ኢህአዴግ ራሱን ይፈትሽ

Wednesday, 01 June 2016 12:27

 

ኢህአዴግ ከመቼውም በላይ እራሱን መመርመሪያው ወቅት ላይ ነው። ምንም አይነት ውጪያዊ ጠላት የሚያሸንፈው አይመስልም። ነገር ግን የኢህአዴግ ጠላት እራሱ ነው። ውስጡ እየተስፋፋ ያለውን ካንሰር ቆርጦ መጣል አለበት። ውስጡ የተሰገሰገው በሽታ ድርጅቱን ከህዝብ ልብ ውስጥ በማውጣት እየገደለው ነው።


ከአንድ ሺህ በላይ የኮንዶምንየም ቤቶች ባክነውበት የነበረው ሹመኛ ዛሬም በተሽከርካሪው ወንበር ላይ ተመችቶት ተቀምጦ ህዝብ ላይ ይሳለቃል። የመብራት ኃይል ሹመኞች በህዝቡ ላይ እየተጫወቱ እድሜያቸውን ያራዝማሉ። ኢትዮጵያ አየር መንገድን የመሰለ ተቋም መምራት የሚችሉ አመራሮችን ያፈራች ሀገር እውን መብራት ኃይል መስሪያቤትን በቅጡ ማስተዳደር የሚችሉ ሰዎች የሏትምን? እንዲህ እንዲህ እያልን በየቦታው ያለውን አስጊ ሁኔታ መተንተን ይቻላል።


ኢህአዴግስ እንደው ጤናውን ደህና ነውን? የድሮው ስብዕናውና ባህሪው በቦታው አለ? በዛሬው ኢህአዴግና በጥንቱ መሀከል ያለው ልዩነት ከመቼውም በላይ እየሰፋ ነው። በዚህ ሁኔታ ወዴት እያመራ ነው? ምነው በውስጡ የተሰገሰጉትን ቆራርጦ ለመጣል ወኔው ካደው? ያንን የጥንቱ ወኔውን ደግሞ መላበስ ካልቻለ እሱም ሆነ ሀገሪቷ መቀለጃ ይሆናሉ።


ምናልባት አሁን ድርጅቱ ላለበት አጣብቂኝ ሁኔታ ምክንያት ነው ብዬ የምገምተው በተገቢው ሁኔታ ያልተካሄደ "መተካካት" ነው። ምናልባትም ታቅዶ የነበረው መተካካት የአቶ መለስን ድንገተኛ ሞት ታሳቢ ያደረገ አልነበረም። ስለዚህም በአሁኑ ወቅት የምናየው የዉሳኔ አሰጣጥ ክፍተት ተፈጠረ።


ስለዚህም ወደ መፍትሄው ስናመራ ድርጅቱንና ሀገሪቷን ለመታደግ ኢህአዴግ ልዩ የተሀድሶ ኮንፈረንስ ማዘጋጀት አለበት። አሁን ድርጅቱ የሚገኝበት ሁኔታ በጣም አስጊ በመሆኑ በወትሮው የአካሄድ ስርአትና በመሳሰሉት እጅና እግሩን ሳያሳስር ያኔ እነ ደጀና ዋሻዎች ውስጥ ያደርግ እንደነበረው በግልጽ ሊገማገም እና ተጎምደው ሊጣሉ የሚገባቸውን ጎምዶ ሊጥል ይገባል። በዚህም እራሱን ያድናል።


በዚህ ወቅት ብዙ መስራት እየቻሉ በመተካካቱ ሰበብ ከውሳኔ ሰጪነቱ የራቁት የቀድሞው አመራሮችን ወደ እቅፉ በማስገባት ልምዳቸውን ሊጠቀምበት ይገባል ... በውሳኔ አሰጣጡ ሂደትም ጭምር። አለዚያ ሂደቱ ውሀ ቅዳ-ውሀ መልስ ይሆናል። ልዩ የተሀድሶው ኮንፈረንስ ሀገሪቷን እንዲቤዛት ከታሰበ ከ Business as Usual አሰራር መወጣት አለበት። ይህንን ለማድረግ ግን አርቆ ማሰብና እውነተኛ ትህትና ይጠይቃል።


ይህንን ስር-ነቀል ለውጥ ሊያዋልድ የሚያስችለው የህዳሴ ኮንፈረንስ እውን እንዲሆን የጠ/ሚ ኃ/ማርያም ሀላፊነት ግዙፍ ነው። ይወጡታል ብዬም እገምታለሁ።


ኢህአዴግ እራሱንም ሆነ ሀገሪቷን ለመታደግ አስቸኳይ የህዳሴ ኮንፈረንስ በመጥራት እራሱን ያጽዳ። ያለዚያ .....? ያለዚያ ታሪክ ግንባሩን የሚያስታውሰው አዲሲቷን ኢትዮጵያን የፈጠረ በሚል ብቻ ሳይሆን ያቺ አስውቦ የፈጠራትን ሀገር ማዳን እየቻለ ያላሳካ በሚልም ነው።


ፈጣሪ ሀገራችንን ይጠብቅ።
ምንጭ፤ (EthiopiaFirst.com)n

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
766 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 966 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us