የህገ-ወጥ እቃዎች መረጃ አሰጣጥ፣ አያያዝና

Wednesday, 30 August 2017 12:58

የወሮታ አከፋፈል

 

ማንኛውም ማህበራዊ፣ ኢኮሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ተገቢው ውጤት እንዲመጡ ህብተረሰቡን ማሳተፍ የመንግስትም ሆነ የተቋማት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግበራቸው መሆን ይጠበቅበታል።


የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንም ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በብቃት ለመሰብሰብ፣ ለልማታችንና ለልማታዊ ባለሀብቱ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንዲሁም ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር የሚያደርገውን ጥረት ለማስቀጠል ህብረተሰቡን የሚያሳትፉ እቅዶችን በማዘጋጀት እየሰራ ይገኛል። ግብር ከፋዩ ማህበረሰብና ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በበርካታ ጉዳዮች ላይ በጋራ እየሰራ ነው።


ኮንትሮባንድ በመከላከል፣ ህገ-ወጥ ንግድ፣ ታክስ ስወራ እና ታክስ ማጭበርበርን ማህበረሰቡ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ቀላል አይደለም። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ መመሪያዎችን በማውጣት ተግባራዊ አድርጓል። በዚህም የህገ-ወጥ እቃዎችን እንቅስቃሴ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ውስብስብ በመሆኑ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ አስፈላጊ ነው። የኮንትሮባንድ፣ የንግድ ማጭበርበር፣ የተከለከሉ ወይም ገደብ ከተደረገባቸው እቃዎች ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በይዘትም ሆነ በመጠን እየተበራከቱና እየተወሳሰቡ በመሄዳቸው በገበያው ወይም በህጋዊ ንግዱ እንቅስቃሴ፣ በመንግስት ገቢ አሰባሰብ እንዲሁም በህብረተሰቡ ደህንነት ላይ አደጋ የሚጥሉ መሆናቸውን፤ በዚህም እየታዩ ያሉ ችግሮች ለመቆጣጠር እና ለመከላከል የሚያስችል ስልቶች ተዘርግተዋል።

➡ የጥቆማ ምንነትና አቀራረብ


ጥቆማ ማለት ለባለስልጣኑ ወይም ለህግ አስከባሪ አካል ስለ ህገወጥ እቃዎች የሚቀርብ መረጃ ነው። በአገሪቱ የጉምሩክ ክልል በየትኛውም ስፍራ ህገ-ወጥ እቃ መኖሩን የሚያውቅ ማንኛውንም ሰው በአቅራቢው ለሚገኝ የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ወይም ህግ አስከባሪ አካል ማሳወቅ አለበት።

 

➡ ጥቆማ የማይቀርብባቸው ሁኔታዎች


በመመሪያ ቁጥር 78/2004 መሰረት የሚከተሉት ሁኔታዎች ጥቆማ አይቀርብባቸውም።
- በህዝብ የሚታወቁ ህገወጥ እቃዎች የሚገኙባቸው ቦታዎች፣
- ቀደም ሲል በጠቃሚ መረጃ የቀረበባቸው፣
- በአሳማኝና በበቂ ማስረጃ ወይም መረጃ ያልተደገፉ ጥቆማዎች
* ባለስልጣኑም ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች የጠቋሚውን መረጃ ካልተቀበለ በአፋጣኝ ለጠቋሚው በፅሑፍ የማሳወቅ ግዴታ አለበት።

 

➡ የጥቆማ አቀባበል


ባለስልጣኑ ወይም ህግ አስከባሪው አካል ህገ ወጥ እቃ ስለመኖሩ የቀረቡለትን መረጃ የሚቀበለው ከጠቋሚው በስተቀር በሌላ በማናቸውም ዘዴ መረጃውን ማግኘት የማይቻል ከሆነ ወይም ይህ የተጠቀሰው ቢኖርም የህገወጥ እቃዎቹ መረጃ ቀደም ሲል በባለስልጠኑ ወይም ህግ አስከባሪው አካል የሚታወቅ ቢሆንም የቀረበው መረጃ እቃው የሚገኝበትን ትክክለኛ ስፍራ የሚያሳይ ከሆነ ብቻ ነው።
ማንኛውም ጠቋሚ ለባለስልጣኑ የመረጃ ንዑስ የስራ ሂደት ጥቆማውን በጽሑፍ፣ በቃል፣ በስልክ፣ በፋክስ ወይም በማናቸውም የመገናኛ ዘዴዎችን ሊጠቀም ይችላል።

 

➡ የጥቆማ አመዘጋገብ


1. ማንኛውንም ጥቆማ በጥቆማ መቀበያ ቅጽ ላይ እንደቅደም ተከተሉ በጥንቃቄ ይሞላል፤ ጥቆማውን ላቀረበው ሰውም አንድ ቅጅ ይሰጣል።
2. ለህግ አስከባሪ የቀረበ ጥቆማ በ24 ሰዓት ውስጥ ባሉት የመገናኛ ዘዴዎች በአቅራቢያው ለሚገኘው የባለስልጣኑ መ/ቤት ይተላለፋል፤ በቁጥር (1) መሠረትም ይመዘገባል።


➡ የጥቆማ ሚስጥራዊነት


- በህገወጥ እቃዎች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም ጥቆማ እና የጠቋሚው ማንነት አግባብነት ካለው የባለስልጣኑ ሠራተኛ ወይም ኃላፊ በስተቀር ለማንም ሰው ወይም አካል ሚስጢራዊ ሆኖ ይጠበቃል።
- የጠቋሚውን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ማናቸውም የመረጃ ብክነት እንዳይኖር ባለስልጣኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋል።
- ከላይ የተጠቀሱት እንደተጠበቁ ሆነው በባለስልጣኑ የሚቀርብ ማንኛውንም ጥቆማ አስገዳጅና አሳማኝ ህጋዊ ምክንያት ከሌለ በስተቀር ተቋማዊ ይሆናል።

ማንኛውም የተቋሙ ሰራተኛ የተቀበለውን ጥቆማ መረጃውን ለማንኛውም ሰው በማናቸውም የመገናኛ ዘዴ አሳልፎ የሰጠ ወይም ሚስጥር ያባከነ እንደሆነ በወንጀል ህግ እና በዲሲፒሊን ይጠየቃል።

 

➡ ህግ ወጥ እቃን መያዝ፣ ማስረከብና ማስቀመጥ


- መስሪያ ቤቱ ወይም ህግ አስከባሪው ህግ ወጥ ዕቃ ለመኖሩ ጥቆማ እንደቀረበለት አቃውን ወዲያው ይይዛል።
- በህግ አስከባሪው አቃው የተያዘ እንደሆነ ባለበት ሁኔታ ተመዝግቦ በ48 ሰአት ወስጥ ለባለስልጣኑ እነዲተላለፍ እና ርክክብ እነዲፈጸም ይደረጋል።
- የተያዙትን እቃዎች በጥንቃቄ በመረከብ መ/ቤቱ ለሚመለከተው ሰው ወይም ክፍል ህጋዊ ማስረጃ ይሰጣል።

 

➡ የወሮታ ክፍያ እና አፈጻጸሙ


በጥቆማ ወይም ከጥቆማ ውጪ ህገ ወጥ እቃ ተይዞና ተወርሶ ለባለስልጣን መ/ቤቱ ገቢ ሲሆን ወይም በማንኛውም መልኩ ሲወገድ ለጠቆሙ ወይም ለያዙ እንደዚሁም ለተባበሩ ሰዎች የሚሰጥ ክፍያ ነው።
የወሮታ ክፍያ የሚከፈለው ለባለስልጣን መ/ቤቱ ገቢ የሆነው ህገ-ወጥ እቃ በሽያጭ ወይም በሌላ መንገድ እንዲተላለፍ ወይም እንዲወገድ ወይም የተያዘውና ዕቃ ቀረጥና ታክስ ተክፍሎ እንዲወጣ ከተደረገ ነው።
የጠቋሚነት ማስረጃ የተሰጠው ሰው የክፍያ ጥያቄ በሚያቀርብበት ወቅት የማስረጃውን ዋና ቅጂ ይዞ መቅረብ አለበት።

 

➡ ህገ-ወጥ እቃ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ እንደተደረገ የሚቆጠረው


- የተከለከለ እቃ ከሆነ በባለስልጣን መ/ቤቱ እንደተያዘ/እንደተረከበው፤
- ባለቤቱ ያልታወቀ ህገ-ወጥ እቃ ተይዞ በአዋጁ መሰረት የእቃው ባለቤት ነኝ ባይ እንዲቀርብ በማስታወቂያ ተጠርቶ በአንድ ወር፤ጊዜ ውስጥ ሳይቀርብ ከቀረ፤
- በህገ-ወጥ እቃው ባለቤት እና ተባባሪዎቹ ላይ ባሉበት ሆነ በሌሉበት በቀረበባቸው የወንጀል ክስ መሰረት ስልጣን የተሰጠው አካል ህገወጥ እቃ ላይ ውሳኔ ሲሰጥ እና አስፈላጊው ክፍያ ተከፍሎ እንዲወጣ ሲወሰን፤
- ቀረጥ እና ታክስ ማሳነስ ወይም ማጭበርበር በተፈጸመበት እቃ ለይ ሊከፈል የሚገባው ቀረጥና ታክስ እና መቀጫ ሲወሰን ህገ-ወጡ እቃ ገቢ ሆኗል ይባላል።

 

➡ የወሮታ ክፍያ መጠን


ሀ. ከቀረጥ ነጻ የገባን እቃ በማስተላለፍ ለጠቋሚ፣ ለያዝዥ እንዲሁም ድጋፍና ትብብር ላደረጉ የሚከፈል የክፍያ መጠን፦ በቀረጥ ነጻ ወይም በጊዜአዊነት ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ መብቱ በሌላቸው ሰዎች ወይም ድርጅት ይዞታ ስራ ሆኖ የተያዘን እቃ እንዲሁም መብቱ ኖሯቸው ከተፈቀደላቸው አላማ ውጪ ሲገለገሉበት የተገኘን እቃ በተመለከተ የሚከፈለው የወሮታ መጠን እንደ አግባብነቱ እቃው በተላለፈበት ጊዜ ወይም የእቃው የተላለፈብትን ጊዜ በትክክለ ለማወቅ የማይቻል ሲሆን እቃው ወደ ሀገር ውስጥ በገባ ጊዜ ይከፈል ከነበረው ቀረጥና ታክስ ላይ፡-


- ለጠቋሚ - 20%/ሃያ ከመቶ/
- ለያዥ ድጋፍና ትብብር ላደረጉ- 10%
- እቃው የተያዘው በህግ አስከባሪ ከሆ ለተቋሙ 30% ይከፈላል።

 

ለ. በኮንትሮባንድ የሚገባን እቃ ለጠቆመ የሚከፈል የክፍያ መጠን
በኮንትሮባንድ ወደ ሃገር ውስጥ የገባን እቃ በተመለከተ የሚከፈለው የወሮታ መጠን እቃው ወደ ሀገር ውስጥ ሲገባ ሊከፈል ይገባ ከነበረው ቀረጥና ታክስ ላይ፦
- ለጠቋሚ - 40%
- ለያዥ፣ ድጋፍና ትብብር ላደረጉ- 10%
- እቃው የተያዘው በህግ አስከባሪ ከሆነ ለተቋሙ 50% ይከፈላል።

 

ሐ. የንግድ ማጭበርብርን ለጠቆመ የሚከፈል የወሮታ መጠን
ማንኛም ሰው መክፈል የሚገባውን ቀረጥና ታክስ ላለመክፈል ወይም አለአግባብ ቀረጥና ታክስ ተመላሽ ለማድረግ መሞከሩ ጥቆማ ከቀረበና ጥቆማው በምርመ፣ራ ከተረጋገጠ ጥፋተኛ ከተባለ በተፈጸመው ህገ-ወጥ እቃ ላይ ሊከፍል በሚገባው ቀረጥና ታክስ ላይ በመመስረት፦
- ለጠቋሚ - 15%
- ለያዥ፣ ድጋፍና ትብብር ላደረጉ- 10% ይከፈላል።

 

መ. እሽጎችን በመፍታት የተፈጸመ ህገ-ወጥ ተግባርን ላጋለጠ የሚከፈል የወሮታ መጠን
ማንኛውም ሰውአግባብ ካለው የመስሪያቤቱ ሹም ፍቃድ ሳያገኝ አስፈላጊውን የጉምሩክ ስነ ስርዓት በመፈጸም ወደ ውጭ ሀገር እንዲወጣ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ በተፈቀደ ማጓጓዣ ወይም የእቃ መያዣ ላይ የተደረገውን እሽግ በመፍታት ወይም በመስበር እቃውን ማጉደሉ ጥቆማ ደርሶ ከተያዘ በተቀነሰው እቃ ላይ ሊከፈል ከሚገባው ቀረጥና ታክስ ላይ ወይም ቀረጥና ታክሱ ከእቃው የመሸጫ ጋር ሲነጸጸር አነስተኛ በሆነ ጊዜ በእቃው የገበያ መሸጫ ዋጋ ላይ በመመስረት፦
- ለጠቋሚ- 30%
- ለያዥ ለተባባሪ እና ደጋፊ- 10%
- እቃው የተያዘው በህግ አስከባሪ የተያዘ ከሆነ ለተቋሙ 40% ወሮታ ይከፈላል።


ሠ. ለሽያጭ የማይውሉ ህገ-ወጥ እቃዎች
እንደ ቅርሳቅርስ በህግ- የተከለከሉ የዱር እንስሳት ተዋጽኦዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ መድሃኒቶች ትምባሆ፣ ልባሽ ጨርቆች እና ሌሎች ህገ-ወጥ እቃዎች ከሆኑ ለባለስልጣን መ/ቤቱ የጠቆሙ የያዘ ድጋፍና ትብብር ላደረጉ ሰዎች በሚከተለው መልኩ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፦

 

➡ ህገ-ወጥ ልባሽ ጨርቅ ከሆነ የወሮታ ክፍያው በኪሎ 25 ብር ሂሳብ ተሰልቶ


- ለጠቋሚ 25%
- ለያዥ፣ ለተባባሪ እና ለደጋፊ 15%
- እቃው የተያዘው በህግ አስከባሪ የተያዘ ከሆነ ለተቋሙ 50% ወሮታ ይከፈላል።

 

➡ ህገ-ወጥ እቃው የገበያ ዋጋ የወጣለት ከሆነ ያዛኑ ዋጋ፦


- ለጠቋሚ 20%
- ለያዥ፣ ለተባባሪ እና ለደጋፊ 15%
- እቃው የተያዘወ በህግ አስከባሪ የተያዘ ከሆነ ለተቋሙ 40% ወሮታ ይከፈላል።

 

➡ ህገ-ወጥ ገንዘብ ሲያዝ ሚከፈል የወሮታ መጠን፦ የተያዘው ህገ-ወጥ ገንዘብ የውጭ ሀገር ገንዘብ ከሆነ ወደ ኢትዮጵያ ብር ተመንዝሮ፦


- ለጠቋሚ 15%
- ለያዥ፣ ለተባባሪ እና ለደጋፊ 10%
- እቃው የተያዘው በህግ አስከባሪ የተያዘ ከሆነ ለተቋሙ 30% ወሮታ የሚከፈል ሲሆን የተያዘው ህገ-ወጥ ገንዘብ የኢትዮጵያ ብር ከሆነ ግን 35% የሚከፈል ይሆናል።
በጠቋሚ፣ በያዥ፣ ድጋፍና ትብብር በማድረግ ሂደት በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ የሆኑ ሰዎች በጋራ ከጠቆሙ ከያዙ ድጋፍና ትብብር ካደረጉ የወሮታ ክፍያው እንደ ድርሻው ተፈጻሚ ይደረግላቸዋል። እነኚህ ባለድርሻ አካላት የወሮታ ክፍያቸው ተፈጻሚ ሳይሆን በሞት ከዚህ ዓለም ቢለዩ መብቱ ህጉ ለሚፈቅድላቸው ባለመብቶች የሚተላለፍ ይሆናል።


ምንጭ፡- የገቢዎችን ጉምሩክ ባለሥልጣን¾

 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
150 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 886 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us