ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የዳያስፖራው ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል

Wednesday, 21 June 2017 13:56

                         

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ሕዝብ በአንድ ዓላማ ዙሪያበማሰባሰብ ብሔራዊ መግባባት የበለጠ እንዲጠናከር ዕድል የፈጠረ  እንዲሁም የዘር፣ የሀይማኖት ወይም የሀብት ልዩነቶችን በቅድመ ሁኔታ ሳያስቀምጥ ህዝቦችን ለአንድ ዓላማ ያሰለፈ ታሪካዊ ግድብ ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ የሚሰጡት የድጋፍ ርብርብ ተጠናክሮ የቀጠለው ግድቡ የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት ከማሳደግ ባሻገር የኢኮኖሚውን ዕድገት ለማፋጠን እንደሚረዳ በሚገባ በመረዳታቸው ነው፡፡ በሀገሪቱ ለረጅም ዘመናት የዘለቀውን ድህነት ከመሠረቱ ለመንቀል የሚደረገውንም ትግል እንደሚያግዝ በመገንዘባቸው ነው፡፡

የግድቡ ግንባታ መጀመር ሲበሰር ግንባታው የሚካሄደው በሀገር ውስጥ ሀብት እንደሆነ በማያሻማ መንገድ መገለፁ ደግሞ የህዝባችንን መንፈስ በማነሳሳት የእውቀት፣ የጉልበትና የሀብት አስተዋጽኦውን እንዲደርግ ምቹ ሁኔታ ፈጥሮለታል፡፡ ይህ የድጋፍ እንቅስቃሴ በሀገር ውስጥ ከሚኖረው ህዝባችን በተጨማሪ በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንንም በስፋት ያሳተፈ ነው፡፡

የግድቡ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 6ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ  በዱባይ መጋቢት 22/2009 ዓ.ም በዓሉን በድምቀት ያከበሩት በዱባይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንኳን የ152 ሺህ 400 አሜሪካን ዶላር ቦንድ ግዢ ፈጽመዋል እንዲሁም አንድ ራቫ 4 የተሰኘ ተሽከርካሪ በስጦታ አበርክተዋል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም በተመሳሳይ ዕለት አቡዳቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲበዓሉን ያከበሩት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የ41‚000 አሜሪካን ዶላር ቦንድ ግዢ ፈጽመዋል፡፡

በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ይህ ዓይነቱን የገንዘብና የቁሳቁስ ስጦታ ሲያደርጉ የመጀመሪያቸው አይደለም፡፡ ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ድጋፍ ሲያደርጉ የቆዩ በመሆኑ ከፍተኛ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ በቀጣይ ለሀገራችን እድገትና ብልጽግና ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ለሚያደርገው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ምን ያህል የጋለ ስሜት እንዳደረባቸው የሚያሳይ ነው፡፡

ከመካከለኛው ምስራቅ ወጣ ስንል ነዋሪነታቸውን በቻይና ሻንጋይ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን በዓሉን ባከበሩበት እለት የ25ሺ300 አሜሪካን ዶላር ቦንድ ገዝተዋል፡፡ እነዚህን ጥቂት ሀገራት ለአብነት ጠቀስን እንጂ በመላው ዓለም የሚገኘው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ከመጋቢት ወር 2009 ዓ.ም  እስከ ሰኔ 2009 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ውስጥ የግድቡን 6ኛ ዓመት ሲያከብር የተለያዩ ድጋፎች በማድረግ  ለግድቡ ያለውን ሀገራዊ ድጋፍ ገልጿል፡፡

ዳያስፖራው ከግድቡ ግንባታ መጀመር አንስቶ በህዳሴ ቦንድ ግዢና ገንዘብ በመለገስ ያደረገውና አሁንም በማድረግ ላይ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ነው፡፡ ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ የዳያስፖራው ማህበረሰብ ከ40 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ድጋፉ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አማካኝነት ሳይቋረጥ እንደቀጠለ ነው፡፡ ነገር ግን ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሁሉንም ጥረትና ርብርብ ይጠይቃል፡፡

ዛሬ ከ2 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በመላው ዓለም በተለያዩ ሀገራት እንደሚኖሩ ይገመታል፡፡ ከዚህ አንፃር የዳያስፖራው ማህበረሰብ እያደረገ ያለው ድጋፍ ምንም እንኳን የሚበረታታ ቢሆንም ከዳያስፖራው ቁጥር አንፃር ሲታይ የተገኘው ድጋፍ መጠነኛ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በመሆኑም የዳያስፖራው ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች መሰራት አለባቸው፡፡ የግድቡ ግንባታ ከ58 በመቶ በላይ ከመድረሱ አንፃር ከግድቡ የግንባታ ሂደት ጋር የሚዛመዱ ወቅታዊ መረጃዎችን ለዳያስፖራው ማህበረሰብ ማድረስ አስፈላጊ ነው፡፡

ወቅታዊ መረጃ የዳያስፖራውን የድጋፍ መንፈስ ያበረታል፡፡ ለግድቡ ግንባታ ብቻም ሳይሆን በየትኛውም የሀገሩ ልማት መስክ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡እስካሁን ድረስ ዳያስፖራው ግድቡን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች በተለያዩ የህትመት ውጤቶች፣ በፊልምና ፎቶግራፎች አማካኝነት እንዲደርሱት እየተደረገ ያለው ጥረት መልካም ቢሆንም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡

የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ዜጎች የዓባይን ስም በስጋት ያነሳሉ፡፡ ስጋቱ ከክፋት የመነጨ ነው ተብሎ በኢትዮጵያ በኩል አይታሰብም፤ ይሁንና ኢትዮጵያ በራሷና በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት መካከል  ፍትሀዊ የሆነ የውሀ አጠቃቀም እንዲኖር ያላት ፍላጎት ከፍተኛ ከመሆኑም ባሻገር በአባይ ውሃ አጠቃቀም ላይ የምትከተለው  መርህ የጸና ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የተቃኘ የዲፕሎማሲ ስራ መስራት ትኩረት የሚሰጠው  ጉዳይ ነው፡፡

የዳያስፖራው ማህበረሰብ በገንዘብና ቁሳቁስ እስከዛሬ ሲያደርገው እንደቆየው ድጋፍ ሁሉ ወደፊትም ለሀገሩ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ሥራን አጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል፡፡ በግድቡ ዙሪያ የሚነዙ የተዛቡ አስተያየቶችን ማስተካከል፣ ግድቡ ሀገራችን ለተያያዘችው የድህነት ቅነሳ ትግል የሚያግዝ፣ ሀገራችን ለምትፈልገው የኃይል ፍላጎት መልስ የሚሰጥ እና የግድቡ መገንባት በተፋሰሱ ሀገራት ላይ አንዳችም ጉዳት የማያስከትል፤ እንዲያውም ዓመቱን ሙሉ የተመጠነ የውሃ ፍሰት እንዲኖራቸው  የሚያደርግ መሆኑን የማስረዳት ሀገራዊ ተልዕኮ ተሰጥቶታል፡፡

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የህዳሴ ግድብን የግንባታ ሂደት በአካል በስፍራው ተገኝተው ቢጎበኙ የመንፈስ እርካታ እንደሚያገኙ ግልፅ ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ግድቡን የጎበኙ የዳያስፖራ አባላት በተመለከቱት በመደነቅ “ማየት ማመን ነው” በሚል መንፈስ የቦንድ ግዢና የገንዘብ ስጦታ ለማድረግ ሲረባረቡ መታየታቸው ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡

ዳያስፖራ ወገኖቻችን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ በማድረግ ረገድ የማይተካ ሚና እንዳላቸው በማመን ድጋፋቸው ሳይነጥፍ በተጋጋለ መልኩ እንዲቀጥል ሁላችንም የተጠናከረ ስራ መስራት ይጠበቅብናል፡፡

በተለይ ደግሞ በውጭ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች፣ ሚሲዮኖች፣ ቆንስላ ጀነራል ጽ/ቤቶች፣ ቋሚ መልዕክተኞች፣ ንግድ ጽ/ቤቶች እና የኢትዮጵያ ህዳሴ ግ/ግ/ህ/ተ/አ/ብ/ ምክር ቤቶች አመቺ በሆኑ መንገዶች ሁሉ ስለ ግድቡ ወቅታዊ መረጃ በማቅረብ ዳያስፖራው ወደ ሀገሩ እየመጣ የግድቡን ግንባታ ሂደት እንዲጎበኝ እድሉን ሊያመቻቹለት የሚገባ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ማሳሰብ ተገቢ ነው፡፡

የዳያስፖራው  ተሳትፎ በፋይናንስ ድጋፍ ላይ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በፖለቲካ ድጋፍ፣ በዕውቀት ሽግግር እና በፐብሊክ ዲፕሎማሲውም መስክ የሚታይ ነው፡፡ ይህ ድጋፍ ወደፊትም ግድቡ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሚያጠራጥር አይደለም፡፡

 

ተጨማሪ መረጃ

.

 

የቦንድበአሜሪካንዶላር

     
   

በጀትአመት

ጠቅላላድምር

   
 

አህጉር

2003/04

2004/05

2005/06

2006/07

2007/08

2008/09

የ9ወር ሪፖርት

ድርሻበፐርሰንት

 

1

አፍሪካ

3,009,471.24

1,520,309.75

568,710.60

1,379,298.68

665,495.38

392,884.09

7,536,169.74

18.70%

 

2

አውሮፓ

1,834,753.02

1,053,605.15

1,265,146.78

186,460.00

700,770.52

145,189.76

5,185,925.23

12.89%

 

3

መካለኛው ምስራቅ

4,075,648.08

2,787,509.70

3,261,378.00

3,185,610.00

3,607,829.08

2,611,360.95

19,529,335.81

47.63%

 

4

አሜሪካ

3,977,017.00

2,136,720.79

714,857.52

67,690.00

82,288.48

17,738.83

6,996,312.62

17.48%

 

5

ኤዥያና ኦሺኒያ

281,807.28

145,907.77

138,489.08

276,800.00

414,235.38

71,580.65

1,328,820.16

3.27%

 

ድምር

13,178,696.62

7,644,053.16

5,948,581.98

5,095,858.68

5,470,618.84

3,238,754.28

40,576,563.56

100%

 

ጠቅላላድምር /USD/

40,576,563.56

 
 

ምንጭ፡- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ም/ቤት ጽ/ቤት

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
197 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 934 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us