የደቡብ ሱዳን ትርምስና የጋምቤላው ፍጅት

Monday, 02 May 2016 15:51

 

ወሰንሰገድ መሸሻ በላቸው/ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የሁለተኛው የአለም ጦርነት ከተጠናቀቀ ከአንድ መት በኋላ እንግሊዝ ሱዳንን ከሁለት ከፍላ በቅኝ ግዛት ስታስዳድር የሰሜን ሱዳን ምሁራን የደቡብ ሱዳንን በመጋራት እንዲመሩ አደረጉ።

የአረብ ዝርያ ያላቸው የሰሜን ሱዳን መሪዎች ከደቡብ ሱዳን ጋር የፌደራል መንግስት በመመስረት ስ4ልጣን አጋርተናቸው አብረን እንጓዝ የሚል አሳተዳደራዊ ሰነድ ለእንግሊዝ አቅርበው በመፈቀዱ እነዚህ አረባዊ ሱዳኖች በዚሁ መስመር ተጉዘው ስልጣናቸው እየተጠናከረ ሲመጣ የተፈቀደላቸውን ስምምነት በመቀየር የደቡብ ሱዳን አመራሮችን ደረጃ በደረጃ በማግለል ስልጣናቸውን ከማጠናከር ባለፈ በደቡብ ሱዳኖቹ ላይ ፍፁማዊ የሆነ የበላይነት በመውሰዳቸው በእንግሊዝ የሚማሩ የደቡብ ሱዳን ተወላጅ ምሁራን የደቡብ ሕዝብን በማስተባበር እ.ኤ.አ.በ1995 ዓ.ም የት4ጥቅ ትግል ጀመሩ።

የደቡብ ሱዳን ችግር ገና በ19 ኛው ክ/ዘመን የእንግሊዞችና የግብፆች ጥምር የቅኝ አገዛዝ በመላው ሱዳን በነበረበት ወቅት ነበር የጀመረው። ደቡብ ሱዳኖች ከሰሜን ግዛት በከፋ ሁኔታ ተይዘው ስለነበር የደቡብ ሱዳን ህዝብ በእንግሊዞችና በግብፆች እንዲሁም በሰሜኑ ሱዳን የበላይነት ተፅእኖ ስር በመውደቃቸው መድሎ፣ የጭቆና አገዛዝ ግፋዊ ድርጊት ስለሚፈፀመባቸው በዚህ መነሻነት ኦገስት 18/1995 የትጥቅ ትግል ጀምረው ለ17 ዓመታት ትግሉ ቀጠለ።

ጃንዋሪ 1/1956 ሱዳን ከነችግሯፓርላሜንታሪ ዲሞክራሲያዊነት ነፃ ሐገር ሆና ብትመሰረትም የሱዳን ችግር ግን ግምት አልተሰጠውም። ይልቁንም መላውን ሱዳን በአሀዳዊ አስተዳደር ሥር አጠቃሎ የእስልምና ኃይማኖትን እንዲቀበልና የአረብኛ ቋንቋ የበላይነት እንዲሰፍን በሰሜነኞቹ የተጀመረው የመሪነት የጉዞ አቅጣጫ በደቡቦቹ ተቀባይነትን ካለማግኜቱ ባሻገር በኢኮኖሚውም ሆነ በስልጣኔ ሁለቱ ግዛቶች እኩል መሄድ ካላመቻላቸውም በላይ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍሉ ጤናማ ስላልሆነ ሰሜነኞቹ እየበለፀጉና እየሰለጠኑ እንደ አውሮፓውያኑ እየተንደላቀቁ ሲኖሩ ደቡቦቹ ግን እየደየሁ በስልጣኔ ወደኋላ እየቀሩ በጉስቁልና በችግር የሚኖሩ መሆናቸውን መገንዘባቸውና በተለይም በደቡብ ሱዳን ውስጥ የሚገኙ ሚስዮናውያንን በማባረር ክርስቲያኖቹ ከቤተክርስቲያን ውጭ ተሰባስበው እንዳይፀልዩ፣ ስብከትም ሆነ ውይይት እንዳያካሂዱ ታገዱ። እስላሞች ግን በየትኛው ስፍር፣ ቦታና ጊዜ ተሰባስቦ ለመፀለይም ሆነ ክርስቲያኖችን ወደ እስልምና ለመቀየር የሚያስችላቸውን መብት የተጎናፀፉበትን መብት በሰፊው የሰጠ ነበር።

ኢኳቶሪያል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አስተዳዳሪ የነበረው አሊ ባልዶ የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ሙሉለሙሉ እስልምናን በግድ እንዲቀበሉና ሙስሊም መሆን እንዳለባቸው አስገዳጅ ሁኔታ በመፈፀምና በብሄራዊ ደረጃ አረብኛና አረባዊነት ቋንቋና ባሕል፣ እስልምና ደግሞ ኃይማኖት እንዲሆን ከፍተኛ የሚባል ተፅእኖ በመደረጉና የቀሩት ሚስዮናውያን በፌበርዋሪ 17/1964 ተጠራርገው በመባረራቸው የተቀጣጠለው አመፅ  

በመስከረም 1963 ጆሴፍ ኦዱሆ የተባሉ ሰው የቀድሞው የኢኳቶሪያል ኮርፕስ ወታደሮችን አሰባስበው ‹አኒያ-ኒያ. የተባለውን አመፅእና የሽምቅ ውጊያ ጀመሩ። በዚህ አመፅ መቀስቀስ በማእከላዊው መንግስት ውስጥ በተከሰተው እንቅስቃሴ የወታደራዊ መንግስት መውደቁም ይታወሳል።

የደቡብ ሱዳንን አመፅ ለማስቆም ብዙ ጥረቶች ተደርገዋል። እ.ኤ.አ በ1972 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ በተፈረመው ስምምነት ለ17 ዓመታት የተካሄደውን ጦርነት ለጊዜውም ቢሆን ያስቆመና ደቡብ ሱዳን ራስ ገዝ እንዲሆንና በሕገመንግስቱ እንዲካተት ማድረግ ተችሎም ደቡብ ሱዳን ማእከላዊው መንግስት ጣልቃ ሳይገባባቸው ራሳቸውን ማስተዳደር ጀመሩ።

ለጥቂት ጊዜ ሰፍኖ የነበረው ሰላም በጃፋር ኤልኒሜሪ መንግስት ተንኮል፣ ስሕተትና ሴራ የደቡብ ሱዳን ራስ ገዝ አስተዳደር ጉዳይ ተቀይሮ ሱዳን ወደዳግም ግጭት ገባች፣ ግጭቱም እስከ ጥር 9/2010 የተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ድረስ ዘልቋል።

የደቡብ ሱዳን የመገንጠል ጥያቄ

የሱዳን ፕሬዚደንት ጃፋር ኤልኒሜሪ ስልጣን ከያዙ በኋላ በ1983 ሱዳን በሼሪአ ሕግ አስተዳድራለሁ፣ ሱዳንን የአረብ ሊግ አባል አደርጋታለሁ ብለው በቆራጥነት ተነስተው ይህንን እንደመርህ ወስደው  ይህንን የነደፉትን አቅጣጫ ፖሊሲ የሚያዘጋጁ መድበው በሕገመንግስት አፀደቁት።

ከሱዳን የውጭ ንግድ 70 ከመቶ ድርሻ ያለውና የአባይ ወንዝ ገባር የሆኑ ብዛት ያላቸው ወንዞች የሚገኝበትን ደቡብ ሱዳን ግዛትን በወታደራዊ አገዛዝ ስር ለመቆጣጠር በማሰብ የአረብ መንግስታት እንደሚረዷቸው እርግጠኛ በመሆን ሊታረም የማይችለውን ታሪካዊ ስሕተት ፈፀሙ።

የኤል ኒሜሪ ፖሊሲና በሕገመንግስቱ የተደነገገው ጉዳይ ያስቆጣው የደቡብ ሱዳን ህዝብ በጆን ጋራንግ የሚመራ የደቡብ ነፃ አውጭ የሚል ድርጅት በማቋቋም የመገንጠል ጥያቄን አንግበው በሱዳን መንግስት ሰራዊትና ደጋፊዎቹ ላይ ግልፅ የሆነ ጥቃት መፈፀም ጀመሩ።

የደቡብ ሱዳን ነፃ አውጭ ድርጅት ጥቃቱ እያየለና ተጠናክሮ በመምጣቱ በጀነራል አብዱልራህማን ሱወር ደሀብ የሚመራ የሱዳን ሰራዊት ተነሳስቶ በሚያዝያ 1985 የጃፋር ኤልኒሜሪን መንግስት ገልብጦ ጊዜያዊ መንግስት አቋቋመ።

የደቡብ ሱዳኖችን ቁጣ ለማብረድ ሱዳን በአረቦች ቋንቋ የምትመራበትንና የአረብ ሊግ አባልነቷን ከህጉ ሰርዘው በሸሪአ ሕግ ግን እንደምትመራ አስታወቁ።

ከሲቪል ማኅበራት ከፖለቲካ ቡድኖች የተዋቀረው ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት ከሲቪል ማኅበራት የተወከሉትን ዶ/ር አልጀዙል ዳፍ አላህ ጠ/ሚንስትር ሆነው ተሰይመው እስከ 1986 ድረስ ከመሩ በኋላ በምርጫ አሸንፈው በሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ለተመረጡት ለሳዲቅ አልማህዲ አስረከቡ።

ሳዲቅ አልማህዲ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ጥምር መንግስት በማቋቋም ከደቡብ ሱዳን ተደራዳሪዎች የሸሪአ ሕግ እንቀበል ማለታቸውን ጠ/ሚንስትር ሳዲቅ አልማህዲ ሙሉ ለሙሉ ጥያቄውን ውድቅ ስላደረጉት በጥምር መንግስት ውስጥ የተካተተው ዲሞክራቲክ ዩኒየን ፓርቲ የጠ/ሚንስትሩን ውሳኔ በመቃወም ከጥምር መንግስቱ ስልጣን እራሳቸውን አገለሉ።

የሱዳን ጦር አዛዥ ሳዲቅ አልመራዢ ለጠቅላይ ሚንስትር ሳዲቅ አልማሃዲ ከሰላም ድርድሩ ወይም ከስልጣናቸው አንዱን እንዲመርጡ ጫና ፈጥረው አስጠነቀቋቸው። ጠ/ሚንስትሩም ጥያቄውን ተቀብለው ከጥምር መንፍስቱ እራሱን ያገለለውን ዲሞክራቲክ ዩኒየን ፓርቲ ወደ ስልጣኑ እንዲመለስ አድርገው የሰላም ድርድር ተጀመረ።   

እ.ኤ.አ. በሰኔ 30/1989 ኮሎኔል ኦማር ሐሰን አልበሽር ይህን የሰላም ድርድር እንደጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም 15 የጦር አዛዦችን አስከትለው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት አካሂደው እስካሁን በሱዳን መሪነት እስከ ጀነራልነት ማእረጋቸው ይገኛሉ።n  

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
569 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us