አሁንም ስለ አገር. . .

Wednesday, 14 June 2017 13:17

 

ግንቦት 9 ቀን 2009  በሰንደቅ ጋዜጣ ዕትም “ስለ አገር ፍቅር ትንሽ ለመወያየት” በሚል ርዕስ ከነገሥታት እስከ ልዩ ባለሙያዎች (ነገሥታት ደራሲያን የህክምና ባለሙያ) ስለ አገር ፍቅር የተናገሯቸውንና የፃፏቸውን ጥቂት ልባዊ ቁምነገሮች አቅርቤ ነበር። እነኚያን ብልህና ተደናቂ አነጋገሮች እኔ ላቅርባቸው እንጂ ምንጩ የዶ/ር አምባቸው ከበደ “መፅሐፈ ጥቅስ የታዋቂ ኢትዮጵያውያን ከተናገሩትና ከፃፉት” (2007) ነው። ይህ አገርን በተመለከተ ሁለተኛው ክፍል ነው።

-    “የሀገሩን ትምህርት ጽሕፈት ቋንቋ እንደሚገባው የማያውቅ፣ የውጭውን እማራለሁ የሚል ምሳሌው ቀዛፊ እንደሌለው ታንኳ ነው”

ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ (ቀ.ኃ.ሥ)

-    “ለሰው ልጅ ክብሩና ኩራቱ አገሩና ነፃነቱ ናቸው”

ቀ.ኃ.ሥ በልዕልት ፀሐይ ሞት (1934)

-    “ለኢትዮጵያ ነፃነት ለልጆቿ ክብር

ሰንደቅ ዓላማችን ዘላለም ትኑር

                     አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ (የሰንደቅ ዓላማ መዝሙር)

-    “እናት ሀገር ኢትዮጵያ እንደ እንጉዳይ በሚፈሉ ጀግኖች ልጆችዋ በአንድነቷ ታፍራና ተከብራ እንደምትኖር የማያጠራጥር መሆኑን በሙሉ እምነቴ አረጋግጣለሁ”

ፕሮፌሰር አሰራት ወልደየስ ፤ በመአሕድ የወጣቶች ምስረታ

-    “እኛ የቆምነው ለጎሳነትና ለነፃ አውጪነት ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነት ነው”

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ (አእምሮ ጥቅምት 1986)

-    “የአንድ ሀገር ነፃነትም መብትም የሚጠበቀው በሕዝብ ሕብረት ነው”

ሌፍትናንት ጀኔራል አቢይ አበበ (አውቀን እንታረም)

-    “ተንኮለኛ እያለ ሸረኛ ጠማማ

መንግስት አይበረታም፣ አገርም አይለማ

ከበደ ሚካኤል (አንባል ገጽ 59)

-    “የገር ፍቅር የሚሉት ጌሾና ብቅል

ሆድ ያባውን እሱ ያስለፈልፋል

               አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ (አቦጊዳ ፊደል ገጽ 26)

-    “ደሙን ለሀገሩ የሚነፍግ ሰው

ውሃ የሌለበት ደረቅ ወንዝ ነው”

               ብላታ ወልደጊዮርጊስ ወ/ዮሐንስ (የወንድ ልጅ ኩራት)

-    “ከድህነት ሁሉ የሀገር ድሃ መሆን ታላቅ ጉዳት ነው”

ብላታ ወልደጊዮርጊስ (አግአዚ ገጽ 60)

-    ሕዝብ እስከ ጊዜው ቆሞ የሚሄድ የሀገሪቱ ጭቃና አፈር ነው”

ዓለማየሁ ሞገስ (ሀገር ምንድናት ገፅ 1)

-    “ፍጥረት ሁሉ ፍሬ ያለው ነገር የሚሠራው መሪ ሲኖረው ነው። ያንድ ሀገር ስልጣኔና ዕድገት ብዙ ጊዜ እንደ መሪው ይሆናል። በትጉሁ ጊዜ ይዳብራል፤ በሰነፉ ጊዜ ይኮስሳል። በጥቅም አባራሪው ጊዜ ይወድማል፤ ባጭበርባሪው ጊዜ ይጠፋል”

ዓለማየሁ ሞገስ (ከላይ በተጠቀሰው መፅሐፍ)

-    “የተወደደች አገራችን ዘወትር በጠላቶች ተከባ ስትኖር ነበረች። ትኖራለችም። ነገር ግን በእግዚአብሔር ቸርነት የውጭ ጠላት ከዚህ በፊት አላዋረደንም። አንድነትም ስንሆን ምንም የሚደፍረን እንደ ሌለ ታሪክ ይመሰክራል። ዘወትርም በስምምና በፍቅር አድረን ብንሆን እስከ ዛሬ ድረስ ብዙውን ትልልቅ ነገር መፈፀም እንችል እንደነበር ጥርጥር የለውም”

ገብረሕይወት ባይከዳኝ (አጤ ምኒልክና ኢትዮጵያ ገፅ 18)

-    አገር በርኅራሄና በብልሃት ነው እንጂ በጭካኔ መች ይገዛል”

     እቴጌ ጣይቱ (ለራስ ቢትወደድ ተሰማ ሰኔ 28 ቀን 1902 ከጻፉት ደብዳቤ)

-    “እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር ሰጥቶ አገሩን የማያድን ሰው ከዚህ የሌለ አይምሰልህ፤ የገዛ ደሙን ገብሮ ለገዛ አገሩ መሞት ጌጥ ነው እንጂ ሞት አይባልም”

አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ (ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ገፅ 75)

አቅራቢ ማዕረጉ በዛብህ 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
276 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1051 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us