አውቀን ወይንስ ሳናውቅ?

Wednesday, 31 January 2018 13:17

 

አሰፋ አደፍርስ / This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

 

ዛሬ በኢትዮጵያ ስለሴቶች እኩልነት ሲወሳ በመስማቴ በጣም ደስ ብሎኛል። 

 

የሴቶች እኩልነት ለኢትዮጵያ አዲስ ሆኖ በብዙ የመገናኛ፤ በሬድዮና በጋዜጣስገለጽ፤ መንግሥትም አዎንታ ሰጥቶ ማየቱ በጣም ደስ የሚል ነው። ለመሆኑ ከኢትዮጵያ በሴቶች እኩልነት የቀደመ አገር ይኖር ይሆን ብዬ መጠየቅ ግድ ሆነብኝ። በዕድሜ ባለፀጋዋ ኢትዮጵያ በሥልጣኔም ቀደምት ብትሆንም፤ በዙሪያዋ የነበሩት ከኋላዋ የተነሱት ሁሉ ሊቀድሟት ችለዋል። ለምን? ብለን ብንጠይቅ፤ እንደዛሬው የመገናኛ ዘዴው ባላመቸበትና ሌሎች ዓይናቸውን ባልከፈቱበት ዘመን የቀደመችን ኢትዮጵያን ለመውረር ያልሞከረ አልነበረም። 

 

በመጀመሪያ የታላቁ የነቢዩ መሐምድ ተከታዎች የነቢዩን ትዕዛዝ ኢትዮጵያን አትንኳት ያሉትን በመዘንጋት ወይንም በመዳፈር የመጀመሪያውን ጦርነት የከፈቱባት የባህር በር አልባ እንድትሆን ያደርጓት የኒሁ ነብዩ ተከታዮች በመሆኑ የአክሱም ሥልጣኔ እየተዳከመ መምጣቱን ማስታወስ ተገቢ ይሆናል። ፈረንጆች እንደሚሉትና አንዳንድ የኢትዮጵያ ዘመናዊ የታሪክ ሙሑራንም ያንን ተከትለው አፈ ታሪክ አዎንታ እንደሚሰጡት ሳይሆን በዓለም የመጀመሪያዋ ንግሥት ዮዲት እንደነበረችና በንግድም ቀይ ባህርን አቋርጠው ወደ ሩቅ ምሥራቅና ሌሎችም አገራት ንግድ እንዲጀመር ፈር ቀዳጅ ንግሥት የኢትዮጵያ ንግሥት እንደነበረች በልኪስ በተባለ ስም የሚጠሯት አረቦች ጽፈዋል።


ይህም ሆነ ያ፤ የኢትዮጵያን ቀደምት ሥልጣኔ ለማመላክትና ከቀደምቷ የሮማን ስልጣኔ፤ ከግሪክና ከግብፅ የ883 ዓመታት ዕድሜ ካላት የዛሬዋ ታላቋ ብሪታኒያ፤ ከፈርንሣይና ከጀርመን ቀድማ የሴትን ነፃነት ያወጀች ኢትዮጵያ እንደሴት ጨቋኝ፤ ቀደም ብለን የጠቀስናቸው እንደሴት ነፃ አውጪ ሆነው ሲወራላቸው በመስማቴ ቅር ብሎኝ ይህንን ለመግለጽ ተገደድሁ።


በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በ14ኛው ክፍለ ዘመን በታላቁና እንደፈላስፋ ይቆጠር በነበረው በዘረያቆብ ዘመነ መንግሥት ነበር የብትወደድ አምደመስቀል ባለቤት ብርሃን ዘመዳ የግራ ቢትወደድ፤ ልጇ መድህን ዘመዳ የቀኝ ቢትወደድነት ማዕረግ የተሾሙት። እንደዚሁም የዘራያቆብ ሴት ልጆች በወንዶች ቦታ ተተክተው ዋና ዋና ክፍላተ አገራትን በገዥነት መርተዋል፤ ዓመተ መሲህ የአማራ ጠቅላይ ገዥ፣ ድል ሰምራ የትግሬ ገዥ፣ አፅናፍ ሰምራ የጎጃም፣ ሮም ገነየላ የሸዋ፣ ፀብለ ማሪያም የቤጌምድር፣ መድህን ዘመዳ የዳሞት፣ ዓመተ ጊዮርጊስ የይፋት፣ ባህር መንገሻ የአንጎት፣ ሶፊያ የግድምና 10-አጽናፍሰገድ እነኝህ ሴቶች በ14ኛው ክፍለዘመን ከወንድ በላይ ሆነው ጠቅላይ ግዛቶችን ይመሩ እንደነበረ ታሪክ ምስክር ነው። በ1541 ዓ.ም ከመሐዲያን ጋር በተካሄደው ጦርነት፤ ጦሩ ሁለት ተከፍሎ አንደኛውን ንጉሠ ነገስቱ ሲመራ የሰሜኑን ጦር በበላይነት የመራችው ንግሥት ሰብለወንጌል ነበረች። እንግዲህ ከአገረ ግዥነት እስከ ጦር አዛዥነት የደረሱት ሴቶች በ14ኛውና በ15ኛው ዘመን በኢትይዕጵያ ነበር። ይህም ብቻ አይደለም።


በቅርቡ ልክ እንደምናውቀው አስመስለን የምናወድሳቸው የአደዋው ጀግናይቱ እቴጌ ጣይቱን የማይዘከር ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም። እላይ እንደገልጽኩት የኢትዮጵያን ቀደምትነት ካሳየሁ በኋላ እስቲ የእንግሊዝን እንመልከት፤ የመጀመሪያዋ የእንግሊዝ ንግሥት ኤልሳቤት የነገሠችው በሴፕቴምበር 7 ቀን 1533 እስከ እለተ ሞቷ ነበር። በዚህ ሁኔታም ቀደምትነታችን ይያዝልኝ። የትናትናዋ ወጣቷ የእንግሊዝን የበኩር ልጅ አሜሪካንን እንመለከት፤ የመጀመሪያዋ የሴት ሴኔተር የተመረች ረቤካ ፌልተን ነበረች። እርሷም ያገለገለችሁ ለአንዲት ቀን ብቻ ነበር። እንዴት ተመረጥች እንዴትስ ወረደች? የባሪያ ባለቤት ብትሆንም ባሪያን ነፃ ለማውጣት የምትጥር ስለነበረ ሴትን ብሎ የባሪያ ነፃ አውጪ ከሚል ቁጭት ካንድ ቀን በላይ ሳትውል መውረዷ ተዘግቧል። ታዲያ ኢትዮጵያ የሴትን ነፃነት የማታከብር አድርጎ አሁን እንደተከበረ ነጋሪት ሲመታ ማየቱ ላገራችን የታሪክን ተቀዳሚነት የነፈግን አይሆንምን? እባካችሁ ለጋራ አገራችን የሚገባትን ክብር እንስጥና የግል ዝናንና ጥቅም ሁለተኛ ቢሆንስ!


ትናንትና በኛው ዘመን በእንግሊዞችና አሜሪካኖች የመንግስት ባለሥልጣን ሴቶች ባልነበሩበት በ20ኛ ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ም/ሚኒስትር ዮዲት እምሩ፤ የትምህርት ቤት ዲሬክተር ስንዱ ገብሩ፤ የምክር ቤት አባል፤ የሬድዮ ዜና አንባቢ ሮማን ወርቅ ካሣሁንና ዛሬም በሕይወት የምትገኝ ሒሌን መኩሪያን መጥቀስ በቂ ቢሆንም ሴት አርበኞቻችንን ረስቼ ሳይሆን ለናሙና ይህንን ካቀርብኩኝ በኋላ መቼ ነበር ታላቋ ቢሪታኒያ እኛ ዘንድ የደረችው ብለን ራሳችንን ብንጠይቅ፣ እንኳንስ ለታላላቅ ሹመት ቀርቶ ለመምረጥና ለመመረጥ እንኳ ዕድሉ የተሰጣቸው በ1960ቹ መሆኑን ተገንዝበን ይሆን? ታዲያ ቀደምቷ ኢትዮጵያ ለወሬ ማሟሻ ይመስል የሴቶች ነፃነት ዛሬ እንደተጀመረ ሲወራ የነበርነው አሜን ብለን መቀበል ስላላስቻለኝ ይህንን ማስታወሻ ለወገኖቼ አቅርቤ ባዶ ከበሮ ከመደለቅ ለማስታገስ ነውና ላሞች ባልዋሉበት ኩበት እንዳንለቅም አደራ እያልኩ ሁሉንም በአክብሮት አሳስባለሁ።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
140 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 936 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us