የመንግሥትን የፕራይቬታይዜሽን እርምጃ ለምን እንደግፈዋለን?

Wednesday, 20 June 2018 13:06

 

አረጋ ይርዳው (ዶ/ር)

ዕድገትን በማንኛውም ደረጃ ላይ ያሉ ኩባንያዎችና ድርጅቶች በትኩረት ሊሠሩበት ይገባል። አድጓል፣ ገዝፏል፣ መጥቋል፣ የሚባል ድርጅት እንኳ ቢኖር ለቀጣይና ተጨማሪ እድገት የማይጥር ከሆነና ያለው ጥሩ ነው አይነካ የሚባል ከሆነ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ለተጨማሪ ዕድገት አለመዘጋጀት ውጤታማነትን ሊገታ ይችላል።  

ተወዳዳሪ የሌላቸው ኩባንያዎች ወይም ድርጅቶች ሥራን በሞኖፖሊ ከያዙ ዕድገታቸውን የሚያነጻጽሩበት የለም። ጥሩ ሠራን ብለው ስለሚያምኑ ሳያስቡት ችግር ውስጥ ይገባሉ። ስለዚህ የካፒታል ዕድገት፣ የሠራተኛ ቁጥር መጨመር፣ ትርፍን ማሳደግ፣ የግብር ክፍያን ማሳደግ የመሳሰሉት ሁሉ ከዕድገትና ጥራት ካለው አሠራር ጋር የተያዙ ናቸው። በመንግሥት ሥር ሆኖ የማምረት ሥራ ላይ መሠማራትና በግሉ ዘርፍ ሆኖ መሥራት በፍልስፍናው የተለየ ነው።

ከመጀመሪያው የ20 ዓመት የፕራይቬታይዜሽን ሙከራ በኋላ፣ አሁን መንግሥት ከፍ ከፍ ያሉ ድርጅቶችን ሙሉ በሙሉ ወይም ከሌላ ባለድርሻ ጋር ተጣምረው እንዲሠሩ የወሰደው ቀላል መሳይ ከባድ እርምጃ የሚደገፍ ነው። ይህ እርምጃ ኩባንያን ከማግዘፍ ወይም በትልቅነቱ ከመለካት ይልቅ በይበልጥ በሚያስገኘው ጥቅም መለካትን ያመጣል። ሥራ መፍጠር፣ ካፒታል ማሳደግ፣ አገልግሎትን ማቀላጠፍ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማጠናከር፣ ተወዳዳሪነትን ማሻሻል፣ መልካም አስተዳደርን ባህል ከማስፋፋት አኳያ ጥቅሙ ከፍ ያለ ነው፡ ይህ እርምጃ ወደ ካፒታሊዝም ወይም ማርኬት ኢኮኖሚ የሚደረገውን ጉዞ ያጠናክረዋል።

በሀገራችን ብርቅዬ የሆኑት እንደ አየር መንገድ የመሳሰሉ ጥቂት ድርጅቶች እስከ ዛሬ ያስመዘገቡትን ጥሩ ውጤት በይበልጥ እንዲያጠናክሩ ያገለግላል። ውድድር የዕድገት አጋር እንደመሆኑ፣ በግል ወይም በመንግሥትና በግል በጥምርት የተቋቋሙ ድርጅቶች የአሠራር ሁኔታዎች ምርትና ምርታማነትን ከጥራት ጋር በማቀናጀት ጥረት ስለሚያደርጉ ጥቅሙ ብዙ ነው።

ስለዚህ በመንግሥት ይዞታ ሥር ያሉ በማምረት ወይም አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የተለያዩ ድርጅቶች እንዲሁም በተወጃጁ አየር መንገድ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች፣ በባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ድርጅት ወዘተ ላይ የባለቤትነት ድርሻ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለግሉ ሴክተር ለማካፈል መንግሥት በቅርቡ መወሰኑ የሚደገፍ ነው።

የውጭ ንግድ በቀዘቀዘበት፣ የውጭ ምንዛሬ ኩባንያዎችን ሽባ እያደረገ ባለበት፣ ወጣቱ በሥራ ማጣት ፈተና ላይ ባለበት፣ ቴክኖሎጂ፣ ካፒታል ለተወዳዳሪነት አስፈላጊ በሆኑበት ወቅት የተወሰደ ትክክለኛ የመንግሥት እርምጃ ነው።

ኢትዮጵያ ከሁለት በላይ ጠንካራ አየርመንገዶች፣ በዛ ያሉ የቴሌኮሙኒኬሽን ተቋማት፣ የባህር ዕቃ የማጓጓዣ አገልግሎት፣ ከፍ ያለ የውጭ ዕዳ የመክፈል ግዴታ ላይ ባለችበት ሁኔታ እነዚህን ታሳቢ በማድረግ የተወሰደ እርምጃ ነው የሚል እምነት ስላለን እርምጃው መደገፍ አለበት።

ከላይ ያለው እንዳለ ሆኖ ይህን ሽግግር ሥራ ላይ የማዋሉ ጉዳይ ራሱን የቻለ ጥንቃቄ ካልተደረገበት የታሰበውን ግብ መምታት አዳጋች ሊሆን ስለሚችል ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ድርጅቶቹን በተጠቀሱት ሞዳሊቲስ ማስተላለፍና ከተላለፉ በኋላ ውጤታማ ሆነው እንዲዘልቁ መምራት የተለያዩ ተግባሮች መሆናቸው ሊታሰብበት ይገባል። የባለሙያዎች እርብርብም በሰፊው ያስፈልጋል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
164 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 830 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us