የአዲስ አበባ አስፋልት - ከተጓዡ ማስታወሻ

Thursday, 07 July 2016 15:21

 

ሙሉጌታ ደሳለኝ

1.የሻሂ ሰዓት

ማለዳሰማዩጉምአዝሎጉድአዝለንጉዞጀመርን። የመንገድ ክፋቱ ርዝመቱ የመንገድ ደግነቱ መደበሪያ አለማሳጣቱ እንዲሉ የሰፈራችን ሰዎች … በከተማዋ የተለጠፉ ማስታወቂያዎችን እያነበብን ዘና ፈታ ብለን እናዘግማለን። እስቲ እድሜያችሁ ከ18 አመት በታች የሆናችሁ የወተት እንዲሁም እድሜያችሁ ከ18 አመት በላይ የሆናችሁ የመጠጥ ባነሮችን ተመልከቱ፡-

ሀ. "በጉዟችሁተደሰቱ" ይላልአንዱ የቢራ ማስታወቂያ -  ወክ እያደረጋችሁ እንድትጎንጩና ከጭንቀታችሁ እንድትላቀቁ

ለ. "ቺርስለአንበሶቹ" ይላልሌላው የቢራ ማስታወቂያ - የረፋድ ብርድ የከሳች ዶሮ ላስመሰላችሁ ገዝፋችሁ እንድትታዩ

ሐ. "All Peoples are equal but All Alcohols are not equal” ሚል የውስኪ ማስታወቂያ - በውርስ ትርጉሙ "ሁሉም ሰካራም ሰው እኩል አይደለም" … ጢምቢራው የዞረና ያልዞረ ጠጪ፤ ተበድሮና አበድሮ የሰከረ (ለምሳሌ ተከራይና አከራይ)፤ ለደስታው ማጣጣሚያ የሚጠጣ ሰው እና ለሐዘን ማስረሻው የሚጠጣ ሰው (ለምሳሌ አይስላንድ ስትሸነፍ በንዴት ስታሸነፍ በሀሴት የሚቸልስ) … ወዘተረፈ።

በስተመጨረሻም የምንጠብቀው ማስታወቂያ… "ሀገር ማለት የኔ ልጅ… በጠዋቱ ሻይህን እየጠጣህ በቢራ ፖስተር የምትሰክርባት ሰፊ ግሮሰሪ ነች … 18+"

2.ተሰዓት

ባለንበት አካባቢ ከሰዓት ላይ ብልጭ ያለች ፀሃይ ጎበኘችን … ድንገት ሳይታሰብ (ዳመናው አሰባስቦትና አስቦበት ሊሆን ይችላል፤ እኛ ግን አልተዘጋጀንበትም) ከባድ ዝናብ ጣለ፤ መኪና የሌላቸው የኔ ቢጤዎች ወደ ቀረባቸው መጠለያ እየሄዱ ተጠለሉ፤ መንገዶች በውሃ ማዕበል ተንጣለሉ። ዶፉ ሲጠፋ የተደበቅን ሁሉ ከየምሽጋችንን  ወጣን። ስንወጣ ምን ገጠመን? … በቄንጠኛ አረማመድ የምንንጎማለልባው ቦታዎች ሁሉ መካከለኛ የዋና ገንዳ መስለዋል። ወደ ጉዳዮቻችን ለማቅናት ስለቸኮልን የመሸጋገሪያ መላዎችን መምረጥ ጀመርን። አማራጮቹም፡-

ሀ. በመዝለል

ለ. በአዛይ በመታዘል

ሐ. በመዋኘት

መ. ፀሐይ እስኪወጣ በመጠበቅ

የተጨናነቀ መንገድና ነፃ ምርጫ ስለታጨቀ ሁሉም የሚያዋጣውን መረጠ። አብራን ያለች ወዳጃችንን ለማያውቃት -ምራቅ ለማስዋጥ እንጂ ለውሃ አጣጪነት አትመረጥም … ቀሽት፣ ቀበጥና ስትወስን የምትፈጥን። መታዘል ደብሯት ይሁን ክፍያው ከንክኗት ሳናውቅ 'ሀ'ን መረጠች፤ ዘለለች። ተንደርድራ ስትዘል የግራ እግር ጫማዋን ጎርፍ ይዞት ነጎደ፤ እኛ ተናደን ግዑዝ ነገሮችን ሁሉ ረገምን … ውሃውን፣ መሬቱን፣ ንፋሱን፣ አስፋልቱንና ወዘተረፈን ረገምን። ከጎን ያለው አዝሎ አሻጋሪ ግን በጫማው ዙሪያ ቀለደ … "አይዞሽ የቀኙን ሳምፕል ይዘሽ ግንፍሌ ወንዝ ጠብቂው ታገኚዋላሽ"። … እባካቹ ጉዳዩ የሚመለከታቹ ወይም 'ንዲ ንብረት ሲሰወር የተመለከታቹ - የከተማ ባቡሩን እንዳመጣቹ ትንንሽ ጀልባዎችን ጀባ በሉን እንጂ በቀጣይ በአዲስ አበባ አስፋልት ሁኔታ እኛ ራሱ የፒያሳ ታክሲ ልንይዝ ወጥተን ጎርፉ ሳሪስ እንዳይዘረግፈን።   

በዚህ ሁሉ አዙሪት ውስጥ ውዬ ቤት ስገባ ግራ ገባኝ። ሄሎ የጎርፍ ሀገር - የዘነበው ከ'ላይ ከሰማይ ወይስ ከ'ስር ከምድር? … ኮፍያዬ ደረቅ ካልሲዬ ግን እምክ እምቅ። ከአየር ንብረት ትንበያ ዜና ላይ የመንገድ ንብረት ትንበያ ይታከልበት … - "በነገው እለት በሚጥለው ከባድ ዝናብ በአንዳንድ አካባቢዎች ያሉ መንገዶች በውሃ ስለሚዘጉ ከዣንጥላ ውጪ ከዘራና ከስክስ ጫማ መያዝ እንዳትዘነጉ"

3.የቢራ ሰዓት

ይኸው የክረምቱን ጨፍጋጋነት ለመዘንጋት እየተጎነጨሁ ስንኝ አሰናኘሁ። የፃፍኩበት ቦታ ከከተማዋ ጥግ ከሚገኝ ወንዝ ዳር ሳይሆን በመሀል ከተማዋ በሚገኝ ባር ስር ባለ ነው።  ዜማው ሰነድ አልባ ነው ብላችሁ የግጥሙን መታሰቢያነት ለሌላ አካል እንዳትሰጡት፤ መታሰቢያነቱ ትናንት በፆታዬ ምክንያት ብዙ ወንዶች የመኪና ሊፍት ሲከለክሉኝ - በመጀመሪያ በዣንጥላሽ ላስጠለልሽኝ ቀጥሎም በትንፋሽሽ ላሞቅሽኝ ጉብል ይሁንልኝ።

ለአዲስ አበባ አስፋልት

እንኳንስ ዘንቦብሽ እንዲያውም እርጥብ ነሽ (ርዕስ ነው)

ወይ አዲስ አበባ - አወይ አዱ ገነት

ወዞችሽ ይከስማሉ - ፀሀይ የከፋ 'ለት

ወንዞችሽ ይሞላሉ - ካፊያ የጣለ 'ለት

***

ቺርስ ውሀን በውሃ - አታኩርፉ እርሱት

ተዳፋሪውን ጎርፍ - በጠጃችሁ አርሱት

ሞቅ ይበል ሙዚቃው - ጭመቂኝ በሙቀት

እሾህን በእሾህ ነው - እሳትንም በእሳት

***

ቅዝቃዜና ወበቅ ሲፍታቱ በአየሩ

በአንድ … ሁለት ብርሌ ሲያዞረን ስካሩ

"ጌሾውን ቀንሱ - ጣፋጩን ጨምሩ"

ብለን ለጠየቅነው - አስካሪ አምራሪዎች ይህን ተናገሩ

"በብርጭቆ ግጭት ሀገር አታማሩ - ጥልቅ ነው ችግሩ

ከመጥ -ጠጥ አምልጦ ዜማ ውስጥ ሰጥሟል - ስኳርና ማሩ"¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
530 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1064 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us