢ ከባህር ወለል ከዜሮ በታች እስከ 30 ሜትር ዝቅ ማለቱ ከዓለማ እጅግ ከፍተኛ ሙቀት ሲኖረው ከባህር ወለል በ4‚591 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኘው የራስ ዳሽን ተራራም በውርጫማነቱ የሚታወቅ ነው። በእነኛህ ተቃራኒ የመሬት አቀማመጥ መካከልም እስከ 18 የሚደርሱ የአየር ፀባዮች እንደሚገኙ ሙያተኞች ያመላክታሉ። ከዚህ አኳያ የሜትሮሎጂ ትንበያ የአየር ንብረት ለውጥ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ህይወት ላይ ሊያሳርፍ የሚችለውን ተፅዕኖ ከመግታት አንፃር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አጠያያቂ አይደለም።

እንደ አቶ ፈጠነ ገለፃ ሀገራችን በዓመት ውስጥ በተፅዕኖአቸው የተለያዮ የአየር ፀባዮች አሉ። የበልግ የበጋና የክረምት ወቅቶችን ታስተናግዳለች ይህ ክስተትም በተለያዩ የመሬት ገፅታዎች ላይ የሚከሰት በመሆኑ ሁኔታውን የተወሳሰበ ያደርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ በአለም ላይ የሚከሰተው የሙቀት መጨመርን የአየር ንብረት ለውጥ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተፅዕኖው ወደ ሀገራችን ስለሚመጣ ወቅታዊ መረጃዎች እጅግ ወሳኝ ናቸው። በመሆኑም የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በአግባቡ በመጠቀም እንዲሁም አሉ የተባሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በግብአትነት በማዋል የተቀላጠፈ አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል። በተለያዩ የጊዜ ቀመሮች የተለያ የአየር ጠባይ ትንበያዎችን በማዘጋጀት ከተጠቃሚዎች ጋር በመመካከርና የመገናኛ ብዙሃንን መሠል የመረጃ ማሳተላለፊያ ዘዴዎችን በመጠቀም አገልግሎቱን እየሠፋ ይገኛል።

በዚህ መነሻነት ኤጀንሲው በዘንድሮው የበጋ ወቅት ሊፈጠር የሚችለውን አዲስ የአየር ፀባይ ክስተት በጊዜና በቦታ ያለውን ስርጭትና ተፅዕኖን በተመለከተ በአመቱ መጀመሪያ ላይ ለደንበኞችና ለባለድርርሻ አካላት መረጃ የሠጠ ሲሆን ከተጠቃሚዎች የተገኘው ግብረ መልስ እንዳመለከተውም መረጃውና በተጨባጭ የተከሰተው የአየር ፀባይ የተጣጣሙ እንደነበሩ የኤጀንሲው ዳይሬክተር አስረድተዋል። መረጃው በሁሉም ክልሎች በተለይም ለግብርናውና ለአርብቶ አደሩ ዘርፍ የተሰራጨ ሲሆን ከወቅቱ ጋር ተያይዘው የተከሰቱት መልካም አጋጣሚዎችን መጠቀም ከማስቻሉም በላይ ተፈጥሮአዊ አደጋዎችን ለመከላከልም አስችሏል። በመጭው በልግ ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ ተፅዕኖዎችን ለመቋቋም ስልት እንዲቀይሱና እንዲዘጋጀም አስችሏል። መረጃዎችን በወቅቱ ተረድቶና ተገንዝቦ ታች ላለው አርሶ አደርና አርብቶ አደር ለማሳወቅ እንዲቻል በተለይ የግብርና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች የማይናቅ ሚና እየተጫወቱ የሚገኙ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ተጠቃሚዎች አየር ንብረት ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ተፈጥሮአዊ ክስተት መሆኑን እንዲገነዘቡ በማድረግ ረገድ ጠቀሜታው የጎላ ነው አርሦ አደሮች የባሕርይ ለውጥ እንዲያመጡና የአስተራረስ ዘዲያቸውን እንዲያፈራርቁ የሚሠጡ ምክር ሊበረታታ የሚገባው ነው።

እንዲያም ሆኖ ገበሬውም ሆነ አርብቶ አደሩ ድርንቅና የአየር ንብርት ለመቋቋም የሚያስችለው ባህላዊ ዕውቀት እንዳለው መገንዘቡ አስፈላጊ ሲሆን ዘመናዊ ትምህርት ባህላዊ ልምዶች በሚገኙ የሀገሪቱ አካባቢዎች የዝናብና የግጦሽ መሬት ዕጥረትን ለመቋቋም እንዲቻል አርብቶ አደሮች ከብቶቻቸውን በራንች (አንድ ቦታ በማሰባሰብ) በአንድ ማዕከል የውሃ አቅርቦት በሚገኝበት አካባቢ እንዲያስማሩ እየተደረገ የለው ጥረትምንም እንኳን በአንዳንድ ሙያተኞች ጥያቄ የሚነሣበት ቢሆንም ውስን ከብቶችን ወደሩቅ ቦታ ሳያጓጉዙ በአንድ አካባቢ አሰማርቶ ማድለብ ለገበያ ማቅረብ ከማስቻሉም በላይ የአርብቶ አደሩን የድርቅ ተገላጭነትን እንደሚቀንስ መረዳት አያዳግትም ስለሆነም የሚትሮሎጂ መረጃን ለዕለታዊ ችግር መፍቻ ከመጠቀም በዘለለ ለዘለቄታዊ ስትራቴጂካዊ ልማት መጠቀምም ተገቢ ነው።

የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ በዕለቱ ባካሄደው ስብሰባ ላይ ያለፈውን የበጋ ወቅት የአየር ፀባይ ግምገማና ከየካቲት እስከ ግንቦት በሚዘልቀው የበልግ ወቅት የሚጠበቀው የአየር ፀባይ ለውጥ አዝማሚያን አስመልክቶ የኤጀንሲው የሚትሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደሪባ ቆሪቻ እንደሚመለከቱት የመጭው በልግ ወቅት በመደበኛው የአየር ፀባይ ተፅዕኖ ስር እንደሚቆይ የበልግ ዝናብ በዋነናነት ለሚያስፈልጋቸው የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ማግኘት የሚገባቸውን መደበኛ ዝናብ ከሞላ ጎደል ሊያገኙ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በመጭው በልግ በተለያዩ የመሬት አቀማመጦች ሳቢያ ሊከሰቱ ሰለሚችሉት የአየር ፀባይ ለውጦች በተመለከተ የውቅያኖስ ሙቀት መጠን እንደሚጠቁሙት የመጭው ዝናብ በአጀማመሩ በስርጭቱና በመጠን አንፃር በደቡባዊ የሀገሪቱ አጋማሽና ምስራቃዊ የበልግ አብቃይ አባባቢቃች ከመደበበኛው የዝናብ መጠን ጋር የተቀራረበ እንደሚሆን ይጠበቃል።

በአብዛኛዎቹ የበልግ አብቃይ አካባቢዎችም የዝናብ አጀማመሩም ሆነ አጨራረሱ መደበኛውን ፈር የተከተለ እንደሚሆን ይገመታል። ይህም ሁኔታ ለበልጉ እርሻ አዎንታዊ ተፅዕኖ የኖረዋል ሆኖም አልፎ አልፎ የሚታይ የዝናብ መጠንና ስርጭት ተለዋዋጭነት ከፍተኛ በመሆኑ የወቅቱ ዝናብ በአንደንድ አካባቢዎች ላይ የመዋዠቅና ከመደበኛው ያነሰ ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል በያዝነው የካቲት ወርም ካሉት የሀገራችን የላይኛው ተፋሰሶች መጠነኛ እርጥበት እንደሚያገኙ በመጋቢት ወር ደግሞ ምስራቃዊ ባሮን አኮቦ የላይኛው ዋቢ ሸበሌ የላይኛው ገናሌ እና ዳዋ ኦሞ ጊቤ እና የላይኛው ስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የተሻለ ርጥበት የሚያገኙ ሲሆን በሚያዝያና በግንቦት ወር ደግሞ በደቡባዊና በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ተፋሰሶች የተሻለ ርጥበት ያገኛሉ ይህ ሁኔታም ጠቀም ያለ የውሃ መጠን ወደ ሀይድሮ ኤሌትሪክ ማመንጫ ጣቢያዎች እንዲገባ ከማድረጉ በተጨማሪ ለመስኖ ስራም አመቺ ሁኔታዎችን ይፈጥራል። በመጪው መጋቢት ወር ከጥቂት ደቡብ ምዕራብ ቆላማ አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች የሚጠበቀው የአየር ፀባይ ለወባ ትንኝ መፈልፈያ የሚያመች ከመሆኑ ባሻገር ስርጭቱም ለእርሻ ስራ ተስማሚነቱ አነስተኛ እንደሆነ የኤጀንሲው ትንበያ ያመለክታል።

በተመሳሳይ በመጪው ሚያዝያ ወር በደቡብ ምዕራብ፣ በጥቂት የምዕራብ፣ የሰሜን፣ የምስራቅና የሰሜን ምስራቅ ቆላማ ስፍራዎች ደቡብና ምስራቅ የሀገሪቱ ቆላማ ስፍራዎች እንዲሁም በግንቦት ወር በአብዛኛው ምዕራባዊ ቆላማ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚጠበቀው የአየር ፀባይ ለውጥ ለወባ ትንኝ መፈልፈል ምክንያት የሚሆን ነው። ስርጭቱም ምቹ እንዳልሆነ በባለሙያተኞች ተገልጿል።

በመጪው በልግ እርሶ አደሩ የሚጠበቀውን ምቹ የአየር ፀባይን በመጠቀም የሚያካሂደውን የግብርና ስራና ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስራዎችን በአካባቢ ማከናወን ይችላል የሚያገኘውን መረጃም በአገግባቡ መጠቀም ይኖርበታል። በአርብቶ አደሩ አካባቢ የሚጥለው ዝናብም የግጦሽ አካባቢዎች መልሰው እንዲያገግሙ ስለሚያደርግ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ለመጠቀም ራሱን ማዘጋጀት እንደሚገባው አቶ ድሪባ ቆርቻ አስረድተዋል።

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ኤጀንሲ ሚትሮሎጂ አጄንሲ የሚትሮሎጂንና ተዛማጅ መረጃዎችን በመሰብሰብና በማደራጀት በመተንተን የአየር ጠባዩ ለውጥንና የአየር ጠባይ ብክለትን በመከታተልና በመተንተን ለሀገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ዕገዛ በማድረግ እንዲሁም ህይወትንና ንብረትን ከውድት ለመታደግ በሀገሪቱ ባሉት አስራአንድ ቅርንጫፎች አማካኝነት ስራውን ያከናውናል። ይህ ተግባሩም ለምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች እንደምርጥ ተሞክሮ እንደሚያገለግል አቶ ድሪባ ይገልፃሉ። ኤጀንሲው ከዚህ ስራው በተጨማሪ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የሚትሮሎጂ መሳሪያዎችን ማምረትና ካሊብሬት ማድረግ መረጃዎችን በመሰብሰብ በመረጃ ቋት (ዳታ ቤዝ) ውስጥ ማከማቸት ለበረራ ደህንነት የሚያገለግል የኤሮኖቲክስ ሜትሮሎጂ መረጃ መስጠት ለውሃ ልማት ኢነርጂ ለግብርና፣ ለጤና ልማት ዘርፎች እገዛ የሚያደርጉ የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ መረጃዎችን በመስጠትና ትንበያዎችን በመስጠት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች በዋነኝነት የሚጠቀሱ ናቸው።

     ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው የኢኮኖሚያችን የጀርባ አጥንት ነው የሚባው ግብርና ለተለዋዋጭ የአየር ንብረትና ለድርቅ የተጋለጠ ነው። ዘርፉ ሲጎዳም መዘዙ ከባድ ነው። በመሆኑም የሜትሮሎጂ መረጃን ከመሰብሰብና ትንበያን ከመግለፅ ጎን ለጎን መረጃዎችን ለመተግበር የሚያስችል አቅምን ማጎልበትም ትኩረተ የሚያሻው ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
1609 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 938 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us