የነፍጠኞች ትምክህትና ሀገራዊ ርዕይ

Wednesday, 03 January 2018 17:11

የነፍጠኞች ትምክህትና ሀገራዊ ርዕይ 

በ“ነፍጠኛ ስንኞች” የግጥም መድበል!

 

መልካሙ ተሾመ - ጠበቃና የሕግ አማካሪ - ከባሕር ዳር

 

‹‹ነፍጠኛ ስንኞች›› የተሰኘችዋን የግጥም መድበል ሸምቼ ደጋግሜ ዘለቅኋት። ብዙ ደስ አለኝ፤ ብዙ ተነሸጥሁ፤ ጥቂት አዘንሁ፤ ከጥቂት ጥቂት ከፍ ያለ ተበሳጨሁ። ይህን ሁሉ ስሜቴን በተደራሲነት መብቴ ጀቡኜ እንደሚከተለው ጣፍሁት። ይህ ጥሑፍ ነፍጠኛ ስንኞችን በማሄስ ወይም በመዳሰስ ዓላማና ቅርፅ አልተሰናድቶም። እንዲሁ በነፃ እይታ ተጣፈ እንጅ።


ገጣሚ መላኩ አላምረው (መለኛው) በፌስቡክ መንደር ‹‹መለኛ ሐሳቦች›› በሚል ገጹ ባለ ከባድ ሚዛን ቦክሰኛ ሆኖ ሲጫወት አውቀዋለሁ። ጎጃም/ሰከላ ተወልዶ አድጎ የሸገር ኗሪ ለመሆኑም ‹የፕሮፋይል› መረጃው ያሳያል። ጎጃሜ ሁሉ ባለቅኔ ነውና ጃል!


ይህ ወጣት ገጣሚ ስለ ሀገር ያገባኛልን በግጥም አዋሕዶና ቀምሞ ‹‹ነፍጠኛ ስንኞች›› ብሎ በሰየመው መድብሉ የአገሬ ፖለቲካ የሁልጊዜ መነሻና መድረሻ ስለሆነው ነፍጠኝነት የራሱን ሙግት ይዞልን ቀርቧል።


1/ “ነፍጠኛ ስንኞች”ን እኔ እንዳነበብኩት፡-


የመጀመሪያ መጀመሪያዋን ገጽ (cover page) እንዲህ ሾፈናታል።


የመደቡ ጥቁር መሆን ጣሊያን፣ እንግሊዝ፣ ግብጥ፣ ሱማሊያ፣ ሱዳን…ወዘተ የቃጡብንን ቅኝ የመግዛት ሙከራ እና ወረራ፣ በጦቢያችን ላይ የጋረጡብንን አደጋ ያመለክታል። የአምስት ዓመት የፍዳ ዘመን፣ የአህመድ ግራኝን የጨለማ ጊዜያችንን ይጠቁማል። የዘመነ-መሳፍንትን ጥቀርሻ የታሪክ ምዕራፋችንን ይገልጥልናል። በዴሞክራሲ እና በፍትህ በኩል ደግሞ የሁልጊዜ የጨለማ በርኖሳችንን ይወክላል። ጥቁሩ ሙሉ ገጹ መሆኑ የሚነግረን በስተቀር ያለመኖሩን ነው። ጨለማው የሁላችንም ነበር፤ ነው። አብሮነታችን ጨለማውን በመጋራት፣ ጥቁር ሸማችን አብሮ በመልበስም ነው።


በዚህ ጥቁር መደብ ላይ በቀጫጭን አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ መስመሮች፣ የተሰራች የኢትዮጵያ ካርታ አለች። ኢትዮጵያ እልፍ ፍዳና መከራ ተከፍሎባት ከጥቁር ባህር የተበጀት እንቁ ናት ሲለን ይመስለኛል። መስመሮቹ መቅጠናቸው ስለምንድነው ብንለው ዛሬ የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ላይ ስለመውደቁ ለመግለጥ፣ ለመጠቆም ነው የሚለን ይመስለኛል። መለኛው በአንድ በኩል ሙሉዋን ኢትዮጵያን በመሳል ኤርትራን እንደ ድሮዋ አንድ የኢትዮጵያ ክፍል ናት ማለት ሲቃጣው በሌላ በኩል ደግሞ ቀይ ባህርን ሌላ አገር ያደረገ የራስን ዕድል በራስ መወሰን ይሉት ፖለቲካ ኢትዮጵያን ጨርሶ እንዳይበትን የፈራ ይመስላል።


ከቀደመ ጠባዩ ተነስተን አደጋው ቢያሳስበውም በኢትዮጵያ ተስፋ አልቆረጠም፤ ይልቁንም ኢትዮጵያ ወደ ቀደመ ክብሯ ተመልሳ ኤርትራንም ይዛ ልዕለ-ኃያል ትሆናለች የሚል ሩቅ አላሚ ነው ማለት እንችላለን። ወዲያውም የዓባይ ልጅ ነውና እንዲህ መተለቅ ይጠበቅበታል። ኤርትራ ሌላ አገር ሆና ሳለ፣ የመመለሷም ነገር የማይታሰብ ሆኖ ሳለ መለኛው ይህንን ሁሉ ዘልሎ የጃንሆይ ዘመንን ኢትዮጵያ ይዞ ብቅ የማለቱን ነገረ-ምክንያት ብንፈልግ የኢትዮጵያን ህልውና ከጨለማው ባህር ከጥቁር አለት ያጎነቆሉ አባታቶቻችን ልጆች ነንና የሚያቅተን የማንችለው የለም የሚል ትምክህት የሚል መልስን እናገኛለን ይመስለኛል። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
185 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 893 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us