የዓመቱበጎሰውሽልማት የመጨረሻዎቹዕጩዎችታወቁ

Wednesday, 24 August 2016 14:01

 

ጋዜጣዊ መግለጫ

ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደውና ለሀገራቸውና ለወገናቸው ላቅ ያለ አገልግሎት የሰጡ ዜጎች የሚከብሩበት የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብር ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ በአቤል ሲኒማ አዳራሽ ይከናወናል። በዕለቱ የክብር እንግዶች፣ ተሸላሚዎች፣ ዕጩዎች፣ ታዋቂ ሰዎችና መገናኛ ብዙኃን  በሚገኙበትሥነሥርዓቱይከናወናል።

የበጎ ሰው ሽልማት ኮሚቴ ያለፉትን ሦስት ዝግጅቶች ሂደት ሲያከናውን እንደኖረው ለዚህ ክብር መብቃት አለባቸው የተባሉ ዜጎች በሕዝቡ የተጠቆሙ ሲሆን፤ በየዘርፉ ከተጠቆሙት ዜጎች መካከልም ሥራዎቻቸው ተመዝነው ሦስት ሦስት ዕጩዎች ተለይተዋል። በእነዚህ እጩዎች ላይ አምስት አምስት ዳኞች (በየዘርፉ) ደምጽ እየሰጡ ነው። የየዘርፉ ተሸላሚዎችም ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓም በሚካኼደው ሥነ ሥርዓት ይከበራሉ።

መገናኛ ብዙኃንና ሌሎች የመገናኛ አካላት እጩዎችን በማስተዋወቅና በማክበር ለሀገራቸው በጎ የሚሠሩ ዜጎችን ለማብዛት የበኩላቸውን እንዲወጡ እየጠየቅን ዕጩዎቹን በየዘርፋቸው እንደሚከተለው እንገልጣለን።

1.  መምህርነት

·         ተ/ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው (በአዲስ አበባ ዩኚቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ መምህር)

·         ተ/ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የነበሩ)

·         መ/ር አውራሪስ ተገኝ (ምሥራቅ ጎጃም፣ ቢቡኝ ወረዳ የሚገኙ፤ በዘውዴ ልየው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር)

2.   ንግድና ሥራ ፈጠራ

·         አቶ ብዙአየሁ ታደለ (የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግስ ባለቤት)

·         አቶ ሳሙኤል ታፈሰ (የሰንሻይን ሪል እስቴት ባለቤት)

·         አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ (የኅብረት ኢንሹራንስ ኩባንያ መሥራች)

3.   ማኅበራዊ ጥናት

·         ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ (የግእዝ መዛግብትን በማጥናት የታወቁ ሊቅ)

·         ዶክተር አንዳርጋቸው ጥሩነህ (በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ የታሪክ ምሁር)

·         ፕሮፌሰር ባየ ይማም (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልሳን ሊቅ)

4.   ሳይንስ

·         ሎሬት ዶክተር መላኩ ወረደ (በኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወት ላይ የሠሩ ሳይንቲስት)

·         ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ (በኢትዮጵያ ሥነ ምኅዳር  ላይየሠሩሊቅ)

·         ዶክተር ወንዱ ዓለማየሁ (የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ እንዲቋቋም ታላቁን ሥራ ሠሩና፣ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ቤ ት ለቤት በመጓዝ የብዙዎችን ዓይን ያበሩ ሳይንቲስት)

5.   ቅርስና ባህል

·         የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ)

·         ኢንጅነር ታደለ ብጡል (የአኩስምን ሐውልት በማስመለስ፣ የኢትዮጵያን ቅርሶች በማስተዋወቅና የታላላቅ ሰዎችን ታሪክ በመመዝገብ የታወቁ ምሁር)

·         መ/ር ካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔር (የኢትዮጵያን ቃላዊ ቅርሶች የሚሰበስቡ ሊቅ)

6.   መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት

·         ኢንጅነር ዘውዴ ተክሉ (የአዲስ አበባን ከተማ ካስተዳደሩትና ለውጥ ካመጡት ከንቲባዎች አንዱ)

·         ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር (የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣንን ለብዙ ዓመታት የመሩ የአካባቢ ሳይንስ ሊቅ)

·         ዳኛ ስንታየሁ ዘለቀ (በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የኮንስትራክሽን ችሎት የሚያገለግሉ ዳኛ)

7.   ስፖርት

·            አቶ ጌቱ በቀለ (በሰበታ አካባቢ ስፖርትን ለማሳደግ የሠሩ ሰው)

·            ጋቶች ፓኖ (ከጋምቤላ ክልል ለብሔራዊ ቡድን የተመረጠ የቡና ክለብ የእግር ኳስ ተጨዋች)

·            ዶክተር ይልማ በርታ (የአትሌቲክስ ስፖርት አሠልጣኝ)

8.   ኪነ ጥበብ (ድርሰት)

·            አቶ አስፋው ዳምጤ (የሥነ ጽሑፍ ሰው፣ ሐያሲና ደራሲ)

·            ወ/ሮ ፀሐይ መላኩ (ሴት የረዥም ልቦለድ ደራሲ)

·            አቶ አውግቸው ተረፈ (የአጫጭር ልቦለዶች ደራሲና ተርጓሚ)

9.   ሚዲያና ጋዜጠኛነት

·            መንሱርአብዱልቀኒ (የስፖርትጋዜጠኛ)

·            አቶ አጥናፍ ሰገድ ይልማ (በኢትዮጵያ የኅትመት ሚዲያ ላይ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ አንጋፋ ጋዜጠኛ)

·            አቶ ደረጀ ኃይሌ (በቃለ መጠይቅ ጥበቡ የሚታወቅ ጋዜጠኛ)

10.  በጎ አድራጎት

·               ዶክተር ቦጋለች ገብሬ (የከምባቲ መንቲ ገዚማ-ቶፔ `የከምባታ ሴቶች አንድ ላይ ተነሥተዋል` የተሰኘው ድርጅት መሥራችና በከማባታ ሴቶች ሕይወት ላይ ለውጥ ያመጡ ሴት)

·               ወ/ሮ ፀሐይ ሮቺሊ (የሰላም ሕጻናት ማሳደጊያ መንደር መሥራች)

·               ወ/ሮ ዘውዲቱ መሸሻ (ሕይወት የሕጻናትና ቤተሰብ መርጃ ድርጅት መሥራች)¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
585 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 949 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us