ስድስተኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብር የዕጩዎች ጥቆማ መስጠት ቀጥሏል

Wednesday, 23 May 2018 14:35

 

ለሀገርና ለሕዝብ አርአያነት ያለው ታላቅ ተግባር ያከናወኑ ሰዎችን ዕውቅና የሚሰጠው የበጎ ሰው ሽልማት ስድስተኛው መርሐ ግብሩን ከግንቦት 2 ቀን 2010 ዓ.ም አንሥቶ የእጩዎች ጥቆማ በመቀበል በይፋ እየተሰጠ መሆኑን አዘጋጆቹ ይፋ አድርገዋል። ስድስተኛው የበጎ ሰው ሽልማት ነሐሴ 27 ቀን 2010 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል።


ለዚህ የሽልማት መርሐ ግብር በአሥር ዘርፎች ማለትም
1. በመምህርነት ዘርፍ
2. ንግድና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ
3. ማኅበራዊ ጥናት ዘርፍ
4. ሳይንስ ዘርፍ
5. ቅርስና ባሕል ዘርፍ
6. መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት ዘርፍ
7. ኪነ ጥበብ (በሙዚቃ ዜማ ድርሰት ዘርፍ)
8. ሚዲያና ጋዜጠኛነት ዘርፍ
9. ለኢትዮጵያ በጎ ሥራ የሠሩ የውጭ አገር ዜጎች ዘርፍ
10. በጎ አድራጎት ዘርፍ


ከሕዝብ የእጩዎችን ጥቆማ በመቀበል ላይ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

 

በበጎ ሰው ሽልማት ከ2005 ዓ.ም አንሥቶ በተካሄዱት አምስት የሽልማት ወቅቶች፤ አገራችን የምትኮራባቸውና የላቀ አርአያነት ያለው ተግባር ያከናወኑ ሰዎች ዕውቅና የተሰጣቸው ከሕዝብ በቀረቡ ጥቆማዎችና በዳኞች ውሳኔ መሠረት ነው። የበጎ ሰው ሽልማትን ለዚህ ያበቃውም በሽልማቱ ሂደት የሕዝብ ተሳትፎ በመኖሩና ይህም ከዓመት ዓመት እያደገ ሄዷል ። ይህ ተሳትፎ አሁንም እንደሚቀጥል ጽኑ እምነት አለን ብለዋል፤ አዘጋጆቹ።


የበጎ ሰው ሽልማት ዓላማ ለሀገራችን ለኢትዮጵያ መልካም የሚሠሩ፣ ሀገራዊ ተልዕኳቸውን በብቃትና በልዩ ልዕልና የሚወጡ፣ የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ለውጥ አምጪ ተግባር የፈጸሙ፤ በብዙ ሰዎች የማይደፈረውን ተግባር በተነሣሽነት የከወኑ፣ለድጋፍ ፈላጊ የማኅበረሰቡ ክፍሎች ትኩረት በመስጠት ሀገራዊ ኃላፊነት ወስደው የሠሩ፣ የሀገሪቱ ታሪክ፣ ቅርስ፣ ባሕል፣ እንዲጠበቅ፣ የሀገሪቱ ሥልጣኔ ከፍ እንዲል የሠሩ ኢትዮጵያውያንን በማበረታታት፣ ዕውቅና በመስጠትና በመሸለም ሌሎች በጎ ሠሪዎችን ለሀገራችን ማፍራት ነው።


ስለዚህ ይህን የበጎ ሰው ሽልማትን ዓላማ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከላይ በተገለጹት መስኮች ግንቦት 2 ቀን 2010 ዓም እስከ ሰኔ 1 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ሕዝቡ ለዚህ ሽልማት ብቁ ናቸው የሚላቸውን እጩዎች ከሁሉም የሀገራችን ክልሎች እንዲጠቁም የበጎ ሰው ሽልማት አዘጋጆች ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
101 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 141 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us